TG Telegram Group Link
Channel: የ ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የስነምግባር እና ፀረ ሙስና ክበብ | Hawassa University Ethics and Anti corruption Club
Back to Bottom
የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የፀረ-ሙስና ቀንን አከበረ
------------------------
በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በአለም አቀፍ ደረጃ ለ19ኛ በሀገራችን ደግሞ ለ18ኛ ጊዜ የሚከበረዉን አለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን “ሙስናን መታገል በተግባር” በሚል መሪ ቃል ዛሬ አክብሯል።

የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ኢንጂነር ፋሲካ ቤተ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ስናነሳ ሰዎች ብዙ ጊዜ ከራሳቸዉ ያርቁታል፤ ሙስናና ብልሹ አሰራር መጠኑ እና አይነቱ ይለያይ እንጂ በሁሉም ተግባር ዉስጥ ይገኛል ብለዋል። አክለዉም ሙስና ከግለሰብ አንስቶ በሀገር ደረጃ ከባድ ጉዳት እንደሚያደርስ ገልፀዉ ይህንን አፀያፊ ተግባር ለማስተካከል በንደፈ ሃሳብ ከማወቅ በዘለለ በተግባር ልንታገለዉ ይገባል በማለት እንደ ተቋምም የተሰጠንን ተልዕኮ ለመወጣት መምህራን፣ የአስተዳደር ሰራተኞች እና ኃላፊዎች ጊዜያችንን፣ ሀብታችንን እና እዉቀታችንን ለታሰበለት ዓላማ በማዋል ሙስናንና ብልሹ አሰራርን የሚፀየፍ ብቁ ዜጋ በየዘርፋችን ልናፈራ ይገባናል ብለዋል።

በዕለቱም በህግና ገቨርናንስ ኮሌጅ መምህር የሆኑት አቶ አዱኛ ስሜ "ሙስና፣ መንስሔዎቹና መፍትሄዎቹ" በሚል ርዕስ የመወያያ ፅሁፍ ያቀረቡ ሲሆን ተሳታፊዎችም በቀረበዉ ርዕስ ላይ ዉይይትና ተሳትፎ በማድረግ ፕሮግራሙ ተጠናቋል።
ዛሬ ከሰዓት ስምንት ሰዓት ላይ በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ እንድንገኝ ።
ሰላም እንዴት ቆያችሁን ውድ የ ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎቻችን እና የክበባችን አባላት !
            
የግቢያችን አንጋፋ ክበብ የሆነው የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ክበብ የዘንድሮውን ዓለም ዓቀፍ የፀረሙስና ቀንን  ''ሙስናን መታገል በተግባር" በሚል መሪ ቃል  በቀን 11/04/15 ዕለተ ማክሰኞ ከጥዋቱ 2:30 ጀምሮ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ስለሚያካሄድ ከሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ሬጅስትራር ጀርባ በሚገኘው የቀድሞው ፕሬዝዳንት ቢሮ አዳራሽ እንድትገኙ ስንል በፍቅር እንጋብዞታለን።
                
 ተማሪዎችን በስነምግባር መገንባት   
         ሀገር መገንባት ነው"
                    
     
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሥነ-ምግባር እና ፀረሙስና ክበብ
የፈረንሳዩ ተጨዋች Kylian Mbappe አባት Wilfred Mbappe እንዲህ ብሏል። " ልጄ ለካሜሮን ብሄራዊ ቡድን እንዲጫወት ከፌደሬሽኑ ሰዎች አንዱን ባማክረው ጉዳዩን ለማሳካት ጉቦ ጠየቀኝ። ያንን አድርጌ ሊጫወት እንደማልፈልግ ወሰንኩ።ፈረንሳዮች ግን ችሎታህን ነው የሚያዩት እንጂ ምንም አይጠይቁህም " ሲል ተናግሯል።

የኪሊያን አባት ካሜሩናዊ ሲሆን እናቱ አልጄሪያዊ ናቸው። የተወለደው በፓሪስ ፈረንሳይ ሲሆን እ.ኤ.አ በ 2018 በሩሲያ የተካሄደውን የዓለም ዋንጫ ከተቀዳጀው የፈረንሳይ ቡድን ውስጥ አንዱ ነበር።

