TG Telegram Group Link
Channel: ወርቃማ ንግግሮች
Back to Bottom
በልቅና ውቅያኖስህ ውስጥ ምናቦች ዋኙ። ከቅድስና ነፀብራቅ እልፍኝህ ውስጥ እዝነትህ ጎላ። በምሉዕነትህ ሜዳ ላይ የደጋጎች ልቦና ተንከራተተ።

የምሩጦች ምኞት ጥጉ በአንተ ተቋጨ። ገፅታህ ከመታየት የተጥራራ ነው፣ ባህሪያቶችህ ከልቦና ምስል የረቀቁ ናቸው፣ በስምህ የቅድስና መገለጫ ከከጃዮችህ ተሸሽገሃል፣ በናፍቆትህ የቦዘኑ ልቦችን በስምህ ቅድስና አፅናንተህበታል።

ጌታችን ሆይ! ለግርማህ ልቅና አይኖች አቀርቅረዋል። ለገዘፈው ወጀብህ ልቦናዎች ደነገጡ። ለፍትህህ ፍራቻ ደጋጎች ተርበተበቱ።

በወደድከው ልክ ተመስገን
በልቅናህ ልክ ተወደስ
ባሻህ ያህል ተጥራራ።

አሚን
~

ዘንጊዎች በዘነጉ፣አሰታዋሾች ባሰታወሱ ቁጥር፣ በረገፈው ቅጠል፣ በፈሰሰው አሸዋ፣ ሰማይን ባደመቁት ክዋክብት፣ ውቂያኖስ በያዘው ጠብታ መጠን የአላህ እዝነትና ሰላም በውዱ ነቢያችን ሙሐመድ(ﷺ)ላይ ይሁን!

➧. #አለይሂ_ሰላቱ_ወሰላም! ♥️
ልብ አትሙት!!
የትኛውንም መቅሰፍት ተጋፍጠህ ታልፈዋለህ!...የትኛውንም ዳገት ትወጣዋለህ!......የትኛውንም እሾህ ትራመደዋለህ.....የትኛውንም አድካሚ ሁሉ ታልፈዋለህ።

ልብ ከሞተች ተስፋ፣ወኔ፣አቅም ሁሉም ነገር አብሮ ይሞታል። ተስፋ መቁረት አማኞች ባህሪ አይደለም። ልብህ አይሙት። ልብ ካልሞተ ግባችንን ከአሏህ ጋር ማሳካት እንችላለን። ተነስና ታግል ሞክር ልፋ። በቅርቡ የሁሉንም ነገር ውጤቱን ታገኘዋለህ።

ምስል የጠንካራዎቹ ፍልስጤማዊ እናት !!
Forwarded from አረብኛ ቋንቋ እና ፅሁፍ መማረያ
በዝህ  ቻናል
አረብኛ እጅ ፅሁፍ
    ለጀማሪ በሚሆን ሁኔታ ተዘጋጅቶ ይቀርብበታል
እናንተም  ይህን እድል ትጠቀሙበት ዘንድ ጋበዝኳችሁ  👇

join request  በመንካት
approve እስከምትደረጉ ታገሱን 

👇👇
hottg.com/+_UDX5IlmY0FiYTk0
hottg.com/+_UDX5IlmY0FiYTk0
በጣም ይዋደዱ ነበር ! ነገርግን ሸይጧን ማሀላቸው ገብቶ አጋጫቸው ለመኮራረፍም ዳረጋቸው. በጧት ተነስታ ቁርሱን ሰርታ ገበታው ላይ አቅርባለት ትታው ወደ ሌላ ስራዋ ገባች. እሱም ከንቅልፉ ተነስቶ ቁርሱን ለመብላት ገበታው ላይ ታደመ ነገር ግን ከጎኑ ያቺ ሚወዳት ሚስቱ የለችም .ምግቡን ለመብላት ቢፈልግም ግን አልተቻለውም እሷ ነበረች እያጫወተች ምታጎርሰው በቃ የምግቡ ጣእምም አልመጣለት አለው ...

ወደ ማድ ቤቱ በመመልከት እንደ ከዚህ በፊቱ የሚስቱን መምጣት መጠባበቅ ጀመረ.ከማድ ቤት ዳቦ ይዛ አጠገቡ ልትቀመጥ ብትሞክርም አልቻለችም ትናንተ እንደዛ ሰድቧትና አስቀይማት ይቅርታ አለማለቱ አናዷታል.

