Channel: #KALTUBE
በክርስቶስ IN CHRIST
ክፍል 61
እግዚአብሔርን ማወቅ
ዕረፉ፥ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ እወቁ፤ በአሕዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፥ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ። መዝ 46:10
➢ታላቅ የእምነት አባት የሆነውን አብርሃምን የማናገር እድል ቢገጥመንና እግዚአብሔር ላንተ ማነው ብንለው።ኤልሻዳይ (ሁሉን ቻይ አምላክ) ይለናል።
-ይስሐቅን እግዚአብሔር ላንተ ማነው ነው ብንለው ደግሞ የሚባርክ የበረከት አምላክ ይለናል።
-ያዕቆብን ብንጠይቀው ደግሞ ትንሹን ትልቅ፣ ጥቂቱን ብዙ የሚያደርግ ፣በትሬን ብቻ ይዤ ይህን ዮርዳኖስን ተሻግሬ ነበርና፥ አሁን ግን የሁለት ክፍል ሠራዊት ሆንሁ። ይለናል። ዘፍ 32:10
- ሙሴን እግዚአብሔር ላንተ ማነው ብንለው እንዲህ ይለናል :- ከግብፅ በታላቅ ተአምራት ያወጣን የአማልክት ሁሉ አምላክ ይለናል።
-ዳዊትን ብንጠይቀው እግዚአብሔር እረኛዬ ነው ይለናል።
➢አባቶችን ነቢያትን፣ነገስታትን፣ሐዋርያትን ሁሉ ብንጠይቃቸው የገባቸውን ያክል እግዚአብሔር ለኔ እንዲህ ነው ብለው ሊገልፁ ይችላሉ።
➢እግዚአብሔር ለእናንተ ማነው ብዬ ብጠይቃችሁ :ለኔ ፈዋሽ፣ጓደኛ፣ ኃያል፣ ሰጪ፣ ረዳት፣ተንከባካቢ፣እናትም፣እረኛዬ ፣አቅሜ፣ ፈራጅ ፣ዳኛ፣ፈጥኖ ደራሽ ነው ብላቹ ልትመልሱልኝ ትችላላችሁ። በርግጥ ትክክል ነው። እግዚአብሔር ካልነው ሁሉ በላይ ነው።
➢በህይወታችን ከእግዚአብሔር ጋር ያለን የልጅና የአባት ግንኙነት እግዚአብሔርን የበለጠ በተለያዩ መንገዶች እንድንረዳው ያስችለናል። ህብረታችን የሚወሰነው ስለሱ ባለን መረዳት ልክ ነው።ከመረዳታችን በላይ ከእግዚአብሔር ጋር ሕብረት ማድረግ አንችልም። ስለ እግዚአብሔር ያለን መረዳት ህይወታችንን የሚባርከው ምስጢር ነው።
➢የመንፈሳዊነት መጀመርያው እግዚአብሔርን ማወቅ በመሆኑ ሐዋርያው ጳውሎስ በኤፌሶን የነበሩ አማኞች እግዚአብሔር አብን በመገለጥ እውቀት ያውቁት ዘንድ ይፀልይ ነበር።
የክብር አባት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እርሱን በማወቅ የጥበብንና የመገለጥን መንፈስ እንዲሰጣችሁ እለምናለሁ። ኤፌ 1:17
➢ያለ መንፈስ እርዳታ እግዚአብሔርን ማወቅ አይቻልም።መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔርን ማወቅ የምንችልበትን ልቦና ይሰጠናል። መንፈስ ቅዱስ አብን በልቦናችን የሚገልጥልን ጣፋጭ መምህር ነው። በሚገባን መንገድ በመግለፅ ፣በእውቀት ለሚታደሰው አዲሱ ማንነታችን እውነትን ያብራራልናል።
➢ ልብ እንበል! እግዚአብሔርን ማወቅ ስለ እግዚአብሔር ማወቅ ማለት አይደለም።
መንፈስ ቅዱስ መረጃ ሊሰጠን (Inform ሊያደርገን ሳይሆን ሊለውጠን( transform) ሊያደርገን ነው የመጣው።እግዚአብሔርን ማወቅ የመረጃ እውቀት ሳይሆን ህይወት ለዋጭ ኃይልና ትርጉም አለው።
➢እግዚአብሔርን አለማወቅ በድቅድቅ ጨለማ መመላለስና ጥፋት ነው። እግዚአብሔርን አለማወቅ ያጠፋል።
ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል፤ አንተም እውቀትን ጠልተሃልና እኔ ካህን እንዳትሆነኝ እጠላሃለሁ፤ የአምላክህንም ሕግ ረስተሃልና እኔ ደግሞ ልጆችህን እረሳለሁ። ሆሴ 4:6
➢እግዚአብሔርን የማወቅ ጅማሬ
እግዚአብሔርን ለማወቅ ከመፈለግ ይጀምራል። ጥፋት ደግሞ እግዚአብሔርን ካለመፈለግ ይጀምራል።
እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው፤
ሮሜ 1:28
እግዚአብሔር ከመታወቅ ያለፈ አምላክ ቢሆንም ግን የማይታወቅ አምላክ አይደለም። ከዛሬ ጀምሮ እግዚአብሔርን እንወቀው፣ለማወቅ እንዘጋጅ።እንፈልገው!
✍ መሳይ አለማየሁ (ነቢይ)
ክፍል 62 ይቀጥላል
👇💐👇💐👇💐👇💐👇💐
@KALTUBE

ክፍል 62
የድንዛዜን ኃይል መስበር
የማታስተውሉ የገላትያ ሰዎች ሆይ፥ በዓይናችሁ ፊት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ተሰቀለ ሆኖ ተሥሎ ነበር፤ ለእውነት እንዳትታዘዙ አዚም ያደረገባችሁ ማን ነው? ገላ 3:1
አዚም የሚለው የእንግሊዝኛው ትርጉም bewitched ሲሆን ትርጉሙም “to exercise evil power over someone, like putting them under a spell.” ወይም መናፍስታዊ ኃይልን በመጠቀም ሌሎችን ተፅእኖ ስር መክተት ነው።
➢አዚም ልክ እንደ ማደንዘዣ ወይንም አንስቴዥያ ነው።እንደሚታወቀው ማደንዘዣ የሚያስፈልገው ለቀዶ ጥገና ህክምና ነው።
ማደንዘዣ ከሰውነት ወደ አዕምሮ የስሜት መልእክት የሚልኩ ነርቮችን በማገድ ወይም አቅጣጫ በማስቀየር ህመምን ለማጥፋ ያገለግላል። በዚህ ጊዜ አዕምሮ ንቁ አይሆንም ( Unconscious) ይሆናል። የደነዘዘው የሰውነት ክፍል ውስጥ የሚገኙ ነርቮች ምንም አይነት የስሜት አይነቶችን ወደ አዕምሮ አይወስዱም።
➢አዚም የተደረገበትም ሰው ለክርስቶስ ያለው ፍቅር፣ለመንፈሳዊ ህይወት ያለው ንቃተ ህሊና consciousnes ዜሮ ይገባል።ከዚህ በኋላ ብፀልይ ባልፀልይ ፣ቤተክርስቲያን ብሄድ ባልሄድ፣ወንጌል ብሰብክ ባልሰብክ ምን ችግር አለው ይላል።ለመንፈሳዊ ህይወት ደንዝዞ እንደመመላለስ ያለ ታላቅ ድንዛዜ የለም።
➢በብሉይ ኪዳን የነበረው ካህኑ ዔሊ መሰረታ ዊ ችግሩ የድንዛዜ ችግር ነበር።የጌታን ፈቃድ አያዳምጥም፣ለእግዚአብሔር የቀረበውን ቁርባን ቅድምያ በመብላት እና የቤተመቅደሱን ስርዓት ባለመጠበቅ፣እንዲሁም ልጆቹ አፍኒንና ፊንሐስ እጅግ ክፉ ኃጢአትን በቤተመቅደስ አደባባይ ሲፈፅሙ ዝም ማለቱ የመንፈሳዊ ድንዛዜ ምልክት ነበር።
➢የገላትያም ሰዎች በሆነ ወቅት ለክርስቶስ የነበራቸው ፍቅር የጋለና ሞቅ ያለ ነበር። ትኩረታቸውና ዋና የህይወት ማዕከላቸው እርሱ ነበር። የገላትያ ሰዎች መዳን በእምነት
መሆኑን አውቀው አምነው ድነዋል። ነገር ግን
ከጊዜ በኋላ መዳን የሚገኘው በእምነት ብቻ ሳይሆን የሙሴን ህግ በመጠበቅ
(በጥረትና በስራም) ነው ብሎ ወደማመን ትምህርት ተቀየረ።
