TG Telegram Group Link
Channel: Hawassa University
Back to Bottom
ኮሌጁ በስርአተ-ጾታ ጉዳዮች ላይ ለአስተዳደር ሰራተኞች ስልጠና አዘጋጀ።
*//*
ሰኔ 19/2017 ዓ/ም
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህግና ገቨርናንስ ኮሌጅ ለአስተዳደር ሰራተኞቹ የስርአተ-ጾታ ጉዳይን በዕለት ተዕለት የአስተዳደር ስራዎች ላይ ታሳቢ አድርገው የስርአተ-ጾታ ፍትሐዊነትንና እኩልነትን ማረጋገጥ እንዲችሉ የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰኔ 18/2017 ዓ.ም ሰጥቷል።

የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ደብረወርቅ ደበበ የስርአተ-ጾታ እኩልነት ሁለቱንም ጾታዎች አጠቃሎ የያዘና ዘላቂ ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ሀሳብ የያዘ በመሆኑ ሁሉም የአስተዳደር ሰራተኞች በዚህ ዙሪያ አስፈላጊውን ግንዛቤ በመያዝ በስራ አተገባበራቸው ላይ ሊያካትቱት ይገባል ብለዋል። ስልጠናው በስርአተ-ጾታ ምንነት፣ አላማዎች፣ ፍላጎቶች፣ ስርአተ ጾታን በስራ ሂደት ላይ የማካተት አስፈላጊነት እና ስልቶቹ ምን ይመስላሉ በሚለው ላይ አተኩሮ መዘጋጀቱን ዶ/ር ደብረወርቅ አክለዋል።

የአስተዳደር ሰራተኞች የስርአተ-ጾታ ጉዳይን ከዋና የልማትና የስራ ተግባሮቻቸው ጋር አካተው እንዲሰሩና በተማሪዎች፣ መምህራን እና ተገልጋዮች አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ለማስቻል ግንዛቤ እንደሚፈጥር የተናገሩት አሰልጣኝ በገቨርናንስና ልማት ጥናት ት/ቤት መምህርና ተመራማሪና የሆኑት አቶ አስፋው ዘውዴ ናቸው።

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
ሁሌም ለልህቀት!

በዚህ ይከታተሉን:-
***
Facebook: https://www.facebook.com/Hawassa.University?mibextid=ZbWKwL
Website: https://www.hu.edu.et
Telegram: https://hottg.com/HUCommunicationsoffice
Hawassa University Hosts National Training on Applied Data Management and Analysis for One Health Professionals
*//*
June 26/2025
Hawassa University is currently hosting a seven-day national training program on Applied Data Management and Analysis for Human, Animal, and Environmental Health Professionals, as part of the Ethio-Pandemic Multi-Sectoral Prevention, Preparedness, and Response (EPPR) Project, funded by the Pandemic Fund, June 23 - 29, 2025.

Prof. Mebratu Mulatu, Senior Adviser to the V/President for Research & Collaboration at HU, officiated the opening ceremony where he emphasized the university’s prominent role as a key stakeholder in the Ethio-Pandemic Multi-Sectoral Prevention, Preparedness, and Response (EPPR) Project. He noted that the university currently oversees over 106 collaborative projects, implemented in partnership with both national and international institutions, delivering significant impact to the university, surrounding communities, and the nation as a whole.
Dr. Bantetegegn Tamirat, Senior Expert in Veterinary Disease Surveillance & Control at the Ministry of Agriculture, underscored that zoonotic diseases have become a critical global issue, demanding strong collaboration across animal, human, and environmental health sectors.

Dr. Hunachew Beyene, the project coordinator, stated that the project will play a crucial role in strengthening timely surveillance data collection, analysis, interpretation, and presentation, thereby contributing to the early detection and prevention of public health threats. Dr. Hunachew mentioned that a total of 100 professionals working in human, animal, and environmental health (representing the One Health approach) from all regions of the country will be trained in three rounds until August 2025.