ዳቦውን አስቀምጣለት ወደ ማድ ቤት በመመለስ እቃዎችን ማፀዳዳት ጀመረች በስራዋም ላይ ሳለች የበር ድምፅ ሰማችና ስትሄድ ባሏ ከቤት ወጥቶ ሂዷል .የበላበትን ለማነሳሳት ስትሄድ ያዘጋጀችው ምግብ አንድም ሳይነካ እንዳለ ነው ...

አዎ ያለኔኮ አይበላህም እኔ እነዳጎርስህና እንዳጠጣህ ፈልገህ ነበር ,ይህ ደሞ ላንተ አይገባህም አንተ እኔ እነደምከባከብህ ሞራሌን መጠበቅ አትችልበትም እያለች ከራሷጋ አወራች .. ምግብ ሳይበላ መሄዱ ግን አሳዝኗታል...

በሀሳብ ተውጣና አዝና ሱፍራውን ለማንሳት ስትል ሁለት አበባ ተመለከትች አንዱ ነጭ እና አንድኛው ቀይ ናቸው አበባዎቹ ከስራቸው ወረቀት ተቀምጧል ለካስ ደብዳቤ ፅፎ ኖሯል...

በአላህ ስም እጅግ በጣም አዛኝ በጣም ሩህሩህ በሆነው ይላል መግቢያው «ይድረስ በሂወቴ ፍፁም ውብ ለሆነችዋ አበባዬ፣ ለውዷ ሚስቴ፣ ሂወቴና እንከወዳኘው የምወዳት ለሆነችዋ...የአላህ ሰላምና እዝነት ባንቺ ላይ ይሰፈን.
የኔ ፍቅር
ዛሬ አብረሽኝ ቁረስ እንድትበዪ ምንኛ ጓጉቼ ነበር ነገርግን አለመምጣትሽን ሳይ ያለልማዴ አንቺን ከጊኔ አጥቼ አንድም ጉርሻ ሊወርድልኝ አልቻለም.
ዛሬ ያ በር ላይ ሁነሽ የምትሰቺኝ ፈግግታሽን መመልከት ምንኛ አጓግቶኝ ነበር ነገር ግን ያ ሳይሆን ቀርቶ ከፍቶኝና ቀልቤ ተሰብሮ ወጣው ...

የኔ ፍቅር
ሸይጧን አሸንፎኝ ሀቅሽን በማጉደል አጠፍቻለው ይቅርታዬን ትቀበዪኝ ይሆን »ይላል ..
🥺🥺🥺🥺
አይኖቿ በእንባ ተሞሉ ወረቀቱን እቅፍ አርጋ እያለቀሰች ሳመችው :አንተም ይቅርታ አርግልኝ የኔ ውድ ባል አለች..
ከዛ እንደ ንብ ተነስታ ቤቷን ማዘገጃጀት ጀመረች ቤቷን ሌላ አለም አደረገችው ያ የትናንቱ ቤት አይመስልም አቤት ውበት !
ለባሏም ሚወደውን ምሳ አዘጋጀች መምጫው ሰአት ሲደርስ የመዋብን ጥግ ተውባ ደስስ በሚል ፈገግታ ከበሩ ቁማ ተቀበለችው እሱም ሁኔታው አስደስቶት ለጥፋቱ ድጋሚ ይቅርታን ጠየቀ ዳግም እንደማይመለስበትም ቃል ገባ!

ባሎች ይቅርታ መጠየቅ ይልመድባችሁ !
ሚስቶች ደሞ ሳትግደረደሩ ይቅርታን ተቀበሉ!

ላጤዎች ደሞ አግቡ ዝምብላቹ የሰው ታሪክ አታንብቡ
አግቡና የናንተንም ታሪክ እንፃፍላችሁ
የገጠር ሰው ነው። የህይወት ትርጉሙን ከግብርናና ከከብቶች ጋር ያደረገ ዘላን የሆነ ሰው። ኢብኑ ዐባስ ጋር መጣና ጠየቀ
«በእለተ ትንሳኤው ማን ነው የሚተሳሰበን?»
«አላህ» አሉት ኢብኑ ዐባስ
«ወረቢል ካዕባ ድነናል።» አለ
#በየቀኑ ባነበውም በየቀኑ ይገርመኛል😊
.
#ከእለታት አንድ ቀን ነቢዩ ሙሐመድ ሰ.ዐ.ወ ዘንድ አንድ ከገጠርየመጣ ኑሮው ያልሰመረለት (ድሃ) ግለሰብ ሰሃን ሙሉ ወይን ስጦታ ያመጣላቸዋል፡፡

ነቢዩም ሰ.ዐ.ወ ስጦታውን ተቀብለው ወይኑን መብላት ጀመሩ..የመጀሪያውን ጎርሰው ፈገግ አሉ..ሁለተኛውንም ጎርሰው ፈገግ አሉ..

