TG Telegram Group & Channel
ISLAMIC SCHOOL | United States America (US)
Create: Update:

🎖🎖 #የአራቱ_መዝሀብ_ባለቤቶች🎖🎖
               ✍🏼 አሚር ሰይድ

የአራቱ ዝነኞቹ መዝሀቦች ባለቤቶች የት እንደተወለዱ፣ መቼ እንደተወለዱና መቼ እንደሞቱ በቅደም ተከተል እነሆ

➊ - አል-ኢማሙ አቡ ሐኒፋ አን-ኑዕማን ቢን ሣቢት፡- በዒራቅ ውስጥ ኩፋ በምትባል ከተማ  በ8ዐኛው ዓመተ ሂጅሪያ የተወለዱና በ150 ዓመተ ሂጅሪያ ሙተዋል

➋ - አል-ኢማሙ ማሊክ ቢን አነስ (የዳሩል ሂጅራ ኢማም)፡- በመዲነቱን ነበዊያ በ93 ዓመተ ሂጅሪያ የተወለዱና በ179 ዓመተ ሂጅሪያ እዚያው ሙተዋል

➌ - አል-ኢማሙ ሙሐመድ ቢን ኢድሪስ አሽ-ሻፊዒይ፡- በ150 ዓመተ ሂጅራ በሻም ሀገር ውስጥ በጋዛ ላይ የተወለዱና በ204 ዓመተ ሂጅሪያ በግብፅ ላይ የሞቱ

➍ - አል-ኢማሙ አሕመድ ቢን ሐንበል:- በ146 ዓመተ ሂጅሪያ በበግዳድ የተወለዱና በ241 ዓመተ ሂጅሪያ እዚያ የሞቱ ናቸዉ
አሏህ ሁሉንም ቀብራቸዉን ብርሀን ያድርግላቸው

🔰🔰🔰 #አራቱ_የመዝሀቦች_ባለቤቶች የአላህ
መልዕክተኛ ﷺ ሱንናን እንዳለ ወስደው በመከተልና አጥብቀው በመያዝ ዙሪያ እንዲህ ብለዋል፡-

☞ ኢማም አቡ ሐኒፋ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፡- ሐዲሡ ትክክለኛ ከሆነ የኔ መዝሀብ እርሱ ነው፡፡ እንዲህም ብለዋል፦ እኛ ከየት እንደወሰድነው ሳያውቅ ለእንድም ሰው የእኛን ንግግር መውሰድ አይፈቀድለትም፡፡

☞ ኢማም ማሊክ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፡- እኔ ስህተት የምሰራና ትክክል የምሆን የሰው ልጅ ብቻ ነኝ፤ ስለሆነም አስተያየቴን ተመልከቱ፤ በውጤቱም ከኪታብና በሱንና ጋር በገጠመ ቁጥር ያዙት፤ በኪታብና ከሱንና ጋር ባልገጠመ ቁጥር ደግሞ ተውት።

☞ኢማም አሽ-ሻፊዒይ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፦ እኔ ካልኩት በተቃራኒ በነቅል (በማጣቀስ) ሰዎች ዘንድ ማንኛውም ከአላህ መልዕክተኛ ﷺ የሆነ ዘገባ ትክክለኛነት ያለበት ጉዳይ ሁሉ ካለ፣ እኔ በሕይወት ሳለሁም ሆነ ከሞትኩ በኋላ ከርሱ ተመላሽ ነኝ፡፡

☞ ኢማም አሕመድ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፡- እኔን በጭፍኑ እትከተለኝ፤ ማሊክንና ሻፊዒይን በጭፍኑ እትከተላቸው፤ ይልቁንስ እነርሱ ሁላቸውም የሀይማኖቱ ኢማሞች ነበሩ፡፡ብለዋል፡፡

⚠️ ዛሬ ግን እኛ ሙስሊሞች ስለመዘሀባቸዉ የሰጡትን አስተያየት ወደ ጎን ትተን በእነሱ ዙሪያ ስንጨቃጨቅ ስንነታረክ ብዙ ዘመናት አለፍን ...መቼ ይሆን ወደ አቅላችን ተመልሰን መዝሀቦቹን ወደ ቁርአን ሀዲስ ወስደን በቁርአን መስመር መከተል የምንጀምረዉ??

◈━━━━━━━━◈━━━━━━━━   
4 another channal👇
             hottg.com/Islam_and_Science
💐<<<<<<>>>>>>⭐️<<<<<<>>>>>>💐
hottg.com/IslamisUniverstiy_public_group

>>Click here to continue<<

ISLAMIC SCHOOL

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)