He also noted that the training was launched after the development of a comprehensive training document on Applied Data Management and Analysis for Human, Animal, and Environmental Health Professionals, prepared by senior experts from Hawassa University and Addis Ababa University's Aklilu Lemma Institute of Pathobiology.

Hawassa University
Ever to Excel!
ኮሌጁ በፕሮግራም አክሬዲቴሽን ላይ የምክክር መድረክ አዘጋጀ።
*//*
ሰኔ 20/2017 ዓ/ም
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በቁልፍ የአፈጻጸም አመላካቾች ላይ የተቀመጠውን የፕሮግራሞች አክሬዲቴሽን ግብ ለማሳካት ሊደረጉ ስለሚገቡ ቅድመ ሁኔታዎች ከኮሌጁ አመራሮችና የትምህርት ክፍል ኃላፊዎች የገላጻና ስልጠና መድረክ ተካሂዷል።

የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ዙፋን በደዊ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለጹት የትምህርት ፕሮግራሞች አክሬዲቴሽን ማግኘታቸው ኮሌጁንና ዩኒቨርሲቲውን አለምአቀፋዊ ተወዳዳሪ ስለሚያደርግ የሚሰጡ ፕሮግራሞችን የጥራት ደረጃና የተመራቂዎችን አጠቃላይ ተፈላጊነት በእጅጉ እንደሚጨምር ገልጸዋል። ተሳታፊዎች በስልጠና ቆይታቸው የፕሮግራም አክሬዲቴሽን ምን ቅድመ ሁኔታዎች ይፈልጋል የሚለውን በመገንዘብ በየደረጃቸው የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ተፈጻሚ ለማድረግ ሊተጉ እንደሚገባም ዶ/ር ዙፋን አሳስበዋል።

ከተወዳዳሪ የምርምር ዩኒቨርሲቲ ከሚጠበቁ ማሟያዎች መካከል የፕሮግራሞችና የቤተ-ሙከራ አገልግሎቶች አክሬዲቴሽን አንዱ መሆኑን የጠቆሙት የኮሌጁ የጥራት ማረጋገጫና ማሻሻያ መሪ ዶ/ር መቅደስ ማሞ በኮሌጅ ደረጃ ያሉ ፕሮግራሞችን ከአለምአቀፋዊው መመዘኛ ጋር ተስተካካይ ለማድረግ ሊወሰዱ የሚገባ እርምጃዎችን የሚዳስስ የምክክር መድረክ ይሆናል ብለዋል።

የፕሮግራም አክሬዲቴሽን ቅድመ ሁኔታዎችንና አፈጻጸሞቹን የተመለከተ ገለጻ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የጥራት ማረጋገጫ ዳይሬክተር ዶ/ር አቻምየለሽ ገ/ጻዲቅ እና በም/ዳይሬክተሯ መቅደስ መኮንን አማካኝነት ቀርቧል።

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
ሁሌም ለልህቀት!

በዚህ ይከታተሉን:-
***
Facebook: https://www.facebook.com/Hawassa.University?mibextid=ZbWKwL
Website: https://www.hu.edu.et
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያው ዙር ከ35 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ለማስፈተን እየተቀበለ ነው::
*//*
ሰኔ 22 ቀን 2017 ዓም

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና በመጀመሪያው ዙር የሚፈተኑ 35,650 የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችን ከሲዳማ ብሔራዊ ክልልና ከአጎራባች የኦሮምያ ክልል ትምህርት ቤቶች ተቀብሎ በሰባቱም የማስተማሪያ ግቢዎቹ (ካምፓሶቹ) በወረቀትና በይነ መረብ ያስፈትልናል:: ተፈታኝ ተማሪዎች ከሰኔ 20/2017 ዓም ጀምሮ ወደየግቢው እየገቡ ነው::

ለተፈታኝ ተማሪዎች በሙሉ መልካም ውጤት እንመኛለን!

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
ሁሌም ለልህቀት!
HTML Embed Code:
2025/06/30 08:48:59
Back to Top