TG Telegram Group Link
Channel: የኔ ማስታወሻ✍🏾በኪያብ🦋
Back to Bottom
ስላንተ ነው የማወራው ስላንተ ብጣሽ ሀሳብ ብጣሽ ልብ የለኝም
የነበረኝ ፍቅር ረቂቅ መሆኑ አሁን ድረስ ያስገርመኛል

ባይገርም ቆፍጣና ሆኛለው ማለቴ ልበ ደንዳና ጀግንነት አይደለም አውቃለው ግን መልካም ነው ይመቻል

ኪያብ
..................................
ከረጅም አመት ቡኋላ እመጣለው…የዛኔም ግን እንደድሮ ሆኜ አደለም…አንቺ ማነሸ?…የት ነበርሽ?…ትለኝ ይሆናል…እኔም አንገቴን ደፍቼ እምልህ ነገር ቢኖር…"እያለሁ መች ነበርክ? ነው ስኖርልክ መቼ ኖርክልኝ ነው መልሴ
...........................🍂

ኪያብ🔉


አብርሃም ፍቅሬ
የቅዳስ ልጅ
🌿#አንጀት_አርስ_እውነታ!

ከ150 አመት በኋላ ዛሬ በህይወት ካለነው ሰዎች አንዳንችም በህይወት አንገኝም፡፡ዛሬ ላይ ከምንታገልላቸው ነገሮች 70 በመቶ የሚሆኑት ከ150 አመት በኋላ አንዳቸውም ለምልክት እንኳ አይገኙም፡፡ፈጽመው ይጠፋሉ ይረሳሉ፡፡

እስኪ ወደ ኋላ 150 አመት እንሂድ፡፡ወቅቱ 1872 ገደማ ነው የሚሆነው፡፡ያኔ የሰው ልጅ እንደ እቃ በአደባባይ ተደርድሮ የሚሸጥበት ወቅት ነበር፡፡በወቅቱ ብርቅ የነበረውን የፊት መስታወት ለማግኘት ሲሉ የገዛ ዘመዶቻቸውን የሸጡ ሰዎች ዛሬ የታሉ? መስታወትንስ ዛሬ ላይ እንደ ሀብት የሚያስበው ማን ነው? ማንም፡፡ጨው ወይም ጌጥ ወይም ሌላ ነገር ለማግኘት ሲሉ የተሻሻጡ ብዙ ሰዎች ነበሩ፡፡ዛሬ ላይ እነዚያ ሰዎች የሞቱላቸው የገደሉላቸው የተካካዱባቸው የተሻሻጡላቸው አብዛኞቹ ነገሮች ይህ ነው የሚባል የረባ ዋጋ ያላቸው አይደሉም፡፡በጊዜው ግን ለሰው ልጅ የሞትና የህይወት ልዩነት ነበሩ፡፡የሰው ልጅ በየጊዜው የሚታገልላቸው አብዛኞቹ ነገሮች ዛሬ ላይ ዞር ተብለው ሲታዩ በጣም የሚያስቁ ናቸው፡፡

አስታውሳለሁ ፥ የሀይስኩል ተማሪ እያለሁ የትምህርት ቤቱ ፌመስ ለመሆን ብዙ ነገር አደርግ ነበር፡፡ዛሬ ከጥቂት አመታት በኋላ እንኳን ያኔ የነበረኝ ዝና ፥ በትምህርት ቤቱ መማሬንም የሚያስታውስ ሰው የለም፡፡አስቡት የዛሬ 150 አመት ደግሞ … ጭራሽ ትምህርት ቤቱም ላይኖር ይችላል፡፡

አሁን አሁን ላይ ዘመኑ የኢንተርኔት በመሆኑ ኢንተርኔት ትዝታችንን ያስቀምጥልናል ብለን እናስብ ይሆናል፡፡ግን እስኪ በዚህ ዘመን እንኳ ዝነኛ የሆኑትን እናስታውስ፡፡ማይክል ጃክሰን በጊዜው ዝነኛ ነበር፡፡ነገር ግን ከሞተ ገና ሁለት አስርት አመታት እንኳ ሳይሞላው እየተረሳ ነው፡፡ዛሬ ላይ ካለው ትውልድ ማይክልን የሚያስታውሰው በጣም ጥቂቱ ነው፡፡እሱንም ገና ካወቁት ነው፡፡ ከ150 አመታት በኋላ ደግሞ ማይክል ጃክሰን የሚለው ስም ጨርሶ ለማንም የማይታወቅ ይሆናል፡፡