➢ይህ ትምህርት የፈጠረው ድንዛዜ ክርስቶስ የሰራውን የመስቀል ላይ ስራ አሳንሰው እንዲያዩ ዳረጋቸው።ለመስቀሉ የነበራቸው መረዳት መበረዝ ሲጀምር መደንዘዝ ጀመሩ። እንደ ድሮው በተሰራላቸው ሳይሆን በሚሰሩት የፅድቅ ስራ መደገፍ ጀመሩ። በፊት ለጌታ የነበራቸው ፍቅር መላው የገላቲያ ከተማ ያውቅ ነበር፤ከጊዜ በኋላ ግን መረዳታቸውም፣ ስሜታቸውም ወደተሳሳተ መንገድ ተቀየረ።ስለ እምነትና ስለ ፀጋ ሲሰበክ ትርጉም አልሰጥ አላቸው።ምክንያቱም ህግን በመጠበቅ ጥረት ተጠምደዋል።
➢መንፈሳዊ ድንዛዜ ለመንፈሳዊ ህይወት ያለንን መሻትና መነሳሳት የሚገድል መርዝ ነው።ሰው በጌታና በተሰራለት ስራ መቀጣጠ ል ካቆመ፣ ግለቱ ከቀዘቀዘ በመንፈስ ቅዱስ መታከም አለበት።
➢አንዳንዶች አንደሚያስቡት በጌታ መቀጣጠል በክርስትና የልጅነት ወራት ላይ ብቻ ያለ አይደለም። ለጌታ ያለን ጋል ያለ ፍቅር ስናድግ የሚጠፋ፣አገልጋይ ስንሆን የሚያቆም ከሆነ ይሄ እድገትም አገልጋይነትም አይደለም።
ለዚህ ነው ሐዋርያው ጳውሎስ በታላቅ አግራሞት ማነው አዚም ያደረገባችሁ በማለት የገላቲያን ሰዎች የጠየቃቸው። መንፈሳዊ ድንዛዜ መፍትሔ አለው።
የመንፈሳዊ ድንዛዜ ጥሩ ጥሩ መድኃኒቶች:
1ኛ በመንፈስ ቅዱስ መሞላት (አፌሶን 5:18)
በመንፈስ መሞላት ዕለት ዕለት በቃሉ፣ በህልውናው እንድንኖር ያስችላል።
2ኛ በመንፈስ መመላለስ (ቆላስይስ 2:6)
በመንፈስ መመላለስ መንፈሳዊ መስመር ጠብቆ መሄድ ነው።ይህም ቃሉን በመታዘዝና በጤናማ ትምህርት ላይ ተመስርቶ ማደግን ያጠቃልላል።
ክፍል 63 ይቀጥላል

ክፍል 63
የባርነትን ቀንበር የሚሰብር ጩኸት
ከዚያም ከብዙ ቀን በኋላ እንዲህ ሆነ፤ የግብፅ ንጉሥ ሞተ፤ የእስራኤልም ልጆች ከባርነት የተነሣ አለቀሱ፥ ጮኹም፥ ስለ ባርነታቸውም ጩኸታቸው ወደ እግዚአብሔር ወጣ።
እግዚአብሔርም የለቅሶአቸውን ድምፅ ሰማ፥ እግዚአብሔርም ከአብርሃምና ከይስሐቅ ከያዕቆብም ጋር ያደረገውን ቃል ኪዳን አሰበ።
እግዚአብሔርም የእስራኤልን ልጆች አየ፥ እግዚአብሔርም በእነርሱ ያለውን ነገር አወቀ። ዘፀ 2:23-24
➢ እስራኤላውያን ለአራት መቶ ሰላሳ አመታት በግብፅ ባርነት ስር ተገዝተው ይኖሩ ነበር። በዚህ ረጅም ዘመናት ውስጥ ጡብ እየጠፈጠፉ፣የግብፃውያንን እርሻ እያረሱላቸው ፣እየገበሩላቸው ይኖሩ ነበር።
➢እስራኤላውያን ለአራት ትውልድ ያክል ከማጉረምረም ውጪ ወደ እግዚአብሔር ያሰሙት ጩኸት አለመኖሩ ያስደንቃል። ከአራት መቶ አመታት በኋላ ስለ ባርነታቸውም ጩኸታቸው ወደ እግዚአብሔር ወጣ። እስራኤላውያን መጮህ ሲጀምሩ እግዚአብሔር ሰማ። ጩከታቸው የርህራሄን አምላክ እግዚአብሔርን አንቀሳቀሰው።እግዚአብሔር ከአባቶቻቸው ከአብርሃም፣ከይስሐቅ፣ ከያዕቆብ ጋር የገባውን ኪዳንም አሰበ።
እስራኤላውያን የጮሁት የባርነት ኑሮ ስላልተስማማቸው ነው። እግዚአብሔርም ጩከታቸውን ሰማ። የባርነት ህይወት የእግዚአብሔር ፈቃድ አይደለም። በኢኮኖሚ ፣በመንፈሳዊ፣በማህበራዊ እና በተለያዩ ባርነቶች መኖር የጌታ ፈቃዱ አይደለም። እንደ እግዚአብሔር ልጆች እንዳንኖር የሚያደርገንን የትኛውንም ባርነት የመቃወሚያ ሰአቱ አሁን ነው። ገደቦች የሚፈርሱት ወደፊት አንድ ቀን ሳይሆን አሁን ነው።
➢ብዙ ጊዜ ያለ ጭካኔ የምንፀልየው ፀሎት ለውጥ የለውም። አንዳንድ እምነት የጎደላቸውና ከልብ ያልሆኑ ፀሎቶች ምንም ለውጥ አያመጡም። እስራኤላውያን አምርረው ወደ አምላካቸው የፀለዩት ፀሎት የ4 ትውልድ ቀንበር ነበር የሰበረው። አንዳንድ ጩኸቶች ታሪክ የመገልበጥ ኃይል አላቸው።
ጩኸታቸው በሚሊየን የሚቆጠር ሕዝብ ከግብፅ ባርነት በተዓምር እንዲወጣ መነሻ ምክንያት ሆነ።
➢በተመሳሳይ ድህነትን፣እርግማንን፣ ጭንገፋን፣ባርነትን፣የበታችነትንና ውርደትን የምናስቆመው የፀለየንና የጮህን ቀን ነው።
እስራኤላውያን ለአራት ትውልድ ያክል ምንም ጩኸት አላሰሙም።ድምፃቸውን አጥፍተው እግዚአብሔር እንደሌለው ሕዝብ ይደክሙ ነበር።
➢ እግዚአብሔር ወደ ኤርምያስ መጥቶ የተናገረው ቃል እናንብብ:- እንዲህ ይላል
ወደ እኔ ጩኽ፥ እኔም እመልስልሃለሁ፤ አንተም የማታውቀውን ታላቅና ኃይለኛ ነገርን አሳይሃለሁ። ኤር 33:3
➢በዙርያችን ያሉ አሉታዊ ነገሮችን፣አብ ያልተከላቸውን ነገሮች ለመነቃቀል፣ለውጥና እድገትን የሚይዙ ማንኛውም አይነት ተቀናቃኞችን የምንቃወምበት ሰአቱ ነገ ሳይሆን አሁን ነው። ድህነት፣እርግማን፣ እጦት፣ችግር፣ በሽታ፣መከራ መካንነት፣ፍሬቢስነት፣ጭንገፋ ሁሉ ታሪክ የሚሆኑበት ጊዜ አሁን ነው።
➢ ሰማይ ጣልቃ እንዲገባ የምትፈልጉት ጉዳይ አለ? ተደላድላቹ፣ ተላምዳችሁ ፣ችግር የለውም ብላቹ ተስማምታችሁ ከተቀመጣቹበት መንደር ለመውጣት ቆራጥ ጩኸት ጩሁ። አለበለዚያ ሁሉም ባለበት ያለ ለውጥ ይቆያል። ዘመኑ የጌታ ልጆች የሚያብረቀርቁበት፣ ፍጥረት የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ የሚናፍቅበት ዘመን ነው። ስለዚህ ከራስ አልፎ ለሌሎች በረከት ለመሆን
ከራስ አልፎ ለሌሎች መፈታት ምክንያት ለመሆን ከልብ ወደ ጌታ መጮህ አማራጭ የለውም።
✍መሳይ አለማየሁ (ነቢይ)
ክፍል 64 ይቀጥላል

ክፍል 64
ፀሎትን መረዳት
በዚያን ጊዜ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ ቀርበው፦ “እኛና ፈሪሳውያን፥ ብዙ ጊዜ የምንጦመው፥ ደቀ መዛሙርትህ ግን የማይጦሙት ስለ ምንድር ነው?” አሉት።
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦“ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉን?
ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት
ወራት ይመጣል፥ በዚያ ጊዜም ይጦማሉ።
(ዮሐ 9:14-15)
➢የጌታ ደቀመዛሙርት ከክርስቶስ ጋር በምድር ላይ ሳሉ አብረው ይበላሉ፣ ይጠጣሉ፣ ያወራሉ፣ ይወያያሉ፣ለአገልግሎት ከተሞችን ይዞራሉ፣ አብረው ይውላሉ፣ ያድራሉ። ይህ ቁርኝት በወቅቱ ከፀሎት ይበልጥ ነበር። ምክንያቱም ፀሎት ጠለቅ ያለ የልብ ትስስር deep inside Intimacy እንጂ ማነብነብ አይደለም።
የጌታ ደቀመዛሙርት ስጋ ለብሶ ከመጣው አምላክ ጋር የነበራቸውን ግንኙነት አስቡት! ኢየሱስን በየእለቱ እያዩት፣እየዳሰሱት ከመዋል የበለጠ ምን አይነት ፆም ፀሎት አለ?
