🎖 #ብቻየን_ትተሁኝ_ጠፉ_እኮ_ሀቢቡና🎖
✍🏼 አሚር ሰይድ
ሠውባን ረዐ ምርጥ የነቢዩ ወዳጅና አገልጋያቸውም ነው። ከአላህ መልዕክተኛ ﷺ ብዙውን ጊዜ ከጎናቸው አይለዩትም። አንድ ቀን ግን ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺበጧት ወጡ። እስከ ማታም ድረስ ሳይመለሱ ቆዩ።
ሰይዲና ሙሀመድ ﷺ ወደ ቤት ሲመለሱ ትልቁ ሠውባን እንደ ሕፃን ልጅ ቁጭ ብሎ ሲያለቅስ አገኙት።
..... ሰውባን ሆይ!' ምን አስለቀሰህ??ብለዉ ጠየቁት
.........ብቻዬን ትተውኝ ጠፉ እኮ አንቱ የአላህ ነቢይ አላቸው
.......ይኸው ነው የሚያስለቅስህ???ሠውባን!ብለዉ ጠየቁት
.......አንቱ የአላህ መልዕክተኛ! ሙሉውን ቀንና ለሊት ብቻዬን ትተውኝ ሲጠፉ ብቸኝነት ተሰማኝ። ጀነት ብገባ እንኳ ደረጃዬ ከታችኛው እንደሚሆን አውቃለሁ። እርስዎ የአላህ መልዕክተኛ ነዎትና በጀነት ውስጥ ደረጃዎ ትልቅ ነው። እኔም ከርስዎ መድረስ አይቻለኝም። በጀነት ከርስዎ መለያየቴ አሳሰበኝና ሥጋት ገብቶኝ አለቀስኩኝ።' አላቸው።
ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ የሠውባንን ስጋት እንዲህ በማለት አቃለሉለት። “ሠውባን ሆይ! አንድ ሰው ከወደደው ጋር እንደሚቀሰቀስ አላወቅክም እንዴ!”
ብለዉ በሀዘን የጨለመ ፊቱን የደስታ ብርሀን ፍካት ሰጡት ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ♥
የኛ ለነብዩ ﷺ ያለን ፍቅር ምን ያህል ነዉ?? ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ ላይ በፍቅር በደስታ ስንት ሶለዋት እናወርዳለን??
ራሳችንን እንፈትሽ!!!
◈━━━━━━━━◈━━━━━━━━
4 another channal👇
hottg.com/Islam_and_Science
💐<<<<<<>>>>>>⭐️<<<<<<>>>>>>💐
hottg.com/IslamisUniverstiy_public_group
hottg.com/IslamisUniverstiy_public_group
>>Click here to continue<<