ማጠቃለያው፥ ህይወትን ቀለል አርገህ ኑር፡፡ምንም ሆነ ምንም ዘላለም የሚኖር የለም፥ ከዚህች ምድር በህይወት የሚወጣ ሰውም የለም፡፡ዛሬ ልትሞትለት እና ልትገድልለት የተዘጋጀኸው መሬት ከዚህ ቀደምም ብዙዎች ተጋድለውለት ሞተው ጭራሽ እንዳልነበሩ ሁሉ ተረስተዋል፡፡ከ150 አመታት በኋላ ዛሬ አንተ እንደ ትልቅ ሀብት የምታያቸው አብዛኞቹ ነገሮች ምንም ፋይዳ የሌላቸው ተራ ቁሶች ይሆናሉ፡፡

እና ምን ለማለት ነው ፥ ፍቅር ይግዛን ፥ መጠላለፍ ከጀርባ መወጋጋት መቀናናት መፎካከር ይቅርብን፡፡ህይወት ከማንም ጋር የምታደርገው ፉክክር አይደለችም፡፡ቀደምንም ዘገየንም መጨረሻችን መቃብር ነው፡፡

@Human_intelligence
በሰላም ብርሀን ያማረ፥ ጤናን ከደስታ ያጣመረ፥ በስኬት በድል የታጀበ...ዓዲስ ዓመት ይሁንልን🙏

       #ዮቶራዊት
    @Mahder_Kasahun
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

           ~~~
እሰይ ደስ ደስ ይበላችሁ ደስ ደስ ይበላችሁ:
ቅዱስ ዮሐንስ መጣላችሁ ደስ ደስ ይበላችሁ።

እንኳን ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሐንስ አሸጋገራችሁ አሸጋገረን::                                  
 
          
    መልካም አዲስ ዓመት!
       🌼እንቁጣጣሽ
                               
                              
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
"...የሰው ልጅ ሲቸግረው ልብሱን የቤቱን ዕቃ፤ ኩላሊቱንም  ሳይቀር ሊሸጥ ይችላል። ህሊናውን ከሸጠ ግን በጠና ቸግሮታል ማለት ነው።"

#ዶ/ር ምህረት ደበበ
Forwarded from LIBANOS
ወደ ስራ ስሄድ አንድ የስልክ እንጨት ላይ የተለጠፈ ወረቀት አየሁኝ: ጽሁፉ እንዲህ ይላል

"እዚህ መንገድ ላይ 50 ብር ጠፍቶብኛል: ያገኘ ሰው ካለ እባካችህን አድራሻዬ በሚቀጥለው መንገድ በቀኝ በኩል ስትታጠፉ ያለው አሮጌ ቤት ነው:: አይኔ እንደፈለግኩኝ አያይም: እድሜዬም ገፍቷል: ልጆችም የሉኝም"
ይህንኑ ጽሁፍ ተከትዬ ወደ አሮጌው ቤት ስሄድ አንዲት ሴትዮ ደጃፍ ላይ ተቀምጠዋል: የእግር ኮቴየን ሰምተው "ማነው? ማን ልበል?" አሉኝ

"እዚህ መንገድ ላይ 50 ብር አግኝቼ ነው: እሱን ልሰጥ ነው የመጣሁት" ብዬ መለስኩላቸው

አሮጊቷ እንባ ቀደማቸው - "ልጄ! እስካሁን ድረስ ከ40 በላይ ሰዎች 50 ብር መንገድ ላይ ወድቆ አገኘን ብለውኝ መጥተዋል"

ቀጠሉ እማማ - "እኔ ይህንን ጽሁፍ አልጻፍኩኝም: ጽሁፍ ለመጻፍም ሆነ ለማንበብም አይኔ እሺ አይለኝም"
50 ብሩን በእጃቸው አስጨበጥኳቸው

ጽሁፉን ከስልክ እንጨቱ ላይ እንድቀደው ቢነግሩኝም አላደረግኩም: የመጣውን ሰው ሁሉ ይህንኑ ነበር የሚሉት

ይህንን ጽሁፍ የጻፈውን ሰው እንዴት እንዳደነቅኩት : እኚህን ሴትዮ ለመርዳት የሄደበት ርቀት በጣም ነው ያደነቅኩት!

