TG Telegram Group Link
Channel: ግጥም ለሚጠማዉ
Back to Bottom
☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆

ወጣትነት በጣም ደስ የሚል፣ ያልተነካ ጉልበት ያለበት የህይወት ክፍል ነው።
ነገር ግን ወጣትነት ማለት ሱሰኝነት ማለት ይመስለኛል። አንድ ወዳጄ እንዲህ ብሎኝ ነበር ስለ ሱስ እና ወጣትነት ስናወራ "ወጣትነት እና ሱስ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ ናቸው " አለኝ እኔም ገርሞኝ እንዴት? አልኩት " አሁን ላይ ወጣት ከተባለ ሱሰኛ ነው እንደዉም አንድ ልጅ ላይ አንድ ሱስ ብቻ ካገኘሽ እሱ እግዚአብሔር የባረከው ነው ማለት ይቻላል።አብዛኞቹ የብዙ ሱሶች ባለቤት ናቸው።" .....እኔ ከዚህ ንግግር ቦኃላ በእኔ እድሜ ክልል ያሉትን ለማየት ሞከርኩ እዉነት ነው። #ሰው እንዴት በህይወት እንደሚቀልድ ሁሌም ይገርመኛል።
ስንቶቻችን በእቅድ እንኖራለን?
ስንቶቻችን ለዉጤት እንለፋለን?
ነገን ትልቅ ለመሆን አቅደን ይሆናል ነገ ትልቅ ለመሆን ነገ አይደለም መስራት ያለብን ዛሬ ነው። ነገን ዛሬ መስራት ማለት ግን ዛሬን ረስቶ ለነገ ዛሬ መኖር ማለት አይደለም አሁን የምናደርገው እያንዳንዷ ነገር ነገ አሻራ ናት
ዛሬ የዘራነዉን ነገ እናጭዳለን።
በሰፈሩት ቁና መሰፈር ያለ ነውና በወጣትነታችን እንጨዋወት በህይወት ዉስጥ አንድ ሰከንድ ጥቅም አላት ይህ እዉነት ነው። ልንሞት ስንጣጣር አንድ ተጨማሪ ሰከንድ ቢሰጠን ከልባችን ልንናገር ያሰብነውን ቢጨርስን ነበር።
ሱስን በራስ ላይ ስትፈቅድ/ስትፈቅጂ ነገህን አስብ ........አዎ ነገስ .......?

"ከሰው ልጅ ስህትት ከብረት ዝገት አይጠፋምና ከተሳሳትኩ አርሙኝ"
@TDtina

ትንቢት ዳንኤል/Tina
7/5/2013

@Getemlemitemaw
Audio
ትርጉሙ ምንድነው????

ደሞ በዚህ ዘመን
እንደሰው ስታስብ ሚዛንት ይደፋል ላጣ ላልኖረው ግን ፍትህ ይዛነፋል
በእንስሳት ነገድ በእንስሳት ህብረት
የለት ጉርሥ ማግኘት ነው ለነሱ ፍትሀት

°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
@ENUunique
👇👇👇👇👇👇
@poembyeyu👈
@poembyeyu 👈
👆👆👆👆👆👆join my new telegram channel
ልቤ ሰው ይወዳል