➢ለዮሐንስ ደቀመዛሙርት እና ለፈሪሳዊያን ፆም ምግብ የመብላትና ያለመብላት ጉዳይ ነበር። ይሀ ሀይማኖታዊ አስተሳሰብ እንጂ መንፈሳዊነት አይደለም።ለዚህ ነው የዮሐንስ ደቀመዛሙርት ግራ ተጋብተው እኛ የዮሐንስ ደቀመዛሙርት ብዙ ጊዜ እንፆማለን፣ ፈሪሳውያንም ይፆማሉ ያንተ ደቀመዛሙርት ግን አይፆሙም፤ ምንድነው ምክንያቱ ብለው ጠየቁ። ጌታችን ኢየሱስ አንዲህ አላቸው
“ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉን? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል፥ በዚያ ጊዜም ይጦማሉ። (ዮሐ 9:14-15)
➢የፆም ፀሎት ዓላማው ከጌታ ጋር ህብረት ማድረግ ነው። ይህን በጥልቀት ያልተረዱት የዮሐንስ ደቀመዛሙርት ሙሽራው ኢየሱስ አጠገባቸው ሆኖ እሱን ፍለጋ ይፆሙ ነበር። እነዚህ ደቀመዛሙርት ኢየሱስ የቅርብ ሩቅ ሆኖባቸው ነበር።ስለ ፆም ያላቸው መገለጥ ሳይሆን ሀይማኖታዊ እውቀት ብቻ ነበር።
እነዚህ ደቀመዛሙርት ይፆማሉ ግን በፆም የሚፈለገው አምላክ አጠገባቸው ሆኖ አላወቁትም ነበር።አምላክ አጠገባቸው ሆኖ ስለ ፆም ውስጣቸው ያለውን ክርክር ይጠይቃሉ።
በፆምና በፀሎት የሚፈለገው አምላክ አጠገባቸው ቆሞ አላወቁትም።ቢያውቁት ኖሮ ስለ ሀይማኖት እሴት ከመጠየቅ ይልቅ ይሰግዱለት ነበር፣ልባቸውን ያፈሱለት ነበር።
➢ፆምና ፀሎት ለሀይማኖተኛ ሰው ወግና ልማድ ነው። ለገባው ግን ከእግዚአብሔር ጋር የሚደረግ የልብ ትስስርና ግነኙነት ነው። መንፈሱ መንፈሳችንን የሚያረሰርበት፣ ፀሎት በአምላካችን ህልውና የምንሞላበት፣ፈቃዱን የምንረዳበት እግዚአብሔር ሰራሽ ድልድይ ነው።
➢ፀሎት ኃይለኛ መሳርያ ነው። ፀሎት መንቀያም መትከያም መሳርያ ነው። ፀሎት ዛሬም አስተማማኝነቱ 100% የተረጋገጠ መንፈሳዊ ኃይል ነው።በፀሎት የማይቻል ይቻላል።ፀሎት ምትክ የለውም።
➢ፀሎትን በመረዳት መፀልይ ውጤቱን ያረጋግጣል። ፀሎትን የምንፀልይበት መንፈሳዊ ሰፍራ አለ።እሱም የልጅነት ስፍራችንና ያለንበት ኪዳን ነው።ይህ ዘመን የብሉይ ዘመን አይደለም። ፀሎታችን በአዲሱ ኪዳን መቃኘት አለበት። በአዲሱ ኪዳን የተቃኘ ፀሎት ከስፍራ ሆኖ መፀልይ ነው።በአዲስኪዳን ፀሎት ልጅ ከአባቱ ጋር ያለው ግንኙነት ነው።በአዲስኪዳን ፀሎት ከፍቅር እንጂ ከቁጣ አይጀምርም።
➢ፀሎትን መረዳት እንደ ባርያ ሳይሆን በእግዚአብሔር እንደተመረጠ፣በክርስቶስ እንደፀደቀ፣እንደተቀደሰ፣መንፈስ እንደሚረዳው አማኝ በመፀለይ ይገለፃል።ትክክለኛና መልስ የሚያመጣ ፀሎት መሰረቱ የአዲስ ኪዳንን እውነታዎች መረዳት ነው።ይህን አለመረዳት በፀሎት የእግዚአብሔርን ፈቃድ ከመፈፀም ይልቅ በፀሎት ሰዎችን መግደል ያሰኛል።
ደቀ መዛሙርቱም ያዕቆብና ዮሐንስ አይተው፦ “ጌታ ሆይ፥ ኤልያስ ደግሞ እንዳደረገ እሳት ከሰማይ ወርዶ ያጥፋቸው እንል ዘንድ ትወዳለህን?” አሉት። ሉቃ9:54
➢ደቀመዛሙርቱ ከገጠማቸው መገፋት የተነሳ ተናደው እሳት ወርዶ እንዲያጠፋቸው ፈቃደቸው ነበር።ነገር ግን የጌታ ፈቃድ አልነበረም። ደቀመዛሙርቱ እንደ ኤሊያስ መሆን ያማራቸው የተቀበሉትን መንፈስ ስላልተረዱ ነበር።
➢ኤሊያስ በኃጢአተኞች ላይ ያለው ቁጣ ያልበረደውን አምላክ ጠርቶ እሳት በማወረድ ብዙዎችን አስበላ። ክርስቶስ ግን በኃጢአተኛ ላይ ሊመጣ ያለውን ቁጣ በራሱ ላይ በማድረግ ነፃ አወጣን። ይህ ነው የኢየሱስ መንፈስ።ይህ ነው በኢዲስ ኪዳን መሰረት ላይ ሆኖ መፀለይ።ይህ ነው ፀሎትን መረዳት።
✍ መሳይ አለማየሁ(ነቢይ)
ክፍል 65 ይቀጥላል

ክፍል 65
ለገንዘብ ባለጠግነት መዘጋጀት
በተነ፥ ለምስኪኖች ሰጠ፥ ጽድቁ ለዘላለም ይኖራል፡ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ እግዚአብሔር፥ ሁልጊዜ በነገር ሁሉ ብቃትን ሁሉ አግኝታችሁ፡ ለበጎ ሥራ ሁሉ ትበዙ ዘንድ፥ ጸጋን ሁሉ ሊያበዛላችሁ ይችላል። 2ቆሮ9:8
➢መጽሐፍ ቅዱሳችን ከ2,350 ጊዜ በላይ ስለ ሀብት፣ስለ ገንዘብና ስለ ብልጽግና ይናገራል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምድር ላይ ሳለ ካስተማራቸው ትምህርቶች ውስጥ 15% የሚሆነው ስለ ገንዘብ ነው። እንዲሁም ከተጠቀማቸው 39 ምሳሌያች ውስጥ 11 ጊዜ የጠቀሰው ከገንዘብ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ነው።ስለ ገንዘብ የጌታ ሐዋርያትም በሰፊው አስተምረዋል።
በአጠቃላይ ስለ ገንዘብ ህብትና ባለጠግነት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጠቀሱት ዋና ዋና ትምህርቶች መካከል:-
-እንዴት ገንዘብ መስራት እንዳለብን፣
-በገንዘባችን ቸሮች መሆን እንዳለብን፣
-ስለ ገንዘብ መዝራት እና ማጨድ ህግጋት፣
-ገንዘብን በአግባቡ ማስተዳደር እንዳለብን፣
-ገንዘብ ወዳድ መሆን እንደሌለብን፣
-በገንዘባችን እግዚአብሔርን ማክበር እንዳለብን፣
-በገንዘባችን የወንጌልን ስራ መስራት እንዳለብን ያስተምራል።
➢እንደ አማኝ ስለ ገንዘብ መንፈሳዊ እውቀትን መቅሰምና መርሆችን መከተል የገንዘብ ባለጠግነትን ያረጋግጣል።
➢ለአንዳንዶች ስለ ገንዘብ ማስተማርም መማርም የብልፅግና ወንጌል ስለሆነ መስማት አይፈልጉም።ስለዚህ ድህነትን ታቅፈው ይኖራሉ። አንደ አገልጋይ መፅሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ሁሉ የመናገር ያስተማረውን ሁሉ የማስተማር ኃላፊነት አለብን።ምክንያቱም እግዚአብሔር ስለ ልጆቹ የገንዘብ ሀብትና ባለጠግነት ግድ የማይሰጠው አምላክ አይደለም።
➢የግድ በገንዘብ መባረክ አስፈላጊ የሆነበት ምክንያቶች
1ኛ መልካም ስራዎችን ለመስራት በገንዘብ መባረክ የግድ ነው።
2ኛ የወንጌልን ስራ ለመስራት በገንዘብ መባረክ የግድ ነው።
3ኛ ሰጪ ለመሆን በገንዘብ መባረክ የግድ ነው። (2ቆሮ 9:8)
4ኛ እራስን ለመቻል መባረክ የግድ ነው። (2ተሰሎንቄ 3:10)
➢የእግዚአብሔር ቃል የገንዘብ ሀብትና ባለጠግነት ዋነኛ ምንጭ ነው።የቃሉን መርሆችን መከተል የመባረኪያ መንገድ ነው።
ለገንዘብ በረከት ለመዘጋጀት የሚያስፈልጉ እውነታዎች :-
1ኛ ድህነት የእግዚአብሔር ፈቃድ እንዳልሆነ መረዳት
➢በየትኛውም የመጽሐፍ ቅዱስ መሰረት ድህነት የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖ አያቅም። ድህነት ያሸማቅቃል፣የበታች ያደርጋል ፣ድህነት የሰውን እጅ ፈላጊ ያደርጋል፣ ድህነት እጅግ አስከፊ ነው።ድህነት ተቀባይ እንጂ ሰጪ አያደርግም።ለዚህ ነው መፅሐፍ ቅዱሳችን ላይ ያሉ አባቶች በሙሉ እግዚአብሔር እንዲባርካቸው አጥብቀው ይፀልዩ የነበረው።
2ኛ የእግዚአብሔር መንግስት ተኮር መሆን
እግዚአብሔር ልጆቹን ለመባረክ ፈቃደኛ ነው። ነገር ግን ልጆቹ ባለራዕዮችና ታታሪዎች ይሆኑ ዘንድ ይፈልጋል።ለእግዚአብሔር መንግስት ምን ለመስራት እያሰብን ነው? መንግሰቱን ለመስራት ምንም አይነት ራዕይም ሀሳብም ከሌለን እግዚአብሔር ለምን ብሎ ይባርካል?!