ግለሰቡም እጅጉን ተደሰተ..የነቢዩ ጓዶች (ሰሃቦች) ሁሌም ለነቢዩ ሰ.ዐ.ወ ስጦታ
ሲመጣላቸው ስለሚያካፍሏቸው ይህንን (ጣፋጭ) ወይን እንዲያካፍሏቸው በጉጉት ይጠብቃሉ..

የአላህ መልእክተኛ ግን ሳያካፍሏቸው እያንዳንዱን የወይን ፍሬ እየበሉ እና ፈገግ እያሉ ሁሉንም በልተው ጨረሱ.. ስጦታ አቅራቢው እጅግ በጣም ተደሰቶ..ስጦታውንም ስለወደዱለት አመስግኖ ሄደ..

አንድ የነቢይ ሰ.ዐ.ወ ጓድ (ሰሃባ) ጠጋ ብሎ ነቢዩን ጠየቃቸው ‹‹የአላህ መልእከተኛ ሆይ..ምነው ሳያካፍሉን?››

እሳቸውም ሰ.ዐ.ወ ፈገግ ብለው መለሱ ‹‹ሰወዬው መደሱቱን አይታችኋል አይደል?!..

ወይኑን ስቀምሰው በጣም ይመር ነበር..ባካፍላችሁ አንዳችሁ ግለሰቡን የሚያስከፋ እና ደስታውን የሚያደፈርስበትን ነገር እንዳታሳዩት ብየ ስለሰጋሁ ነው ብለው መለሱላቸው;;;;;

ሀቢቢ የኔ ነቢይ እናቴም አባቴም ህይወቴም ፊዳ ይሁንሎት።
Forwarded from Qidmiya Letwhid
ጥያቄ 👇እውነት /ሀሰት

1// የሀቅ መመዘኛ የሸሪአ ትምህርትን ነው
  በእኛ ላይ ደግሞ መማር  ግዴታ ነው ?
 
ትክክለኛ  መልስ ላይ ተጨማሪ ስጦታ👍
ቁረአን ልክ እንደ ጠንካራ ገመድ ሆኖ አንዱ ጫፍ ያለው ከአላህ ዘንድ ሲሆን ሌላው ጫፍ ደግሞ በእናንተ እጅ ነው። ስለሆነም አጥብቃችሁ ያዙት። እንደዚያ ካደረጋችሁ ጥመት አይነካችሁም። አትጠፉምም።
[ሃይሰሚ]

💚
https://hottg.com/Golden_Speech
https://hottg.com/Golden_Speech
Forwarded from ስለ ቀልባችን
ስለ ቀልባችን…

የዚህ ቻናል ዓላማ፦የልብ ድርቀት ለመቋቋምም ሆነ ለማከም ሰበብ ይሆን ዘንድ አላህ ያገራልንን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ከ ቁርኣን እና ከሀድስመድሐኒቱን ለመጠቆም ታስቦ የተከፈተ ቻናል ነው።

በዚህ ቻናል ላይ፦
➜ ልብ የሚያረጥቡ አጫጭር ፁሁፎች፣
➜ ከ ቀልባችን ጋር የተያያዙ የሙሓደራ ፕሮግራሞች፣
➜ ወ.ዘ.ተ....

Join Request በመንካት ቤተሰብ ሁኑ
👇👇👇👇
https://hottg.com/+CL_1nL1UHLFhZjU8
https://hottg.com/+CL_1nL1UHLFhZjU8
ዛሬ ጁምኣ ነው ሱረቱል ካህፍን እንቅራ
ያልቻለ ያልቻለ እያዳመጠ ይቅራ

እስቲ የምታዳምጡትን የምትወዱትን
ቃሪእ ሱረቱል ካህፍን ላኩልን።

በኮሜንት መስጫው ውስጥ ሼር አድርጉልን

ያማረ ፏ ያለ ጁምኣ ይሁንላችሁ 🌺
ከሙናፊቆች ተደርጎ…

ረሱል (🤍) እንዲህ ብለዋል፦

﴿مَن ترك ثَلاثَ جمعاتٍ، مِن غيرِ عذرٍ، كُتِبَ مِنَ المنافقينَ.﴾

“ሶስት ጁምዓዎችን ያለ በቂ ምክንያት የተወ ከሙናፊቆች ተደርጎ ይመዘገባል።”

