TG Telegram Group Link
Channel: ወኔ እና ቅኔ -(ፈይሠል አሚን)
Back to Bottom
. . .of the day!😎
. . .of the day!😎
የምፈልግበት ቦታ ላይ ባሰብኩት ሰዓት አልደርስም. . .ምክንያቱም :-
👉አላጭበረብርም
👉አልዋሽም
👉አልሰርቅም
👉አላታልልም
👉አላጎበድድም(አላሽቃብጥም)
👉ዙሪያዬ ያሉትን አልጠልፍም
👉በሰዎች ደስታ አልናደድም
👉አልመቀኝም

ስለዚህ ሕልሜ ላይ ለመድረስ እዘገያለሁ። የዚህ ዘመን ጽልመታዊ ጎን ይኽ ነው። ስኬትህ ሕሊናን በሚጎዱ ፋሻዎች የተጠቀለለ ነው። ቢኾንም ግን ዘግይቼም ቢኾን እደርስበታለሁ። Life is not easy...and so am I.
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
@huluezih
@huluezih
. . .of the day!😎

(እስቲ የገባው ያብራራልን)
ዐውቃለሁ ተጠፋፍተናል ግን. . .
.
ይኼ ቻናል ከነ ቤተሰቦቹ በእጅጉ ናፍቆኛል። ከእናንተ ጋር ቃላትን፣ሐሳቦችንና ስሜቶችን መጋራት እኔ ዘንድ እንደ ዕድል የሚቆጠር ነገር ነው። ዕድሉ ስላለ ብቻ ደግሞ ያሰብኩትን እና የጻፍኩትን ግሳንግስ ሁሉ እዚህ አላመጣም። (መጥፋቱ ከመጠንቀቅም የመነጨ ነው ለማለት ነው)
.
ላለፉት ብዙ ቀናት በጥሞና እና ከሥነ-ጽሑፍ ካልራቁ ሌሎች ሥራዎች ጋር ስታገል እንዲሁም ትንሽ እረፍት ስወስድ ቆይቻለሁ። ከአሁን በኋላ በሚከተሉት ቀናት ውስጥ አዳዲስ ነገሮች ይዤ እንደምመጣ ተስፋ አደርጋለሁ። የሚመጡት አዳዲስ ነገሮች ይሳኩ ዘንድ ደግሞ የእናንተ እገዛ እና ተሳትፎ ከምንግዜውም በላይ ያስፈልገኛል። ብዙዎቻችሁ በዚህ ቻናል ለብዙ ጊዜያት በመቆየታችሁ፣ በቅርብ የተቀላቀላችሁን ወዳጆች ደግሞ በምትሠጡት በጎ አስተያየቶች ምክንያት ከእናንተ የምፈልገውን ነገር እንደማላጣ ልቤ ያምናል። በዚህ ጉዳይ ላይ በሰፊው እመለሳለሁ።
.
ሙስሊም ወንድምና እህቶቼ እንኳን ለ1445ኛው ዓመተ ሒጅራ የዒድ አል ፊጥር በዓል በኸይር አደረሳችሁ!
.
ሁላችሁንም እወዳችኋለሁ
.
@huluezih
@huluezih
ገድሎ መትረፍ!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
በጅምላ ሲበርደን፣
ብርዱ አጋመደን. . .
እየሣቁ መኖር፣በወል አዋሃደን!
ክፉ ቀን ሲያልፍ ግን. . .
ሙቀት አካካደን!
ምቾት አሳበደን!
.
ያለፈውን ረስተን፣
ጎዳናውን ስተን፣
ያረገዝነው ቂም፣አማዘዘን ሽመል፣
ገድሎ መትረፍ ኾነ የበረሃ አመል!
የደጉ ቀን ገድል፣ተመርዞ ቀረ፣
ያሳደግነው እባብ ቆዳ እየቀየረ!
.
@huluezih
@huluezih
. . .of the day!😎
ሰው አለኝ የሌለ!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
ሽንቁር አለኝ እንደ ሰው፤
የማልነካው!
የማልዳብሰው!
ተረት እየመሰለኝ ችዬ 'ማልጨርሰው!
.
አለችኝ አንዲት ሐረግ፤
ገሃድ ያልወጣች፣ረቂቅ ፈለግ፣
የማታደምቀኝ የሩቅ ማዕረግ!
.
አለችኝ አንዲት ቁስል፣
እንደ ሳል የምታ'ስል፣
የማትተው የትዝታ ምስል!
.
በዚህ መሐል አለሁ!
እዚህ ደርሼያለሁ!
በማይጥል ውድቀት ውስጥ፣
መስዬ ቆሜያለሁ!
ኦናነት ሞልቶኝ:ልቤን እያቄለ
ሩሔን እያቄለ. . .
ብቻ ሰው አለኝ!
የሌለ!
.
@huluezih
@huluezih
አልጠበቅንም አሁን!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
አለ! ይኖራል! ነበረ!
ሞት እውነት ነውና፣
ያልተጠረጠረ!
ሁሉም መሞቱን ያውቃል፣
የሰው ልጅ ሊሞት. . .
ስለተፈጠረ!
.
ግን ያንቺ ሞት. . .
ከነ አመጣጡ፣
ከነ አቀጣጡ፣
ይለበልበናል እያደር እስካሁን፣
መሞትሽን ብናውቅም. . .
አልጠበቅንም አሁን!
.
ሰው መንገደኛ ነው፣
በሞት መንገድ አዝግሞ
ወደ 'ማይቀር ሒያጅ፤
የራሱን ሞት አይጠብቅም እንጂ!
.
@huluezih
@huluezih
ስለ መጽሐፍት ቀን ሲነሣ. . .
.
አንዳንድ በተለያየ መልኩ የተበደሉ መጽሐፍት መደርደሪያችን ውስጥ አይጠፉም። ከየት እንዳመጣናቸው የማናውቃቸው፣ ሀፍረት ይዞን የገዛናቸው፣ መርጠን ገዝተናቸው የመነበብ ዕጣ ያልሠጠናቸው. . .በብዙ መንገድ የተበደሉ መጽሐፍት ይኖሩናል።
.
"ስለ ትናንሽ አለላዎች" መደረደሪያዬ ውስጥ ካሉ እጅግ ከሚያሳዝኑኝ መጽሐፍት በቁንጮነት ይቀመጣል። መጽሐፉን ከገዛሁት ከብዙ ጊዜያት በኋላ አማራጭ ሳጣ ነበር ያነበብኩት። አንብቤ ስጨርሰው በእጅጉ ተቆጨሁ..."እስከዛሬ ለምን አባቴ ነው ያላነበብኩት?" የሚል ፀፀት ወረረኝ።
.
ዮናስ አ.(አ ማንን እንደሚወክል አላወቅኩም) ይባላል ደራሲው። ሥሙንም ሠምቼው አላውቅም። ወጣትም ጎልማሳም ሊኾን ይችላል(አጻጻፉ ወጣትነትን ቢያስገምትም)፣ ማንም ሲያወራለት አልገጠመኝም። ግን በጣም የሚደነቅ የሥነ-ጽሑፍ ችሎታና ዕውቀት እንዳለው መጽሐፉን ያነበበ መረዳት ይችላል። ቋንቋው፣ ገለጻው፣ "በድንገተኛ መገለጥ (instant realization) በኩል የሚነግረን ንዑስ ታሪኮች...ለዛ አላቸው።

