ኢየሱስ ክርስቶስ ማን ነው?
ክፍል 1⃣
“እየሱስ ክርስቶስ ፍጡር እንጂ ፈጣሪ ኣይደለም”
1• ” የጌታችን የእየሱስ ክርስቶስ ኣምላክና ኣባት ይባረክ”
( 2ኛቆሮንጦስ 1:3)
“የጌታችን የእየሱስ ክርስቶስ ኣምላክና ኣባት ይባረክ”(ኤፌሶን
1:3)
“የጌታችን የእየሱስ ክርስቶስ ኣምላክና ኣባት ይባረክ”
(1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1:3)
🍂የኛ ጥያቄ:🍂
1• ማነው የእየሱስ ክርስቶስ ኣምላክ?
2• እየሱስ ክርስቶስ ኣምላክ ከሆነ, ለኣምላክ ሌላ ኣምላክ ኣለው
ወይ? ኣምላክ ስንት ነው?
2• “እውነተኛ ኣምላክ ብቻ የሆንህ ኣንተን የላክኸውንም እየሱስ ክርስቶስ ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሂወት ናት”
( የዬሐንስ ወንጌል 17:3)
🍂የኛ ጥያቄ:🍂
እየሱስ ክርስቶስን የላከ እውነተኛውና ብቸኛው ኣምላክ ማነው?
3• ” ሁሉ ከተገዛለት በኃላ ግን እግዚኣብሄር ሁሉ በሁሉ ይሆን ዘንድ
በዚያን ጊዜ ልጁ ራሱ ደግሞ ሁሉን ላስገዛለት #ይገዛል”
(1ኛ ቆሮንጦስ 15:28)
🍂የኛ ጥያቄ:🍂
1•ለእየሱስ ክርስቶስ ሁሉን ያስገዛለት ማነው?
2• እየሱስ ክርስቶስ ኣምላክ ከሆነ ኣምላክ ገዢ ነው ወይስ ተገዢ?
ለማን ነው የሚገዛው?
4• “ኢየሱስም ገና ወደ ኣባቴ ኣረግሁምና ኣትንኪኝ, ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ,እኔ ወደ ኣባቴና ወደ ኣባታችሀ ወደ ኣምላኬና ወደ ኣምላካችሁ ኣርጋለሁ ብለሽ ንገሪያቸው ኣላት”
( የዬሐንስ ወንጌል 20:17)
🍂የኛ ጥያቄ:🍂
1• ወደ ኣምላኬና ወደ ኣምላካችሁ ሲል ኣምላኩ ማነው?
2• እየሱስ ኣምላክ ከሆነ, ወደ ወንድሞቼ ሲል, ኣምላክ ወንድሞች ኣሉት ወይ?
5• ” በዘጠኝ ሰዓትም ኢየሱስ,ኢሎሄ ኢሌሄ ላማሰበቅታኒ? ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ ትርጓሜውም ” ኣምላኬ ኣምላኬ ለምን ተዉከኝ? ማለት ነው”
( ማርቆስ ወንጌል 15:34)
🍂የኛ ጥያቄ:🍂
እየሱስ ኣምላክ ከሆነ, ማንን ነው ኣምላኬ ኣምላኬ እያለ የሚጠራው?
6• ” እየሱስም መልሶ እንዲህ ኣለው,ከትእዛዛቱ ሁሉ
ፊተኛይቱ,እስራኤል ሆይ ስማ ጌታ ኣምላካችን 1 ጌታ ነው”
( ማርቆስ 12:29)
እዚህ ላይ እየሱስ ጌታ ኣምላካችሁ ሳይሆን ጌታ ኣምላካችን ነው ያለው።
🍂የኛ ጥያቄ:🍂
እየሱስ ኣምላክ ከሆነ ” እኔ ነኝ ኣምላካችሁ” ለምን ኣላለም?
7• “ኢየሱስም ስለምን ቸር ትለኛለህ? ከኣንዱ ከእግዚኣብሄር በቀር ቸር ማንም የለም”
( ማርቆስ 10:17)
የኛ ጥያቄ:
እየሱስ ኣምላክ ከሆነ, ቸር መምህር ሆይ ተብሎ ሲጠራ ለምን ተቃወመ?
“እየሱስ የተከበረ የፈጣሪ መልእክተኛ"
በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል.........
https://hottg.com/Ibnrediwancomparative_channell
>>Click here to continue<<