"ልቤ ሰው ይወዳል
ወድያው ይላመዳል
የቀረብኝ ሁሉ ወዳጅ ይመስለዋል"
እኔን ያንተ ለማድረግ የሰራኸው ሴራ
እዉነተኛ ፍቅርን በልቤ ዘራ
እኔማ መስሎኝ ...
ከቤቴ ስትመላለስ
በሁለቱ አይኖችህ እንባን ስታፈስ
ስትል ደፋ ቀና መንፈሴን ልታድስ
ምንም አልጠረጠርኩ
ይልቁንም ዉስጤን ለማሳመን ስጣጣር አደርኩ
በዉሸታሙ ገፅታህ ልቤን አታለልኩ
ልቤም አመነና ዉስጤም ተቀብሎክ
ናፍቆትም ጀመረኝ ዉስጤ ፍቅርህን አኖርክ
ያለመደብኝን መሽቀርቀር ጀመርኩ መዋብ
አቃተኝ ካንተ ላይ ቀልቤን መሰብሰብ
የዉስጤን ልነግርህ አንተን ስጠባበቅ
አንተ ግን ቀረህ አልል አልከኝ ብቅ
እራሴን ወቀስኩኝ
እራሴን ጠየኩኝ
ፍቅሩን ሊገልፅልኝ ከቤቴ ሲመላለስ
ችላ በማለት ሳልሰጠዉ መልስ
ወቶ ቀረ ፍቅሬ
ከጎኔ የለም አይመጣም ዛሬ
ዛሬ እንኳን ሳይገባኝ
አንተ በበደልከኝ እራሴን ከሰስኩኝ
አንተ ለካ ባለ ቅኔ
ለግዝያዊ ስሜት ምትመላለስ ከጎኔ
ከረፈደ ቢገባኝም
ባንተ መሰበሬ
አልቀነሰም ነበር ላንተ ፍቅሬ
አሁን ግን ገባኝ ዉሉ
ልቤ ባንተ መታለሉ
ለነገሩ ተወዉ
ልቤን ጉድ የሰራው
ሰው መዉደድ ሰው ማመኑ ነው።
የኔ ልብ የዋህ ነው ለምለም ስንክ ሳር
ሰበራዉን ችሎ ዛሬም ሳይማር
ዳግም ሰው ያምናል
ዛሬም ሰው ይወዳል
የቀረበው ሁሉ ወዳጅ ይመስለዋል
ልቤ ሰው ይወዳል

ትንቢት ዳንኤል/Tina
@TDtina
7.9.2013
ፍቅር እና ፀፀት

እግርህን ስታነሳ ከ ጎኔ ስትርቀኝ
የማደርገው ባጣ እንባ ተናነቀኝ
ተመለስ ባልልም አፌን ሞልቼ
ታች ላይ ብዬ አላስቀርህም ለፍቼ

ምክንያቱም .....!
ቃሌን በልቻለሁ ልብህን ሰብሬ
ርቄህ ሄጃለሁ እየኖርኩ አብሬ
በእቅፍህ ዉስጥ ከሚሞቀዉ ገላ
አለው በሰመመን አጥቼ መላ
አልገባህ ነገሩ መያዝ በድን
በቆይታ መስሎህ የተላመድን
አንተ እየገባህ እኔ ስወጣ
ፍቅር በሰጠኸኝ በዉሸት ስቀጣህ
አንተን ሲገባህ እኔ ተሸነፍኩ
መራቅ ስትጀምር እኔ እያቀረብኩ
በመንታ መንገድ ላይ እኔ ተዝለፍልፌ
ፍቅር ወይ ይቅርታ የቱን ይናገር አፌ
እዉነቱ የገባኝ ከቆየ ቢሆንም
ያንተ ፅናት እኔ ጋር የለም
አልቻልኩም ዉድዬ ፍቅርህን መደበቅ
ለቀሪው ህይወቴ ይሆነኝ ዘንድ ስንቅ
ሸሽጌዉ ኖራለሁ በልቤ ስር ግርጌ
አንተን ስለማለገኝህ ፈልጌ አስፈልጌ።
በገዛ ስራዬ ልቤ እየደማ
ህሊናዬ ሆኖብኛል የጦርነት አውድማ
እናማ አለሜ
ከተሰማህ ድምጼ ካለህበት ቦታ
አትመለስ ወደኔ ግን ስማኝ አንድ አፍታ
በፍቅር እና ፀፀት ተጨንቃለች ነብሴ
ይቅርታን አትንፈጋት ገብቶኛል እራሴ
ይቅር በለኝና በማግስቱ ልሙት
ሰዉነቴ መንምኖ በፀፀት ከምሞት።