የእግዚአብሔር የገንዘብ ባርኮት ከመንግሰቱ ጥቅሞች ጋር የተያያዘ ነው። እግዚአብሔር የሚባርከው ለዓላማ እንጂ ለጨዋታ አይደለም ።የእግዚአብሔር በረከት ዓላማ ተኮር ነው። ዓላማ ለሌለው ነገር የምንጠይቀው የገንዘብ ጥያቄ ከሰማይ መልስ የለውም።እንደ አማኝ የበረከታችን ምስጢር ስለ እግዚአብሔር መንግስት ያለን አመለካከት (kingdom mentality) ነው።
3ኛ በገንዘብ ንቃተ ህሊና ማደግ
➢እንደ አማኝ የገንዘብ ንቃተ ህሊናችን ከፍ ሊል ይገባል።የገንዘብ ንቃተ ህሊና ስለ ገንዘብ ያለን የበሰለ አመለካከት ነው። ለአንዳንዶች ገንዘብ ሁሉ ነገር ነው። ገንዘብ ካለ ሁሉም አለ ብለው የሚያምኑ ጥቂቶች አይደሉም። ሆኖም ግን ገንዘብ መጠቀሚያ ብቻ ነው።ገንዘብ መገልገያ ነው። ገንዘብ የሁሉ ነገር መሰረት አይደለም።በገንዘብ ሁሉንም ማድረግ አንችልም።ይህ አመለካከት የገንዘብ ፍቅር የወለደው አመለካከት ነው። ለገንዘብ በረከት ጤናማ አስተሳሰብ አስፈላጊ ነው። በገንዘብ ፍቅር የተነደፈ ልብ ከእግዚአብሔር መንገድ ይወጣል።
4ኛ በገንዘብ ፍቅር ላለመውደቅ መጠንቀቅ
የገንዘብ ፍቅር የሀጢአት ሁሉ ስር ነው። ገንዘብ መውደድ ከእምነት ያጎድላል። የገንዘብ ፍቅር ያስታል።የገንዘብ ፍቅር መንፈሳዊ አይኖችን ያሳውራል።
ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና፥ አንዳንዶች ይህን ሲመኙ፥ ከሃይማኖት ተሳስተው በብዙ ሥቃይ ራሳቸውን ወጉ። 1ጢሞ6:10
✍ መሳይ አለማየሁ(ነቢይ)
ክፍል 66 ይቀጥላል

ክፍል 66
የገንዘብ ህግጋት
➢እንደ አማኝ ስለ ገንዘብ ያለን ጤናማ አመለካከት በገንዘብ በረከቶች ለመባረክ አንዱ መስፈርት ነው። ገንዘብ መፅሐፍ ቅዱሳዊ ህግጋት አሉት።የገንዘብ ህግጋት ሲባል ስለ ገንዘብ የተቀመጠ መርህ፣ አካሄድ፣ መስፈርት እና መሟላት ያለባቸውን ነገሮች ያሳያል።
በዚህ ክፍል ከነዚህ ህግጋት መካከል ጥቂቶቹን ብቻ እናያለን።
1ኛ ጤናማ የገንዘብ አስተሳሰብ :-
ጤናማ የገንዘብ አስተሳሰብ ለገንዘብ በረከት የሚያስፈልግ ዋነኛው መስፈርት ነው። የተሳሳተ የገንዘብ አስተሳሰብ ውስጥ ያሉ ሰዎች በእግዚአብሔር የመባረኪያ ሰአታቸው ገና ነው። ገንዘብ ባገኝ ሁሉን ማድረግ እችላለሁ ብሎ የሚያምን ሰው አስተሳሰቡ እስኪቀየር ድረስ በረከት ደጅ ይጠብቀዋል።
እንደ አማኝ ለገንዘብ ያለን አመለካከት ከአለማዊያን የተለየ መሆን አለበት።አለማዊ አስተሳሰብ ''ገንዘብ የሁሉ ነገር ማዕከል ነው ይላል'' (Money is the central point of everything ) በዚህ አመለካከት የሚመሩ ጥቂቶች አይደሉም። ስለ ገንዘብ ጤናማ አመለካከት የሌለው አማኝ ገንዘብ መጥፍያው ሊሆን ይችላል።
2ኛ የአንደበትን ኃይል መረዳት
ሁለተኛው የገንዘብ ህግ የአንደበትን ኃይል መረዳት ነው።
በአንደበታችን አረም መትከልም ሆነ መንቀል እንችላለን። አንደበታችን ኃይለኛ መሳርያ ነው። አንደበት ድህነትንም፣በረከትንም የመሳብ አቅም አለው።ይህ ጉዳይ አንዳንዶች እንደሚያስቡት የአነቃቂ ንግግር ውጤት ሳይሆን የአንደበት ህግ ውጤት ነው።አንደበት መስመር ካልተበጀለት የሰውን ህይወት ቁልቁል ይዞ ይወርዳል።
ቃሉ እንደሚናገር ሰው በልቡ ሞልቶ የፈሰሰውን በአፉ ይናገራል። ስለዚህ አንደበታችሁ ህይወታችሁን እንዲያጨልም አትፍቀዱ። በአንደበታችሁ ስለ ገንዘብ ቀውሶች አታናፍሱ ፣እግዚአብሔር በማይመቹ ሁኔታወች ውስጥ እንኳ ሊባርካች ሁ እንደሚችል በእምነት አውጁ።
ያላመኑ ሰዎች ኢትዮጵያ መኖር ከባድ ነው ሲሉ እናንተም ተባብራቹ አዎን፣ በጣም ከባድ ነው አትበሉ። በአሁን ሰአት ብዙዎች በሀገራቸው ተስፋ ቆርጠዋል።አሁን የሚታየው የኑሮ ውድነት ፣የሰላም እጦት፣ የፓለቲካ አለመረጋ ጋት በገንዘብ ለመባረክ ከባድ ነው ብለው የሚያስቡ ጥቂቶች አይደሉም። ስለዚህ ወደሌላ ሀገር ተሰዶ በመኖር መባረክ እንደሚቻል ያስባሉ። ነገር ግን እራስን አንድ ጥያቄ መጠየቅ መልካም ነው።
የሚባርከው እግዚአብሔር ከሆነ እግዚአብሔር ምቹ ቦታ እየፈለገ ነው የሚባርከው??