ከሴትዮዋ ቤት ስወጣ አንዲት ወጣት ልጅ አስቆመቺኝ
"ወንድሜ! እዚህ መንገድ ላይ 50 ብር አግኝቼ ነበር: የቤቱ አቅጣጫ በየት በኩል እንደሆነ ታውቃለህ እንዴ?"
በልቤ እየሳቅኩኝ ቤቱን ጠቆምኳት😍
     #ሰው_መሆኛ_መንገዱ_ብዙ_ነው ❤️🙌🏼
Zemelak

@poethaymi
..................................
ከረጅም አመት ቡኋላ እመጣለው…የዛኔም ግን እንደድሮ ሆኜ አደለም…አንቺ ማነሸ?…የት ነበርሽ?…ትለኝ ይሆናል…እኔም አንገቴን ደፍቼ እምልህ ነገር ቢኖር…"እያለሁ መች ነበርክ? ነው ።
ወደ ኃላ መመለስ ብችል የማስተካክለው ነበረኝ …ያለ ግን የተቋጨ ።

ኪያብ✍🏾
(...
ልክ ሲገባን ይረፍዳል 😞
🦋🦋
(...............................

ነገስ ፡እንደዛሬ ፡ይሆን ፡እንዴ፤ ነገስ ፡ይቀር ፡ይሆን ነገስ፡ ይከፋኝ፡ ይሆን፡ በንግግሬ፡ መሀል፡ እንባዬ፡ ይመጣ፡ ይሆን፡ ነገስ ፡ወድሻለው፡ የኔ፡ መባሉ፡ ይቀርብኝ፡ ይህን፡ ነገስ፡ ድምፁን፡ አልሰማው፡ ይሆን፡ ደስታ፡ ያልኩት፡ ነገ፡ እነዚን፡ ሳሳልፍ፡ ሰንብቻለው፡ ስለዚ፡ ለነገ፡ የዛሬ፡ ጭንቀቴ፡ ናቸው😞

🦋🦋ኪያብ
አንዳንድ ሰዎች ወደ ህይወትህ ሲመጡ አስተምረውህ ይሄዳሉ ጭካኔን በሁለት እግርህ መቆምን አስተምረውህ ይሄዳሉ ትዝታቸው ግን አይለቅህም የፈግታህም የስብራትህም ምንጭ ሆነው ይቀራሉ….

ኪያብ✍🏾
፡ እ ረ ግ ሜ ሻ ለ ው ❤️‍🩹

    አንቺ ከምታስቢው በላይ ደጋግሜ እረግሜሻለው…እረግሞኛል ብለሽ ካሰብሺው በላይ…ቤተ-ክርስትያን ፊት ቆሜም ሳይቀር እረግሜሻለው… ድ ፋ ል ኝ ብዬዋለው…ግን እርግማኔ አልሰራም…እንደለመንኩት ቢደፋሽስ ብዬ ስስቼስ ከልቤ ስላለመንኩት ይሆን…እርግማኔ ከልቤስ ስላልሆነ ይሆን…ግን ምንስ ልብ አለኝ እድሜ ለአንቺ ልብ አልባ አድርገሺኛል…ግን ቢደፋሽ ውስጤ ነው…🥀

       ✍🏽 ፊሊሞን የማርያም ልጅ
       🍁 @filimonletters 🍁
         🍃 @itsmefilimon 🍃
Forwarded from የኔ' ማስታወሻ ...✍️ (እንቊ ጳዝዮን ♥️)
አንድ ሰው ሞቶ የህይወት ታሪኩ ሲነገር... "ከአባታቸው ከአቶ እገሌ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ እገሊት ተወለዱ..." ይባላል

ምን ማለት ነው እንግዲህ?🤔
ድሮስ ከአባታቸው እና ከእናታቸው ውጪ ከአጎታቸው እና ከአክስታቸው ሊወለዱ ኖሯል?😏

@poethaymi
HTML Embed Code:
2024/04/30 00:29:33
Back to Top