📚 ሶሂህ አልጃሚዕ: 6144

====🌺
የሲራ ትምህርቶችን ለመከታተል
ይህንን ቻናል ይቀላቀሉ።

👇
~ hottg.com/ibrahim_furii
    hottg.com/ibrahim_furii
4 ማግባት
**
የሰው ልጅ ወንዱ ብዙ ሚስት ፈላጊ (polygamous) ነው። ይህ ታዲያ ተፈጥሯዊ (Biologic) ነው። አንዳንድ ወንዶች ቢያሽሞነሙኑትም ይህን የተፈጥሮ ክጃሎት እውነታ ሊቀይሩት አይችሉም። አላህ ታዲያ በሂክማው ይህን የወንድ ልጅ ፍላጎት (ማስተደርም ስለሚቸግረው) በእስልምና በ 4 ገድቦታል።

ወንድ ልጅ ጀነት ሲገባ ራሱ በብዙ ሁረል አይን ይሸለማል። ሴት ልጅ monogamous አንድ አግቢ ናት። ተፈጥሮዋ አንድ አፍቃሪ ነውና በጀነት ሽልማቷ ባሏ ነው። እንደወንዱ ለሴትም የደስታዋ ምንጭ በተፈጥሮዋ መነጽር እንጂ አሀዳዊ ይሁን አይባልም። ለ ዳልጋ አምበሳ ጥሩ ጨፌ አጭደህ ብታቀርብለት ትርጉም አልባ ነው። አምበሳ ስጋ እንጂ ሳር አይበለም። ዋናው ቁም ነገሩ ሁሉም በተፈጥሮው ልክ በጀነት ይደሰታል።

ብዙ ጊዜ በዚህ ጉዳይ አንዳንዶች ሲሸማቀቁ አንገት ሲደፉ እናያለን። እንግዲህ ካናገራችሁን ዘንድ 4 ሚስቶችን በእስልምና መፈቀዱን ስናስብ ፊጥራ ስለሆነ ኢማናችን ከፍ ይላል። አልሀምዱሊላህ እንላለን። አንዳንዶች በተመታ ሳይኮ ማስተዳደር ከቻለ ነው ሲሉንም እሱንማ ካልቻለ አንድም ሚስት አይፈቀድለትም ብለን ጸጥ እናደርጋለን።

ሌሎች ደግሞ ይመጡና የራሳቸውን phenotype ኤክስፕረስ አድርገው "የመጀመርያዋ ምን ጎድሏት" ይላሉ። በ men genotype ሲመለስ ከጎደላት ይሞላል። ሙሉ ከሆነች ደሞ በርካታ ኒእማን ማን ይጠላል ነው። አስፈቅዶ ከሆነ ይሁን የሚሉም ጨካኞችም አሉ። ይህ ስህተት ነው። አንድ ወንድ ሚስቱን የዚህ አይነት ሁኔታ ላይ ከ genetics profiሏ ውጭ ለምን ያስቸግራታል። የሱ ተፈጥሮ ጣጣን ራሱ ይወጣ።

እንደ ግል ምልከታየ ይህንን ጉዳይ ወንዶች ዞልመውታል። ትግበራው እንዲበላሽም ሴቶች አስተዋጽኦ አድርገዋል። አንድ ወንድ አንድ ሚስቱን በትክክል ማስተዳደር ካቃተው ግን መጨመሩ መፍትሄ አይመስለኝም።

ሂክማው የረቀቀ ጀሊል ተአዲን ስለፈቀደ አልሀምዱሊላህ። ይህንን ያጻፈኝ አንድ የጀነቲክስ ጥናት ሲደመድም እንዲህ ይላል።
The effective population size of females has been larger than that of males throughout human history.
ታላቅ    የምስራች  !!!

ለሰለፊያ ዳዕዋ ናፋቂዎች ለሆናችሁ በሙሉ

📌  እነሆ ዛሬ  ቅዳሜ ማታ ከ3:00 ጀምሮ
    በትዳር እና ኢስላም ቻናል ለየት ያለ ፕሮግራም
ተዘጋጅቶ  እየጠበቃችሁ ነው

🪑   « ፕሮግራሙን የሚያቀርቡት »🪑

1/ አብዱሽኩር አቡ ፈውዛ
ርዕስ أحوال يوم القيامة
2/አብዱራህማን አቡ ኡሰይሚን
ርዕስ
فتنة الدجال
የደጃል ፈትና
3/ አቡ አብዱላህ  ሳዲቅ ኢብኑ ኸይሩ

ርዕስ ♦️التَّحْذِيرُ مِنْ خَطَرِ اللِّسَانِ
ከምላስ አደጋ መጠንቀቅ!!