ይሰሀቅ ድርቅ ምድሪቱን ባጠቃ ሰአት ዘርን ዘራ በዚያውም አመት መቶ እጥፍ አጨደ ይላል ቃሉ። ከገንዘብ በረከታችን ጀርባ እግዚአብሔር ካለ በየትኛውም ቦታ፣ በየትኛውም ጊዜ፣ በማንኛው ም አይነት ሁኔታ ውስጥ እግዚአብሔር ሊባርካችሁና ሊባርከን ይችላል። ይህ እምነት ካላቹ በአንደበታችሁ ህይወትን ተናገሩ፣ አንደበታችሁ በበረከት ተደላድላችሁ እንትኖሩ ያደርጋችኋል።ሞትም ህይወትም ያለው በአንደበታችን ላይ ነው።
አንደበታችን ወይ ሞትን ወይም ደግሞ ህይወትን የምንጠራበት መሳርያ ነው። በአንደበታችን እጦትን፣ ጭንገፋን፣ውድቀትን፣ ኪሳራን፣ አለመከናወንን መጥራት የለብንም። በፋይናንስ ለመባረክ እየፈለግን አንደበታችንን የማንገራ ከሆነ የገንዘብ መትረፍረፍን መለማመድ ይከብዳል።
3ኛ ምስጋና
እግዚአብሔርን ስላለን ነገር ማመሰግን ስላደረገው ነገር እውቅና መስጠት ነው። ምስጋና ታላቅ የገንዝብ ጥርመሳን ወደ ህይወታችን የሚያመጣ የህይወት ልምምድ ነው።እግዚአብሔርን ማመስገን ታላላቅ ደጆች ይከፍታል። እግዚአብሔርን ስላለን ስለ ጥቂቱ ስናመሰግን በረከት ወደ ቤታችን ተትረፍርፎ ይመጣል።ማመስገን ወዳልታሰበ የበረከት ህይወት ይመራል።
4ኛ ስራ:-
የገንዘብ በረከት ከሚስቡ ህግጋት መካከል ስራ አንዱ ነው። ስራ መስራት ምርታማነትን ያረጋግጣል።
-በእምነት ታላቁ አባታችን አብርሃም ገበሬ ነበር
-ይስሀቅም ገበሬ ነበር፣
-ጳውሎስ ድንኳን ይሰፋ ነበር።
ስራ አቋራጭ የሌለው የበረከት መንገድ ነው።
ደግሞ ከእናንተ ጋር ሳለን፦ “ሊሠራ የማይወድ አይብላ፡” ብለን አዘናችሁ ነበርና።
2ኛ ተሰሎንቄ2: 10:
5ኛ በገንዘብ ላይ ጌታ መሆን
ገንዘብ እኛን መግዛት የጀመረ ቀን ባርያ መሆን እንጀምራለን። የጊያዝን ህይወት ስናይ
ግያዝ የነቢዩ የኤልሳ ተተኪ መሆን የሚችልበት እድል ከፊቱ እያለ በገንዘብ ፍቅር ተነድፎ ከፍፃሜው የጎደለ ሰው ነበር። ግያዝ ገፀበረከቱን ተመኝቶ ንዕማንን ተከትሎ የሄደ እለት ከታላቅ ፍፃሜ እራሱን ያጎደለ አሳዛኝ ሰው ነው።( 2ነገ 5:20)
ወደ በረከት እየሄደ ያለ አማኝ እለት እለት መፀለይ ካለበት ፀሎት መካከል ገንዘብ ልቤን ከእግዚአብሔር መንገድ እንዳያወጣው ብሎ መሆን አለበት።
አምላኬም እንደ ባለ ጠግነቱ መጠን በክብር በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይሞላባችኋል። ፊልጵስዩስ 4:19
✍ መሳይ አለማየሁ(ነቢይ)
ክፍል 67 ይቀጥላል

በክርስቶስ IN CHIRST
ክፍል 67
የላይኛው ጥበብ
ጥበብን ማግኘት ምንኛ ከወርቅ ይሻላል! ማስተዋልንም ማግኘት ከብር ይልቅ የሚመረ ጥ ነው። ምሳ 16:16
ጥበብ የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ 227 ጊዜ ተጠቅሷል። 99 ጊዜ የተጠቀሰው በምሳሌ መጽሐፍ ውስጥ ሲሆን፣በአጠቃላይ መጽሐፍ ቅዱስ 4 አይነት ጥበብ እንዳለ ይገልፃል። እነሱም :-
1ኛ የምድር ጥበብ- earthly wisdom
2ኛ የአዕምሮ ጥበብ-intellectual wisdom
3ኛ ሰይጣናዊ ጥበብና-devilish wisdom
4ኛ ከሰማይ የሆነ ጥበብ ነው።the wisdom from above
➢በዚህ ክፍል ከሰማይ ስለሆነው ጥበብ በአጭሩ እንመለከታለን።
እንደ መጽሐፍ ቅዱስ እይታ ጥበብ ማለት ህይወትን ከመንፈሳዊ ህይወት አንፃር የማየት ብቃት እና መንፈሳዊ እውቀትን በተግባር የማዋል ብቃት ነው። በእያንዳንዱ የህይወት አቅጣጫ ውስጥ የበሰለ፣እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ውሳኔ መወሰን የጥበበኛ ሰው መገለጫ ነው።ጥበብ እጅግ አስፈላጊ የሆነበ ት ዋነኛው ምክንያት እግዚአብሔርን ደስ እያሰኘን እንደ ፈቃዱ ለመኖር ነው።
መጽሐፍ ሲናገር :--
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ሰነፎች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ።
ምሳ 1:7
➢የላይኛው ጥበብ እግዚአብሔርን ከመፍራት ይጀምራል።የላይኛው ጥበብ በአስተሳሰብ በንግግር እና በአኗኗር የሚገለፅ ነው።
ላይኛይቱ ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽሕት ናት፥ በኋላም ታራቂ፥ ገር፥ እሺ ባይ ምሕረትና በጎ ፍሬ የሞላባት፥ ጥርጥርና ግብዝነት የሌለባት ናት። ያዕ 3:17
➢እንደ አማኝ ሕዝቦች በምድር ሳለን በሚገጥሙን ተግዳሮቶች፣በጀመርናቸው ቢዝነሶች፣በትዳር ህይወት፣በልጆች አስተዳደግ፣ከአስቸጋሪ ሰዎች ጋር ባለን መስተጋብር ሁሉ ጥበብ ብልጫ አላት!
➢የሰማይ ጥበብ ከብዙ የምድር እንቅፋት፣ ከብዙ መጠላለፍ እና አላስፈላጊ ዋጋ መክፈል ይታደጋል።የሰማይ ጥበብ ሊመጡ ካሉ ስጋቶች፣ፍርሀቶች ነፍስን በመምራት እረፍት ይሆናል።የሰማይ ጥበብ አዕምሮን ብሩህ ያደርጋል፤ጨለማን ይገፋል።ጥበብ በነገሰችበ ት አማኝ ህይወት ውስጥ አላዊቂነት ስፍራ የለውም።በጥበብ የተሞላ አማኝ በዘመነኛው ቋንቋ አይሸወድም።አይበላም።
➢የእግዚአብሔር ጥበብ የሚፈልጓትን ከፍ ከፍ ታደርጋለች፣ታገናለች ፣አሸናፊ ታደርጋለች። የሰማይን ጥበብ ይዞ በምድር ጥበብ መሸነፍ አይታሰብም።የላይኛው ጥበብ የአጋንንትን እና የስጋን ጥበብ ከንቱ ያደርጋል።የላይኛው ጥበብ የትኛውም አይነት የሰው አመክንዮ (LOGIC) የመርታት እና አዕምሮን ሁሉ ለእግዚአብሔር የማስገዛት ኃይል አለው።
=ሐዋርያው ጳውሎስ በዘመኑ የነበሩትን የግሪክ ፈላስፎች የረታው በዚህ በላይኛው ጥበብ ነው።
=እስጢፋኖስ የፊቱ መልክ እስኪቀየር ድረስ ክርስቶስን በአይሁድ ፊት ሆኖ የገለጠው በዚህ ጥበብ ነው። (ሐዋ 6:10)
ጥበብን እንፈልጋት!
ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፥ ለእርሱም ይሰጠዋል። ያዕቆብ 1:5
ጥበብ ስንፈልጋት ትገኛለች፣ስንጠራት አቤት ትላለች ፣ስናከብራት ታከብራለች!
ጥበብን የሚያገኝ ሰው ምስጉን ነው፥
ማስተዋልንም ገንዘቡ የሚያደርግ፤በወርቅና
በብር ከመነገድ ይልቅ በእርስዋ መነገድ
ይሻላልና። ከቀይ ዕንቍም ትከብራለች፥
የተከበረም ነገር ሁሉ አይተካከላትም።
ምሳ 3:13-15
✍ መሳይ አለማየሁ(ነቢይ)
ክፍል 68 ይቀጥላል

ኢየሱስ ስትበራልን ተስፋችን ለመለመ ፤መኖርን አስወደድከን ፤ከህይወትህ አካፍለህ እልፍና ጥልቅ ደስታ ውሰጥ ከተትከን።
ኢየሱስ ብርሃናችን ነህ !
“ደግሞም ኢየሱስ፦ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም ብሎ ተናገራቸው።”
— ዮሐንስ 8፥12
ኢየሱስ ብርሃናችን ነህ !
“ደግሞም ኢየሱስ፦ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም ብሎ ተናገራቸው።”
— ዮሐንስ 8፥12
በክርስቶስ IN CHRIST
ክፍል 69
የእግዚአብሔር መንግስት የኃይል እንጂ የንግግር ጉዳይ አይደለም !