(ባለፈ ድርጊት ከመፀፀት
ቸሩ አምላክ ይሰዉረን)
ትንቢት ዳንኤል/Tina
20.10.2013
10:30am
F,C @TDtina
@Getemlemitemaw
እባብ በህይወት እያለ ጉንዳንን ይበላል እባብ ሲሞት ጉንዳኖች ይበሉታል ጊዜ በማንኛውም ሰአት ይለወጣል በህይወትህ የማንንም ዋጋ አታሳንስ ምንአልባት ሀይለኛ ትሆን ይሆናል ነገር ግን ጊዜ ካንተ የበለጠ ሀያል ነው አንድ ዛፍ መቶ ሺህ ክብሪቶችን ሲሰራ አንድ ክብሪት ግን መቶ ሺህ ዛፎችን ታቃጥላለች አንድ መጥፎ ስራ ጥሩ ድረጊቶችን ታጠፉለች ዋናው ነገር ሰዎችን የምታከብር በአስተሳስብ ዘመናዊ እና ሁል ጊዜ ጥሩ አመለካከት ያለህ ሁን

መልካም ምሽት
መልካም አዳር
ሰላማቹ ብዝት ይበልልኝ👍👍👍👍
Forwarded from የልቤን በብዕር  (Birukti Yefonkowa)
እንደሷ ማን አለ

የኔን ስም ከስሟ በላይ ያከበረች
እንደ እህት አንሶባት እንደ እናት የኖረች
የኔ ሁለ ነገር እሷ ብርሃኔ..................
አለም ምጨልመኝ ስትርቅ ከጎኔ......
የእናቴ ስጦታ ሁለተኛ እናቴ.............
የሃዘኔ ተካፋይ ብርታቴ ፅናቴ............
ፍቅር ያስተማረችኝ ንፁህ ማንነቴ....
እህት የምለው ቃል ምያንሳት ምርጧ እህቴ
ከራሷ አብልጣ ስለኔ አሳቢ....................
ቁጭ አርጋኝ እንደ ልጅ ገላዬን አጣቢ......
ደስታዬን ለማንሳት ደስታዋን የጣለች.......
እንደ እህቴ ያለች ሌላ ሴት ማን አለች......

birukti

ሰናይ ቅዳሜ
ሰናይ ቀን ውዶቼ😇😇


ብሩክቲ ነኝ 😉

@yfonkowa
@saktawa
#አስተውል_ይሄ_እውነታ_ነው

•| ጠንካራ ሰው ሁን ማለት አትውደቅ ማለት አይደለም ! ወድቀህ መነሳትን ልመድ ማለት እንጂ😘
•| ዝም በል ማለት አትናገር ማለት አይደለም ! ሌሎችን ለመስማትም ጆሮ ስጥ ማለት እንጂ::
•| ሆዳም አትሁን ማለት አትብላ ማለት አይደለም ! በሰዎች ሃቅ ላይ አትለፍ ማለት እንጂ።
•| ጠላትህን ውደድ ማለት ጠላት ጥሩ ነው ማለት አይደለም ! ከጥላቻ ይልቅ ፍቅር ስለሚያሸንፍ እንጂ።
•| ደስተኛ ሁን ማለት ሁሉ ይኑርህ ማለት አይደለም ! ባለህ ነገር ደስ ይበልህ ማለት እንጂ።
°\°\°\ የህይወት ቅመም°\°\°\
🤓ዝም በል!!🤓