የፕሮግራሙ መሪ ኢብራሂም ኸይረዲን

ፕሮግራሙ በኢትዩ የሰአት አቆጣጠር  ከምሽቱ
3:00 ይጀመራል

ቀጥታ ስርጭት የሚተላለፍበት ቻናል
👇👇
https://hottg.com/tdarna_islam
https://hottg.com/tdarna_islam
እኔ ቁርዓንን አጠናሁ፣እሷም መፅሐፍ ቅዱስን አጠናች ከዛም.…

የኔ ወደ ኢስላም መቀየር የራሱ የሆነ ታሪክ አለው ከባለቤቴ ጋር የተዋወቅነው ቱርክ ውስጥ በ1996 ሲሆን በ1997 ተጋባን ሁለታችንም ስለ ሀይማኖታችን ግድ የለሾችና የራቅን ነበርን፣ በዛ ሁኔታ ለ10 ዓመታት ዘለቅን።

በድንገት አንድ ቀን ባለቤቴ ስለ እምነቷ ኢስላም መጨነቅ መጠበብ ጀመረች፣በዚህ ሁኔታ እያለች ከ2 ዓመት በኋላ በድርጊቷ መፀፀቷንና ክርስቲያን ማግባቷ ከኢስላም አንፃር ስህተት መስራቷን ነገረችኝ።

ከዚያም ወደ ኢስላም እንድገባ ታግባባኝና ትለምነኝ ጀመር እኔ ደግሞ በወቅቱ ስለ ኢስላም ምንም ግንዛቤና ዕውቀት የሌለኝ ሰው ነበርኩ፣ይሁን እንጂ እኔም ክርስቲያን ትሆን ዘንድ በውስጤ አስብ ነበር።

የአሜሪካ ሚሊታሪ አባል ነኝና ለስራ ወደ ቀጠር ኳታር ተመደብኩ በዚህም በጉዳዩ ሁለታችንም ቁጭ ብለን
ከተወያየን በኋላ እኔ ቁርዓንን ላነብና ላጠና እሷም መፅሐፍ ቅዱስን ልታነብና ከዛም ልንወስን ተስማማን።

ከዚያስ!? ከዛማ ቁርዓኑ ባነበብኩት ቁጥር እየሳበኝ እየማረከኝ መጣ፣ የቃላት ውበቱ፣ እርስ በርስ ስምም መሆኑ፣ከግጭት መፅዳቱ ወዘተ ምርኮኛው እያረገኝ መጣ። ከመወሰኔ በፊት እኔም መፅሐፍ ቅዱስን ማንበብ እንዳለብኝ ወሰንኩና ጀመርኩት፣ለስድስት ወራት አጠናሁት፣ በፍፁም ከቁርዓኑ የተለየና በግጭትና አስቂኝ ታሪኮች የተሞላ መሆኑን አጤንኩ፣ባለቤቴም ተመሳሳይ ግራ መጋባት ተፈጥሮባት እንደነበር ተነጋገርንበት።

ለሁለት ዓመት ከራሴ ጋር ክፉኛ ከታገልኩ በኋላ ኢስላም ትክክለኛው ሀይማኖት መሆኑን አረጋግጬ በ2009 ረመዳን ወር ላይ south dakota ውስጥ በሚገኝ መስጂድ ኢፍጧር ላይ ሸሐዳዬን የምስክርነት ቃሌን ለአላህ ሰጠሁ።

አሁን ኢስላምን በሚገባ ተምሬ ተግባራዊ ሙስሊም በመሆን ዑምራም አድርጊያለሁ አልሃምዱሊላህ
አላህን አብዝተን ብናመልከው እንኳን ሐቁን አላሟላንም፤ ብዙ ብናወድሰው የችሮታዉን ኢምንት አልደረስንበትም፡፡ ዘወትር ደግ ብንሠራ ሁሌም አሁንም ኃጢኣታችን ብዙ ነው፡፡ ከምሉእነታች ጉድለታችን አያሌ ነው፡፡

ቀን በተለወጠ ቁጥር ኃጢኣታችን ብዙ ነው ብለው ኢስቲግፋር እያደረጉ የሚነሱ ሰዎች አትራፊዎች ናቸው፡፡
ፃድቅ ነን፣ ፍፁም ነን፣ እንከን የለብንም ያሉት ግን ከስረዋል፡፡
ቀጥ ብለው የቆሙ የመሠላቸው ብዙዎች ወድቀዋል፡፡

አላህ ሆይ! በየቀኑ ወዳንተ መመለስን፣ መንቃትን፣ ከዝንጋቴ መባነንን ስጠኝ፡፡



©Muhammed Seid Abx
HTML Embed Code:
2024/05/15 03:44:42
Back to Top