የእግዚአብሔር መንግሥት በኃይል ነው እንጂ በቃል አይደለምና። 1ቆሮ 4:19
➢ክርስትና የሀይል ውጤት ነው።የክርስትና መሰረት የክርስቶስ ሞትና ትንሳዔ ነው። ትንሳኤ የክርስትና የኃይል ምንጭ ነው። የኃይሉ ታላቅነትና ባለጠግነት የተገለጠው በክርስቶስ ትንሳኤ ነው። እግዚአብሔር ሰዎች ን ከህግና ከሐጢአት ጭቆና ነፃ ሊያወጣ ታላቅ የሆነ የማዳን ኃይሉን የገለጠው በክር ስቶስ ትንሳኤ ነው። ክርስትና ሀይማኖት አይደለም።ምከንያቱ ሀይማኖት የሰው ልጅ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነትና ጽድቅን ለማግኘት የሚለፋው ልፋትና ከንቱ ጥረት ነው።
➢ክርስትና በእግዚአብሔር ኃይል ታጥቀን የምንኖረው ህይወት ነው። ክርስትናን በግል ጥረታችን መኖር አንችልም። ያለ እግዚአብሔር ኃይል መፀለይ፣መቀደስ፣ለወንጌል መጨከን፣ እና እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አይቻልም።
ይህ ትምህርት ለብዙዎች ቀለል ያለ ትምህርት ይመስላቸዋል።ነገር ግን ይሄ ተግባራዊ ክርስትና ነው።በክርስቶስ የሚለው ይህ ተከታታይ ትምህርት ተግባር ተኮር ትምህርት እንጂ መላምትና ቅዠት አይደለም።
በኃይል ታጥቆ ክርስትናን በመኖር ደረጃ ስንቶቻችን ነን በዓለም ላይ ተፅዕኖ እየፈጠርን ያለነው?! መልሱን ለራሳችን።
➢የጌታ ደቀመዛሙርት የሶስት ዓመት የቲዎሎጂ ስልጠና ከወሰዱ በኋላ በመጨረሻ አንድ የቀራቸውና ሊቀበሉት የግድ የሆነው የእግዚአብሔር ኃይል ነበር።
➢ የእግዚአብሔር ኃይል ማለት እውቀት ወይም ልምድ ማለት አይደለም። ደቀመዛሙ ርቱ ምንም እንኳ የአገልግሎት ልምድና የመጽሐፍ እውቀት ቢኖራቸውም ይሄ ብቻውን ዓለም ላይ ወንጌል ለመስበክና ተፅዕኖ ለመፍጠር በቂ አልነበረም። የመጽሐፍ እውቀት መልካም ነው። ቃሉን አንባቢ መሆን ድንቅ ነው፣የፀሎት ሰው መሆንም እጅግ መልካም ነው፣ የቲዎሎጂ እውቀትም ጥሩ ነው። ይሄ ሁሉ ተፅዕኖ የሚያመጣው ግን ኃይል ስንታጠቅ ነው።
➢ኃይል መቀበል ማለት መለኮት በሰውነት ውስጥ ሲገለጥ ማለት ነው።የእግዚአብሔር ኃይል ሲባል ከተፈጥሯዊ አቅም በላይ የሚገለጥ ልዕለ ተፈጥሯዊ ኃይል ነው።
እግዚአብሔር ያለርሱ ኃይል እንድንኖረው ያዘዘን ህይወት የለም።
➢የእግዚአብሔርን ኃይል በህይወታችን ተረድቶ መኖር ክርስትናን ጣፋጭ ያደርገዋል።
ክርስትናን ከሌሎች ኃይማኖቶች የሚለየው ህያው ኃይል በመካከላችን መገለጡ ነው።
መንፈስ ቅዱስ የኃይላችን ምንጭ ነው። የመንፈስ ቅዱስ ኃይል አሸናፊ አማኞች የመሆናችን ዋስትና ነው።
➢የጌታን እያንዳንዱን የህይወቱን ጉዞ ስናነብ
ጌታ በመንፈስ ኃይል ተፀነሰ፣በመንፈስ ኃይል አደገ፣ በመንፈስ ኃይል ተጠመቀ፣በመንፈስ ተቀባ፣ በመንፈስ ኃይል ተዓምራትን ይሰራ ነበር፣በመንፈስ ኃይል አጋንንት ያስወጣ ነበር፣ በመንፈስ ኃይል ወደ ሰማይ አረገ።ጌታ ሁሉን ም ያደረገው በእግዚአብሔር ኃይል ነበር።
➢እንደ አማኝ ኢየሱስን የግል አዳኛችን አድርገን ስንቀበል የእግዚአብሔር ልጆች የመሆን ታላቁን ስልጣን ተቀብለናል። ይህ አይዶሎጂ አይደለም። የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችን የመጨረሻው የኃይል ስልጣን ባለቤት የመሆናችን ማረጋገጫ ነው። ከእግዚአብሔር ልጅነት የሚበልጥ ስልጣን የለም። ይህ እውነት በኑሮ እውን ይሆን ዘንድ ቃሉን ማሰላሰልና በመንፈስ ኃይል መታጠቅ አስፈላጊ ነው።
➢ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆናችሁ አጋንንታዊ ኃይል አይቋቋማችሁም። የእግዚአብሔር ልጆች ከሆናችሁ በሽታ በእናንተ ላይ ስልጣን የለውም። የእግዚአብሔር ልጆች ከሆናችሁ ውድቀት ኪሳራ ፣ጭንገፋ በእናንተ ላይ ኃይል የለውም።
➢ እንደ አማኝ በዚህ ንቃተ ህሊና መመላለስ ኃይልን በህይወታችን እውን ያደርጋል። የእግዚአብሔር ኃይል ዛሬም ይሰራል፣ ይገለጣል።
➢በዚህ ዘመን ያለውን ዓለማዊ ፣አጋንንታዊና ሰዋዊ ፈተናዎች ሁሉ የምናሸንፈው በእግዚአብ ሔር ኃይል ነው።ሐዋርያው ዮሐንስ ይህን እውነት ያረጋግጥልናል።
ልጆች ሆይ፥ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ አሸንፋችኋቸውማል፥ በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ታላቅ ነውና። 1ዮሐ 4:4
➢የጳውሎስም የዘወትር ምጡ አማኞች፣ የእግዚአብሔርን የኃይሉን ታላቅነት እንዲረዱ ነበር።የኃይሉን ምሰጢር የተረዳ አማኝ በዚህ የምድር ቆይታው ኃይሉን እየገለጠ ይኖራል። ለኃይሉ ያለን መረዳት አጠቃላይ የህይወት ምልልሳችንን ውብ ያደርጋል፤እግዚአብሔር የሰጠንን የምድር ተልዕኮ በብቃት እንድንወጣ ያስችለናል።
ጳውሎስ ይህን እውነታ ያስረዳል:-
እምነታችሁም በእግዚአብሔር ኃይል እንጂ በሰው ጥበብ እንዳይሆን፥ ቃሌም ስብከቴም መንፈስንና ኃይልን በመግለጥ ነበረ እንጂ፥ በሚያባብል በጥበብ ቃል አልነበረም።
1ቆሮ 2:4-5
✍ መሳይ አለማየሁ(ነቢይ)
ክፍል 70 ይቀጥላል

ክፍል 70
የኢየሱስ ልዕልና
እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥ በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ። ፊል2:9
➢ጌታ ኢየሱስ ሰውን ለማዳን ክብሩን ትቶ በሰው መልክ (ሰው ሆኖ መምጣቱ) የመጨረ ሻው የዝቅታና የትህትና መገለጫ ነው። ኢየሱስ ፍፁም አምላክ ሆኖ ሳለ ስጋ ከመልበሱ የሚበልጥ ራስን ማዋረድ የለም።ኢየሱስ ልዕልናውን ተወ።ክብሩን፣ስልጣኑን፣ኃይሉንና ዘላለማዊ የመኖርያውን ስፍራ ትቶ የአዳምን ዘር ለማዳን የአዳምን ስጋ ለብሶ ወደ ምድር
ወረደ።ሊያድነው የመጣውን የሰው ዘር መልክ ለበሰ፣ስለውበታችን ሲል ደምግባቱን አጣ፣ ህይወትን ሊሰጠን ሞታችንን ሞተ፣ከመላዕክት ጥቂት አንሶ ተገኘ።ይህ ሁሉ ስለኛ የተከፈለ ታላቅ ዋጋ ነው።
➢የእግዚአብሔር ቃል ስናጠና ክርስቶስ ኢየሱስ ዓልፋና ኦሜጋ መጀመርያ መጨረሻ የሌለው ዘላለማዊ እንደሆነ ይናገራል። እንዲሁም ዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ አንድ ላይ እንደተጠቀሰው ፣ በመጀመርያ ቃል እንደነበርና ቃልም(ኢየሱስ) እግዚአብሔር እንደሆነ ያብራራል።
ኢየሱስ :--
-ዘላለማዊ የእግዚአብሔር ልጅ ነው፣
-የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው፣
-የፍጥረት ሁሉ በኩር ነው፣
-የማይታየው የእግዚአብሔር መልክ መገለጫ ነው፣
-የእግዚአብሔር ሙላት እና ተራኪ ነው።
-የፍጥረት ሁሉ ፈጣሪ ነው።
-ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ፦ አልፋና ዖሜጋ ነው።
እርሱም የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው። የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው። ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል። ቆላስይስ 1:15-16
በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና። ቆላስይስ 2:9
➢ስለ ኢየሱስ ስናስብ ማሰብ ያለብን ክብሩን ትቶ፣ራሱን ባዶ ያደረገበትን ጊዜ ብቻ መሆን የለበትም።ኢየሱስ እራሱን ባዶ ያደረገው እኛን በክብሩ ሊሞላንና ከአብ ጋር ሊያስታርቀን ነው። ይህ የሆነው ከ2ሺህ ዓመታት በፊት ነው። ሆኖም ግን የእርሱ የማዳን ስራ አንድ ጊዜ ለሁልጊዜ ስለሆነ ዛሬም ህያው ነው።
ኢየሱስ ለዘላለም ከብሯል!