አፍሪካ ውስጥ ስንት አቅም ችሎታ ያላቸው ሰዎች እየተኮረኮሙ በገንዝብ ሀይል የሚረማመዱ ችሎታና ብቃት የሌላቸው ወደ ከፍታ የሚደርሱበትን ሁኔታ ስታይ የአፍሪካ አለማደግ አይደንቅም አፍሪካ ከእርግማኗ የምትወጣው ሙስናና ጉቦን የሚጠየፍ ትውልድ ሲመራት ብቻ ነው፡፡

"ተማሪዎችን በስነምግባር መገንባት   
         ሀገር መገንባት ነው"
                    
   
          
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሥነ-ምግባር እና ፀረሙስና ክበብ

Join our telegram page

https://hottg.com/HUethics
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ Main Campus '‘ሙስናን መታገል በተግባር’' በሚል መሪ ቃል ዓለም ዓቀፍ የፀረ ሙስና ቀን በዛሬው ዕለት ተከብሯል፡፡

የምርምርና ቴ/ሽ/ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታፈሰ ማቲዎስ ሙስናና የስነ ምግባር ችግር ለአለምችን እና ለሰው ልጆች ፈተና ሆኖ የቆየ ሲሆን በተለይ በአፍሪካ በሚገኙ ሀገራት እጅግ በጣም ብዙ ሀብቶች እንደሚመዘበሩና በዚህ ችግር ውስጥም እየዳከሩ እንደሚገኙ በርካታ ጥናቶች እንደሚያሳዩ ጠቅሰው አለማችን ለመሰረታዊ ፍላጎት የሚሆን በቂ ሃብት ቢኖራትም ጥቂቶች በስግብግብነታቸው የተነሳ የብዙሃኖችን ሃብት በመመዝበር ያለቅጥ በማከማቸታቸው ምክንያት ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል እንዳይኖር፣ የሰዎች የእርስ በርስ ግንኙነት እንዲደፈርስና በየቦታው ግጭት እየነገሰ እንዲመጣ ሆኗዋል ብለዋል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የስነ-ምግባርና ፀረሙስና ክበብ አስተማሪና ትምህርታዊ የሆነ ጭውውት እንዲሁም ሙስናን በተመለከተ ድንቅ የሆነ መነባነብ ለታዳሚው አቅርበዋል።

በተጨማሪም በፕሮግራሙ ላይ አቶ አባይነህ ገናሌ የስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት ተወካይ ዳይሬክተር ሙስናን መታገል በተግባር እንዴት ይቻላል በሚል ሃሳብ ላይ የመወያያ ሃሳብ ያቀረቡ ሲሆን ተሳታፊዎችም የተለያዩ ነጥቦችን አንስተው ተወያይተዋል፡፡

በመጨረሻም የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አያኖ በራሶ እንደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ከከፍተኛ አመራር ጀምሮ መምህራኖችና የአስተዳደር ሰራተኞች ለስራ የተመደበላቸውን ጊዜና ሰዓት እንዲሁም መገልገያ ቁሳቁሶችን በአግባቡ ከመጠቀም አንስቶ ሙስናን እና የስነ ምግባር ብልሽቶችን በመጋፈጥ እና ተማሪዎችም በስነ ምግባር የታነፁ ብቁ ዜጋ እንዲሆኑ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ አሳስበው ፕሮግራሙ ተጠናቋል።


https://hottg.com/HUethics
ለክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው አደረሳችሁ!

መልካም ፋሲካ ❤️

የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የስነምግባር እና ፀረሙስና ክበብ

https://hottg.com/HUethics
ለ እስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1444ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!


ኢድ ሙባረክ!

በዓሉ የሰላም: የፍቅርና የአንድነት ይሁንላችሁ!


የ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የስነምግባርና ፀረሙስና ክበብ

https://hottg.com/HUethics
እንኳን ለአዲስ ዓመት 2016 ዓም በሰላም በጤና አደረሳችሁ!

*****

አዲሱ ዓመት የሰላም: የፍቅር: የአንድነትና የስኬት ይሁንላችሁ!!!
HTML Embed Code:
2024/04/26 02:16:20
Back to Top