©ብዙ የሚያወሩ ትንሽ የሚሰሩ ናቸው። ጥቂት አዉራ ተግባርህ ግን ይብዛ። ነገሮችን በቃላት ለማስረዳት ብዙም አትጣር ምክኒያቱም ድርጊቶች ከቃላት በላይ ናቸውና።
® በወሬ ለሚበልጡህ ሰዎች አትጨነቅ፣ስራ ላይ ባዶ ናቸው። ሁሌም የሚወረወሩ ስራ ፈቶች ናቸው መገለጫቸው ደግሞ አቃቂር ማውጣት ይወዳሉ።
©ዝምታን ምረጥ አትቸኩል ማንንም ይሁን ማን በጭንቅላት ብለጥ፣ ይገባኛል ተናጋሪዎች ተሰሚ ናቸዉ ያንተ ግን ሰዓቱ ሲደርስ ስራ ይናገራል።
®ከምንም ነገር በፊት ለራስህ ክብር ይኑርህ ያኔ ለሁሉም ነገር ክብር ይኖርሃል።
©ቅድሚያ ለሚሰጠው ቅድሚያ ስጥ ነገሮችን ከማድረግህ በፊት በጥልቀት አስብ የመሰለህን ነገር ከማድረግ ወደኋላ አትበል!!

:ዝም ለጊዜው ተናገር በጊዜህ:🧐

እነዚህን ነገሮች ከፈፀምክ እርግጠኛ ነኝ ህይወት ቀለል ይላል !!
ትንቢተ ዳንኤል @TDtina
መልካም የጀግንነት ቀን💚💛❤️

ገጣሚያን፦በሱፍቃድ እና
፦የአብ
@Getem_lemitemaw
ቃል አላት ሀገሬ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
በብዙ ድምጾች ትፈርሳለች ቢባል
ሰው ቢረክስ ከሜዳ ቢጣል
ከግራ ከቀኝ ጠላት ቢበዛባት
ሀገሬ አትፈርስም ቃል አላት
በርሃቡ ግዜ በ ሰባሰባቱ
ያልጠፍች ሀገር ያሁኑማ ከንቱ! ከንቱ!
ትንሽ ትልቁ ቢያበዛ ክርክር
ብትቀጥንም እንደ ክር
በአስተሳሰብ ድህነት
አንዱ ልጅዋ ቢከዳት
ጭንቋ ቢበረታ በምጥዋ ግዜ
ምንም እንኳ ቢከባት ትካዜ
ብዙ ሰው ቢሰዋ
ብዙ ደም ቢፈስ
እንኳንስ ልትፈርስ
አትነቃነቅም!!!
ፈጣሪ አለላት ረስቶዋት አያዉቅም
እናማ ወገኔ .....
ቀኑ ቢረዝም ጭንቋ ቢበረታ
አትጣ ወኔ ክንድህን አበርታ
በፀሎቱ ስፈራ በእየ አድባራት
የዘወትር ፀሎት
አደራ ፈጣሪ እትዮጵያን ጠብቃት!!
አባቶች ቆመዉ ሳህታተት
ይማፀናሉ
የምስኪኖች አይን አሁንም
ያነባሉ
ንገሩት ለዛ ለጠላትዋ......፣

ንገሩት ለሰው በሊታ
ከሀገሬ ላይ ጉልበቱን ይግታ!!!
የ ሰማዩ ንጉሥ የምድሩ ጌታ
ዘብ የቆመላት
አትፈርስም ሀገሬ ቃል አላት!!!!!!!!