አሁን ኢየሱስ ባዶ ወይም የባርያን መልክ ይዞ አይደለም ያለው፤ኢየሱስ ከምንም ዝቅ ብሎ አይደለም የሚገኘው።ኢየሱስ አሁን በፍጹም ልዕልናውና በክብሩ ነው የሚገኘው። ከእንግዲህ በኋላ ኢየሱስን በውርደትና በዝቅታ አናውቀውም። ተመልሶ የሚመጣውም የሰው ቋንቋ በማይብራራው ክብር ነው።
ክርስቶስንም በሥጋ እንደ ሆነ ያወቅነው ብንሆን እንኳ፥ አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ እንደዚህ አናውቀውም።2ቆሮ 5:16
> ሐዋርያው ዮሐንስ በይሁዳ ምድር ሲመላለሱ ያያቸውን የኢየሱስን እግሮች በመንፈስ ሲያይ እግሮቹ በእቶን የነጠረ የጋለ ናስ ይመስሉ ነበር፥
> ምድር ላይ ሳለ በስጋ ያያቸውን ዓይኖች በመንፈስ ሲያይ ደግሞ ዓይኖቹ እንደ እሳት ነበልባል ነበሩ፤ እንዲሁም ምድር ላይ ሳለ የሰማውን የጌታን ድምፅ በመንፈስ ሲሰማው ግን ድምፁ እንደ ብዙ ውኃዎች ድምፅ ነበረ።
ቃሉ እንዲህ ይላል:-
ራሱና የራሱ ጠጕርም እንደ ነጭ የበግ ጠጕር እንደ በረዶም ነጭ ነበሩ፥ ዓይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ነበሩ፤ እግሮቹም በእቶን የነጠረ የጋለ ናስ ይመስሉ ነበር፥ ድምፁም እንደ ብዙ ውኃዎች ድምፅ ነበረ። በቀኝ እጁም ሰባት ከዋክብት ነበሩት፥ ከአፉም በሁለት ወገን የተሳለ ስለታም ሰይፍ ወጣ፤ ፊቱም በኃይል እንደሚበራ እንደ ፀሐይ ነበረ። ራዕ 1:14-16
➢የኢየሱስ መልኩም፣ ድምፁም፣ፊቱም፣ እግሮቹም ልዕልናውም የተለየና በቃላት የማይገለፅ ነው። ኢየሱስ በንጉስ ኃይልና ስልጣን ተመልሶ ይመጣል። ያኔ ያዋረዱት በክብሩ ያዩታል፣ያኔ የናቁት አሁን ያከብሩታል። ያኔ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንክ ራስህን አድን እያሉ ያላገጡ ሁሉ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ይረዳሉ። ያኔ በምድር ሳለ በአጋንንት አለቃ አጋንንት ያወጣል ያሉት ሁሉ እያዩ አጋንንትንና ዲያብሎስን ሲቀጣ ያያሉ።
እነሆ፥ ከደመና ጋር ይመጣል፤ ዓይንም ሁሉ የወጉትም ያዩታል፥የምድርም ወገኖች ሁሉ ስለ እርሱ ዋይ ዋይ ይላሉ። አዎን፥ አሜን። ራዕ1:7
ኢየሱስ በክብር ይመለሳል !
✍ መሳይ አለማየሁ(ነቢይ)
ክፍል 71 ይቀጥላል

ክፍል 71
የእግዚአብሔር አብሮነት
ለሙሴ እንደ ነገርሁት የእግራችሁ ጫማ የሚረግጠውን ቦታ ሁሉ ለእናንተ ሰጥቼአለሁ። በሕይወትህ ዕድሜ ሁሉ ማንም አይቋቋምህ ም፤ ከሙሴ ጋር እንደ ሆንሁ እንዲሁ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ አልጥልህም፥ አልተውህም። ለአባቶቻቸው። እሰጣችኋለሁ ብዬ የማልሁላቸውን ምድር ለዚህ ሕዝብ ታወርሳለህና ጽና፥ አይዞህ።ነገር ግን ጽና፥ እጅግ በርታ፤ ባሪያዬ ሙሴ ያዘዘህን ሕግ ሁሉ ጠብቅ፥ አድርገውም፤ በምትሄድበትም ሁሉ እንዲከናወንልህ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል።የዚህ ሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፥ ነገር ግን የተጻፈበትን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ በቀንም በሌሊትም አስበው፤ የዚያን ጊዜም መንገድህ ይቀናልሃል ይከናወንልሃልም ።በምትሄድበት ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና ጽና፥ አይዞህ፤ አትፍራ፥ አትደንግጥ ብዬ አላዘዝሁህምን?
መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 1 : 7-9
➢በመግቢያ ጥቅሳችን እንዳነበብነው እግዚአብሔር ከሙሴ ሞት በኋላ ኢያሱን የእስራኤላውያን መሪ አድርጎና የሙሴ ተተኪ መሪ በማድረግ ለአገልግሎት ሲጠራው እንመለከታለን።ቀጥሎ የአገልግሎት ስብእና እንዲላበስና የእግዚአብሔር አብሮነት ከሱ ጋር መሆኑን እንዲረዳ ማበረታቻ ሲደርሰው እንመለከታለን።
➢በህይወታችሁ ማወቅ ካለባችሁ አንዱ እውነታ በክርስቶስ ከሆናችሁ የእግዚአብሔር አብሮነት ከእናንተ ጋር መሆኑን ነው። የክርስቶስ ከሆናችሁ ቀን ጀምሮ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው። ይህን በመረዳት መመላስ የእናንተ ድርሻ ነው።
በዙርያችሁ ምንም ነገር እያንዣበበ ሊሆን ይችላል፣ሁኔታዎች መልካቸውን ቀይረው ሊሆን ይችላል፤ግድ የለም ጌታ ከእናንተ ጋር ነውና አይናችሁን ወደሰማይ አንሱና የተናገራችሁን አስቡ።ስሙን ጥሩት። ቃሉን ለሁኔታችሁ ንገሩት። ለተፈጠረው ነገር እጅ አትስጡ። ቃሉን አስቡ።ፈጥኖ ደራሽ የሆነው ጌታ ነገራችሁን ሁሉ መልክ ያሲዘዋል።
➢እግዚአብሔር በተናገራችሁ ቃል እና ቃሉ በሚፈፀምበት ጊዜ መካከል ብዙ ነገሮች ግልፅ ባይሆኑላችሁም አንድ ነገር ግን ግልፅ ነው ከተናገረ ያደርገዋል።እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንዳለ ተረዱና በህይወት ጉዳዮቻችሁ ንገሱ፣ተከናወኑ።ክብርን ለእግዚአብሔር አምጡ።
➢እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ሲሆን
1ኛ ህይወታችሁ በብርታት ይሞላል።
2ኛ የምትሰሩት ሁሉ ይከናወናል።
3ኛ አላማው በእናንተ ይሳካል።
➢የእግዚአብሔር ለኢያሱ የተናገረውን 12 ዋና ዋና ትዕዛዛትና ማበረታቻዎች ለራሳችሁ አስቡት አሰላስሉት።
1ኛ ካንተ ጋር እሆናለሁ አልጥልህም፣
2ኛ ምድሪቱን ታወርሳለህ፣
3ኛ ጽና፣
4ኛ በርታ፣
5ኛ ህጉን ጠብቅ፣ አድርገው፣
6ኛ እንዲከናወንልህ ወደ ግራም ወደ ቀኝም አትበል፣
7ኛ ህጉ ከአፍህ አይለይ፣
8ኛ ህጉን በቀንም በሌሊትም አስበው፣
9ኛ አትፍራ ፣
10ኛ አይዞህ፣
11ኛ አትደንግጥ ፣
12ዐከሙሴ ጋር እንደሆንኩ ካንተ ጋር እሆናለሁ።
አሜን !!
ክፍል 72 ይቀጥላል
✍ በመሳይ አለማየሁ (ነቢይ)

Forwarded from ሜርሲ እና ብዕሯ✍
በሜርሲ እና ብዕሯ በሚዘጋጀው የመጀመሪያ ዙር online ስልጠና የሚካተቱት:-
#ልብወለድ ምንድነው እንዴትስ ይፃፋል?
#የፅሁፍ ሀሳቦች እንዴት በቀላሉ ማግኘት እንችላለን?
#መንፈሳዊ ልብወለዶች እንዴት ይፃፋል?
#film script ምንድነው እንዴትስ ይፃፋል?
#telgram channel ከፍተን አንባቢያንን እንዴት መያዝ እንችላለን?
#Life experience
#telgram ላይ የሚለቀቁ ልብወለዶች እንዴት ይፃፋሉ?