በርግጥ አጻጻፈ-ዘይቤውን የዚህ ዘመን ደራሲዎችን የሚያጠቃው የአዳም ረታ ሕፅናዊነት ያጠቃዋል። መጽሐፉን ሳነብ በተደጋጋሚ "ግራጫ ቃጭሎችን" በትውስታ አነፈንፍ ነበር።ቢኾንም ንባብ ወዳጅን በሚመጥን ደረጃ የተጻፈው መጽሐፍ ነው "ስለ ትናንሽ አለለዎች"
.
ያልተወራለት፣ብዙ ማሕበራዊ ገፆች ያላስተዋወቁትን መጽሐፍ የማመን ችግር ስላለብን ነው እንጂ አንገታቸውን ደፍተው ሲሠሩ ከርመው እንዲህ ድንገት ብቅ የሚሉ ገሞራ ጸሐፊዎች አሉ። ያላነበባችሁት ሰዎች ይኽን መጽሐፍ አንብቡት። ከታተመ 5 ዐመት ሊኾነው ነው...ጃዕፈር ጋር አይጠፋም። ደራሲውን የምታውቁ ካላችሁ አመሥግኑልኝ...ሥነ-ጽሑፍ ላይ ተስፋ እንዳንቆርጥ ስላደረግከኝ!
እናንተስ underated ወይም ብዙ ያልተባለላቸውን ምርጥ መጽሐፍት ታውቃላችሁ? እስቲ ንገሩኝ!
.
@huluezih
@huluezih
. . .of the day!😎
የሙዓዚኑ ድምጽ!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
ምቹ ፍራሼ ላይ. . .
ስክነት አልሰፈረም፤
ከላባው ትራሴ፣
ከሐር መከዳዬ፣ሰላም አልነበረም!
እጋላበጣለሁ!
.
ልብ ወደ አምላኩ አዘውትሮ ሲያምጽ፣
ከመስጊድ ተሰማኝ የሙዓዚኑ ድምጽ!
"ጸሎት ከእንቅልፍ ይሻላል"
እያለ ደጋግሞ ይጣራል!
.
ሳይጸልይ ያነጋው ልቤ አመጸኛው፣
ድርብርብ ኩኔነው ፊትስ መች አስተኛው?
.
ከሁለት አንድ አጥቶ፣ እንዲህ ከመቀጣት፤
መጸለይ ይሻላል እንቅልፍም ከማጣት!
.
መልካም ጁምዓ!
.
@huluezih
@huluezih
HTML Embed Code:
2024/05/05 10:53:58
Back to Top