ትንቢት ዳንኤል
Tina
መስከረም 12,,,,,,,2014
የሀገር ዋርካ

አንቺ...
የሰውነት ተክል የምትሆኚ ዋርካ
ሀገር ያኖረችሽ ልቦናሽን ባርካ
ለህዝብሽ ሰቆቃ እንድቆትሚለት ዘብ
ካለምንም ዋጋ ካለምንም ገንዘብ
በአይምሮሽ ተቀርፆ የሰውነት ምስል
ይኸው እስከዛሬ
ሌላው ጥሬ ሲሆን አድርጎሻል ብስል
አንቺ...
ደግነት ያለሽ የሴቶች አምሳል
ይህን እወቂ
ጠላት ሊቀብርሽ ጉድጓድ ይምሳል
የኔ ጥያቄ?
ክፉ ወይስ ደግ የቱ ይብሳል?
"ጅምሩ ቢያምር የገፊ በደል
መሀሉ እሾህ ማለቂያው ገደል
መባቻው ቢሰምር ለዘመን ዳኛ
ሀቅ ነውና የሰው መዳኛ "
እንዳትከፊ!
በፅልመት አይንሽ ቢቆስል ታሽቶ
የጭንቅ ቀንሽ ባይነጋ መሽቶ
ተስፋ ህልምሽን ህይወት ቢነሳው
መረቡን ያዢ ቀድመሽ ከአሳው
እንዳትገፊ!
የጊዜ ቀለብ ያሰባው ነፍሳት
ዛሬ ያደለው...
የግፍ ቀረጢጥ ነገ ላይ ሊያፍሳት
በጉልቤዎች ክንድ ጥረትሽ አይቁም
ወትሮም ወረኞች
ከማማት ውጪ አንቺን አያቁም ።
#በሱፍቃድ
ለማንኛውም አስተያየት @besunet
13/11/2013
@Getem_lemitemaw
@Getem_lemitemaw
@Getem_lemitemaw
እንካፈል

በህይወት መንገድ ላይ...
መኖር ያገናኛል ደግ ነው መሰንበት
ወረተኛ ወዳጅ
ቅዳሜ ተዋውቆ ይጣላል በሰንበት
በህይወት መንገድ ላይ...
ልብ እየኮፈሰ በአፍታነት እርሾ
ሲገናኝ በፍቅር ሲለያይ በቁርሾ
ሆኖበት አመሉ
ሌላውን ለማፍራት የእጁን መጨፍለቅ
ከደስታ ምንጭ ስር አዲስ እንባ ማፍለቅ
ሆኖበት አመሉ
የሩቁን ለማንሳት የያዘውን መጣል
ወረትም አይደለ?
አንደኛው ሲነጉድ ሌላኛው ይመጣል!
እናልሽ እታለም...
ወዳጅን መስርቶ ለመኖር ሲታለም
ለነገ እንዳይናድ ዛሬ ላይ ነው መስራት
እስቲ ልጠይቅሽ
መርዶ በሌለበት ይገኛል ወይ ብስራት?
ስለዚህ እንካፈል
ከሀዘኑ ማዕድ ቢመርም ቢጥምም
አብሮ የሆኑት ሁሉ
እሱ ካልፈቀደው እህል ውሃ አይገጥምም
ስለዚህ እንካፈል
ከደስታው መሶብ ላይ ባይደርሰንም አሸን
ምንም እንኳ ኑሮ
ክንዱ ቢደቁሰን በችግር እያሸን
እኔ እስካለሁልሽ
የጭንቀትሽ ጫናው በኔ ተደግፎ
ደስታሽ ሲለመልም እንደ ቅጠል ረግፎ
እንደ ዛፍ ቅርንጫፍ
ፍቅራችን ይሰፋል ከአለም እስካለም ጫፍ
አንቺ እስካለሺልኝ
ስለ ቺስታነቴ እኔን መች ሊገደኝ
በመኖሬ እኮ ነው ልብሽ የሚወደኝ
የኔና አንቺ ህይወት
በፅናት ይኖራል ሁሉን ይታገሳል
ፍቅር በቃኝ ብሎ መች በላይ ያገሳል
እንዳሽከር ባይኖርም እንዳክተር ይነግሳል
የኔና አንቺ ህይወት
በተረት አያልፍም ታሪክን ይወልዳል
ፍቅር በሞላበት
መሰንበትን እንጂ ማን መሞት ይወዳል?

#በሱፍቃድ
@Getem_lemitemaw
Audio
ገጣሚ : የአብ
Forwarded from Gulilat
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ነፀብራቅ ሙዚቃዊ ቴአትር
በታላቁ ብሄራዊ ቴአትር በዕለተ ሰኞ በቀን 23 ከቀኑ 11 ሰዐተ በታላቅ ስነስርዓት ይመረቃል። በደራሲ አየሁ ሞላ የተዘጋጀ ሲሆን ደራሲዉ በቀደመ ስራዉ እጅጉን ተወዳጅነትን አትርፏል። ይህም ስራ አሉላ "አባ ነጋ"ይሰኛል።
ስለሀገራችን ኢትዮጵያ ጊዜያዊ ሁኔታን
#በድንቅ ትወና ብቃት
#በጥዑም ዜማ
#በልዩ አቀራረብ
ይዞላቹ በታላቁ ብሄራዊ ቴአትር እናንተን ዉድ ተመልካቾቹን ይጠበቃል።

ከተዘጋጀዉ የጥበብ ገበታ ለመካፈል፤ጠሪም አክባሪ ነዉና በቸር ለመገናኘት ያብቃን🙏
Audio
በሄድክበት እለት
@ENUunique
አንተ የኔ❤️❤️❤️
.
.

ስለ መልካም ጓደኝነትህ አመሰግናለሁ

Tina....!
@TDtina
የፍቅር ሰላምታ
ጠጉርሽን ዳብሶ በጆሮሽ ያለፈው
ነፋሱ ምን አለሽ? በመስኮት ላይ ሆነሽ፡፡
የፍቅሬን ሰላምታ ሲያስተጋቡ ይዘው ተራሮች የላኩት፤
በሩቅ የሚታዩት።
የሚወዛወዙት ቆመው በመስኮትሽ
ዛፎቹ ምን አሉ? ይንሾካሾካሉ፡፡
አይተዋል ደብዳቤ ማታ ስጽፍልሽ ፤
ይግለጹ ምሥጢሩን ልቤ መሸበሩን።
ልብስሽን ስትለብሽ ወፎች የሚዘፍኑት
የሚሉት ምንድነው? ጡቶችሽን አይተው
በፍቅርሽ ሰላምታ ልቤን እንዲያክሙት ላኪያቸው ያምጡልኝ፤
መድኃኒቱን ይስጡኝ፡፡ ኮከቦች ከሰማይ ይጠቃቀሳሉ
ውበትሽን አይተው፤
በቅርጽሽ ተደንቀው።
በሰማዩ ባሕር ጠልቀው ይዋኛሉ
ፍቅርሽን ሊይዙ
ወደኔ ሊጓዙ፡፡
ምን አለች ጨረቃ በመስኮትሽ ገብታ
ስትነካ ፊትሽን፤ ተደግፋ አልጋሽን፡፡
ልኬልሽ ነበረ የፍቅር ሰላምታ ጠይቂአት ውሰጂ፤
መልሱንም ስደጂ፡፡
የቤተ ክርስቲያን ደወሉ ዘመረ ምን ሆኖ ይጮኻል?
ሰው ይሰበሰባል።
ጉዳችንን አይቶ ገልጦ ተናገረ
እባክሽ ለፍቅር ሞተን እንቀበሮ፣
ምነው ምን ፈለገ ሲጨፍር ከበሮ?
ተነሣ የሚለኝ? የሚቀሰቅሰኝ፡፡
ፍቅርሽና ፍቅሬን በመሐረም አስሮ እንሒድ ተቃቅፈን፤
ደብቆ ይውሰደን፤
የበረረው ልቤ ካጠገቤ ጠፍቶ ምን ምሥጢር አወራ?
ደንግጦ እየፈራ፡፡
ስታንጎራጉሪ መኝታሽ ቤት ገብቶ የፍቅሬን ሰላምታ
ይስጥሽ በቀስታ፡፡ከታሪኩ ረጋሳ❤️❤️
HTML Embed Code:
2024/04/28 01:00:14
Back to Top