ስልጠናው እንዚህን እና ሌሎች ተጨማሪ course ችን የያዘ ሲሆን በስልጠናው መጨረሻ ጥሩ ተሳትፎ ያላቸው ልጆች ሜርሲ እና ብዕሯ በሚዘጋጀው Digital መፅሄት ላይ ተሳታፊ ይሆናሉ።ሰልጣኞች የእራሳቸውን ቻናል ከፍተው እንዲፅፉ አስፈላጊው ድጋፍ ሁሉ ይደረግላቸዋል። ምዝገባው ለአንድ ሳምንት ይቆያል።
ውስን ሰልጣኞችን ብቻ ስለሆነ የምንቀበለው ፈጥነው ይመዝገቡ።የዚህ ስልጠና ዋና ዓላማ ክርስቲያን ፀሃፊያንን ማበረታት እና ውስጣቸው ላይ ያለውን talent እንዲያወጡ ማድረግ ነው።
ስልጠናው ለሶስት ሳምንት የሚቆይ ሲሆን በሳምንት ለሶስት ቀን ይሰጣል።በሰዓቱ መገኘት ላልቻሉት record ተደርጎ ይለቀቃል።
ምዝገባው Normal:- 500 ብር
ለተማሪዎች :-45% discount አለን።
ለመመዝገብ @Mercyasta ላይ ያናግሩን።
ሰናይ ጊዜ❤️
@Mercy_ena_berua✍

"አስጨንቀን"
ፊል 1:23-26
ይሄ ክፍል አንዳች ልብ የሚያሞቅ ሀሳብ አለው። ከብዙዎቻችን በተለየ መልኩ ጳውሎስ አብዝቶ ይጨነቃል። የሚያስገርመው ታዲያ መጨነቁ ሳይሆን የጭንቀቱ ምክንያቶች ናቸው። አስቀድሞ ስለመሞት ያስባል። ይህም ከስጋው ሞት በኋላ ከክርስቶስ ጋር አብሮ መኖርን እየናፈቀ ነው። ግን ደግሞ ያገለግላቸው ወገኖቹን ሲያስብ ሌላ ጭንቀት ሰቅዞ ይይዘዋል። በስጋ ኖሮ እነርሱን የክርስቶስ ደቀመዝሙር በማድረግ ፍሬን ያገኝባቸው ዘንድ ይፈልጋል። ስለዚህም በህይወት እንደሚቆይ ተረድቷል።
ጳውሎስ እየደረሰበት ካለው መከራ ወደ ዘለአለም እረፍት በክርስቶስ እቅፍ መሆንን ቢመኝም ከዚህ ትይዩ የክርስቶስን ህዝብ ማገልገልና አካሉን ማነፅ ትልቁ ተልዕኮው እንደሆነ ገብቶታል።
ትልቁ ተልእኮአችን ወንጌልን መመስከር እና የመሰከርንላቸውን ደቀ መዝሙር ማድረግ ነው። ይህን የህይወታችን ማዕከል ማድረግ መቻል ከብዙ አላስፈላጊ ጭንቀት አሳርፎ ለመንግስቱ ያስሮጠናል።
እግዚአብሔር ህይወታችንን ለመንግስቱ ጉዳይ በመጨነቅ እየሞላ ለጉዳዩ ያስሩጠን። የጌታ ስራ ሀሳባችንን ከወሰደው በእርግጥም ለእርሱ መኖር አይከብደንም።

Forwarded from Kingdom of heaven (KHM)
1ኛ ቆሮንቶስ 16
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ ንቁ፥ በሃይማኖት ቁሙ፥ ጎልምሱ ጠንክሩ።
¹⁴ በእናንተ ዘንድ ሁሉ በፍቅር ይሁን።
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ ንቁ፥ በሃይማኖት ቁሙ፥ ጎልምሱ ጠንክሩ።
¹⁴ በእናንተ ዘንድ ሁሉ በፍቅር ይሁን።
በክርስቶስ IN CHRIST
ክፍል 72
የአንደበት ኃይል
የእግዚአብሔር ቃል ስለ አንደበት ኃይል ከ100 ጊዜ በላይ ይናገራል።
ቃሉ አንደበት ህይወትን ለማፍረስ ወይም ለመገንባት፣ጥበብን ለመናገር ወይም ስንፍናን ለማውራት፣ ለመባረክ ወይም ለመርገም ትልቅ መሳርያ መሆኑን ያስተምራል። በመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ መሰረት የአንደበት ቃል ኃይል አለው። ይህም ኃይል የህይወት እና የሞት ኃይል ነው።
➢በአንደበት ሞትንም ህይወትንም መጥራት እንችላለን። መዳናችን ሳይቀር የአንደበት አዋጅ ውጤት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር
''ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና።ሮሜ 10:10 '' ይላል።
👉ለመዳችን የኢየሱስን ጌትነት ማወጅ አስፈላጊ ከሆነ '''አዋጅ''' (መልካም የምላስ ቃል) ምን ያክል ትልቅ ሰፍራ እንዳለው ማሳያ ነው። በሌላ ክፍል ደግሞ እንዲህ ይላል።
ሞትና ሕይወት በምላስ እጅ ናቸው፤
የሚወድዱአትም ፍሬዋን ይበላሉ።ምሳ 18:21
➢የሞትና የህይወት አድራሻቸው ምላሳችን ላይ ነው። ሞት መቃብር ስፍራ ሳይሆን ያለው አንደበታችን ላይ ነው። ህይወትም በተመሳሳይ ። ሞትም ህይወትም ምርጫ ናቸው።ማለትም ሰው አንዲመርጣቸው የቀረቡ አማራጮች ናቸው። ሰው የመረጠውን ውጤት ይቀበላል። ከፈለገ በአንደበቱ እራሱን መራገም ይችላል። ከዛ ህይወቱን ወደማይወጣበት አዘቅት መክተት ይችላል።ከፈለገ መልካሙን የአንደበት ፍሬ መርጦ ህይወቱን ብሩህ ማድረግ ይችላል።
ሰው በልብ መልካም እየተመኘ በአንደበቱ ክፉ የሚናገር ከሆነ ምኞት ህልም ብቻ ሆኖ ይቀራል። ትላልልቅ ህልሞች የሚሞቱት ህልምን በሚገድሉ የራስ ንግግሮች ነው። አንደበት እንደ ትልቅ አውዳሚ የጦር መሳርያ ያወደመው ብዙ የሰው ህልሞች አሉ።
አንደበት የክፋት መሳርያ ሲሆን ተፅእኖው ከአጋንንት ሊበልጥ ይችላል።
➢ብዙ ሰዎች '' የምንናገረው ነገር ምንም አይነት ተፅዕኖ የለውም ብለው ስለሚያምኑ አንደበታቸውን መቆጣጠር አይፈልጉም። የአንዳንዶች ህይወት የተበላሸው በአጋንንት ሳይሆን በገዛ ምላሳቸው ነው።
ሁላችን በብዙ ነገር እንሰናከላለንና፤ በቃል የማይሰናከል ማንም ቢኖር እርሱ ሥጋውን ሁሉ ደግሞ ሊገታ የሚችል ፍጹም ሰው ነው።
ያዕ 3:2
➢ከእግዚአብሔር ቃል ጋር የተስማማ አዋጅና የአንደበት ቃል ህይወት ያስውባል፣ህይወት ያሸበረቀ እንዲሆን ያደርጋል፣ህይወትን ከክብር ወደ ክብር ይለውጣል፣ መንፈሳዊ አቅራቦቶቸን ማጣጣም ያስችላል።
➢አንድ ሰው ከአንደበቱ ስድብን፣እርግማንን ፣ከንቱ ነገሮችን፣ሀሜትን፣ውሸትን እያወጣ ህይወቱ እንዴት ጤናማ ሊሆን ይችላል?! ምክንያቱም እነዚህ ሁሉ የሞት ውጤቶች ናቸውና።ሰው በአንደበቱ እግዚአብሔርንም ዲያብሎስን መጥራት ይችላል።ምርጫው የሰውየው ነው። አንደበታችን የህይወት መፍለቂያ እንጂ የሞት ጉድጓድ መሆን የለበትም።ለአንደበታችን መስመር ማበጀትና አንደበትን መቆጣጠር ህይወትን ከብዙ ምስቅልቅል ያተርፋል። በእኛ ጋር ብሂል
'''በለፈለፉ በአፍ ይጠፉ''' ይባላል።
አንደበታችን የቆጥ የባጡን አንዲያወራ መፍቀድ የለብንም።አንደበታችን ተራ አለመሆኑን ተረድተን ክቡር የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ተረድተን፣እንደተመረጡ ትውልዶች ህይወትን በአንደበታችን ማወጅ አለብን።
ቃሉ አንደሚል ''ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ።' ኤፌ 4:29
በክርስቶስ አምኖ የዳነ ሰው አንደበት:--
1ኛ-የህይወት መፍለቂያ ነው።
2ኛ-የንጉስ ልጅ አንደበት ነው።
3ኛ-የባለሥልጣን አንደበት ነው።
4ኛ-ወንጌል የሚያውጅ አንደበት ነው።
5ኛ-አመንሁ ስለዚህ ተናገርኩ ተብሎ እንደተፃፈ የአማኝ አንደበት የእምነት መሳርያ ነው።
6ኛ-ሌሎችን የሚያንፅ መሳርያ ነው።
ሕይወትን የሚፈቅድ ሰው ማን ነው?
በጎንም ዘመን ለማየት የሚወድድ አንደበትህን ከክፉ ከልክል፥ከንፈሮችህም ሽንገላን እንዳይናገሩ። ( መዝ 34:12)
ክፍል 73 ይቀጥላል

HTML Embed Code: