TG Telegram Group Link
Channel: ✝ኢትዮ ግእዝ ወ አማርኛ ቅኔ እና ሌሎችም
Back to Bottom
➊Ⓚ Thanks

🙏
Audio
🔔አዲስ_ዝማሬ

🎤አኑርልኝ_ለአፌ_ጠባቂ

🎙ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

JOIN US
🔔
🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘🔺‌‌
https://youtu.be/nMkoV-wIjTw

🤗ኦርቶዶክሳዊ ዝማሬ🤗
👳🏽‍♂ በግሩም እና በተወዳጅ ዘማሪያን
ብዙ እውቀትን ታገኙበታላችሁ ከታች ባለው ሊንክ መከታተል ትችላላችሁ።
👇🏽👇🏽
https://youtu.be/ggPuK3XXHF4
https://
         👆 ይቀላቀሉን   👆

ቴግራም ቻናል
👇👇👇
JOIN US
@kidus_yared_kidus
@kidus_yared_kidus
አንዳንድ ነጥቦች በብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ወደ ሀገራቸው እንዳይገቡ መከልከል ዙሪያ፦
1. ለዚህ አሳዛኝ ድርጊት የተቀነባበረ ሽፋን በቅርብ ሲሰጥ እንደምንሰማ የታወቀ ነው። በመንግሥት አካላት ተደርሶ የሚቀርበው ድራማና ዶክመንተሪ አያልቅምና ያልሠሩትን ወንጀል ሲያሸክሟቸውና ሲያጥላሉዋቸው እንሰማ ይሆናል። ስለዚህም ከሚዲያ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ልሳን የሆኑ ሚዲያዎችን ብቻ እንከታተል።
2. መንግሥት ይህን መሰል አንገት ሰባሪና ድፍረት የተሞላበት ድርጊት ሲፈፅምም ብፁዕነታቸው ያሉበትን ኃላፊነት ከግምት አላስገባም። ክብራቸውን የሚወክሉትን ቤተ ክርስቲያንና ሕዝባቸውን አላከበረም። በዚህ ጸያፍ ድርጊቱ እርሳቸውን ብቻ ሳይሆን መላውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አማኝን እንዳሳዘነ መታወቅ አለበት።
3. ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ፓትርያርኩን ሸክም ጎንበስ ብለው የሚሸከሙ አባት ናቸው። የዛሬው የመንግስት ድርጊት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስን ከሜዳው በማግለል የቅዱስ ሲኖዶስን ማዕከላዊነት የመናድ ሙከራ ነው።
4. ብፁዕነታቸው በእምነታቸው የማይደራደሩ ታላቅ አባት ሲሆኑ እርሳቸውን ወደ ሀገራቸው እንዳይገቡ የማድረግ ርምጃ የቤተ ክርስቲያንን በር የበግ ለምድ ለለበሱ ተኩላዎችና ለእንደ ልቡዎች ክፍት የማድረግ ዕቅድ አካል ነው። ከዚያም ውጪ ሌሎች ውጪ የሚኖሩ አበው ብፁዓን አባቶችንም አፍ የማስያዣ አካሄድ ነው።
5. በሌላ በኩል በውጪ ያሉ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ቁጣቸውን ማሳደር አለባቸው። ምክንያቱም መንግሥትም ሆነ ሕገ ወጥ አካላት በተለያዩ ሚዲያዎች በኩል ይህን ነገር እያራገቡ ጫና ፈጥረው ሌላ ሲኖዶስ እናቋቁም የሚል ሀሳብ እንዲፈጠር መሥራታቸው አይቀርምና በዚህ በኩል ረጋ ብሎ  መጠንቀቅ ተገቢ ነው። ተተኪ ጸሐፊ ይመረጥ የሚል ሤራ እንዳይሸርብም ነቅቶ መጠበቅና መሥመር ማስያዝ እንደሚገባው ሳይረሳ!!
6. ይህ ድርጊት ቤተ ክርስቲያንን ለመከፋፈል የታሰበ እቅድ ነው። ስለዚህም እንደ ምእመን በበለጠ የቤተ ክርስቲያን አንድነት ላይ ማተኮርና ቤተ ክርስቲያናችንን በንቃት መጠበቅ አለብን።
7. ይሄ ጉዳይ መሥመር እንዲይዝ የሚያደርጉ አባቶችን በሚያስፈልጋቸው ሁሉ ማገዝና ትዕዛዛቸውንም እንደ ልጅ መፈጸምም ይገባናል።
ልዑል እግዚአብሔር ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅልን

#ኢንፈርህሞተ
#ሞትንአንፈራውም
ብርሃኑ ተ/ያሬድ
Forwarded from 🔵ናታኒም ፕሮሞሽን🔵 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
ናታኒም ፕሮሞሽንም ዓላማችን መፈሳዊ ሚዲያዎችን በመንፈሳዊነት እናብዛ ብለን በርከት ያሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ቻናሎች መዝግቦ ለምእመናን  እንዲዳረሱ  ፕሮሞት እያደርገ ይገኛል ።
  በፍጥነት ለማሳደግ አሁኑኑ ያስመዝግቡ
      Wave ፕሮሞሽን በፎልደር ለመዝገብ
10k በላይ ኦርቶዶክሳዊ ቻናል በዚህ አናግሩኝ👉 @Mane_tekel
Forwarded from 🔵ናታኒም ፕሮሞሽን🔵 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
ናታኒም ፕሮሞሽንም ዓላማችን መፈሳዊ ሚዲያዎችን በመንፈሳዊነት እናብዛ ብለን በርከት ያሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ቻናሎች መዝግቦ ለምእመናን  እንዲዳረሱ  ፕሮሞት እያደርገ ይገኛል ።
  በፍጥነት ለማሳደግ አሁኑኑ ያስመዝግቡ
      Wave ፕሮሞሽን በፎልደር ለመዝገብ
10k በላይ ኦርቶዶክሳዊ ቻናል በዚህ አናግሩኝ👉 @Mane_tekel
Forwarded from 🎤ድምፀ ተዋህዶ🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
" " " " ኢየሱስ ማን ነው?" " " "
     ❖ ❖ ❖
"እናንተስ እኔን ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ?"
(የማቴዎስ ወንጌል 16:15)

ይሄ ጥያቄ ከክርስቶስ ለሐዋርያቱ የቀረበ ቢሆንም ህያው ሆኖ ይሰራልና ለእኛም የተጠየቀ ነው!
ስለዚህ እናንተ ክርስቶስን ማን እንደሆነ ትላላችሁ? የሚለውን ጥያቄያችንን ለልባችሁ በመተው በዚህ ተከታታይ ፅሁፍ የኢየሱስ ክርስቶስን ማንነት ከመጽሐፍ ቅዱስ እና ከኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ አንጻር እንማማራለን።
ኢየሱስ ክርስቶስ የክርሰትናችን መስራች የሃይማኖታችንም ራስ በመሆኑ እርሱን በሚገባ ማወቅ ከእኛ ከክርስቲያኖች ይጠበቃል። እርሱን ማወቃችንም ለሚከተሉት ዋና ዋና ተግባራት ይረዳናል።

1. እርሱን አውቀን በህወታችን ያለውን ድርሻ ተረድተን ለእርሱ እንድንታዘዝና በአግባቡ እንደናገለግለውና እንድናመልከው

2. የምናውቀውን ለማያውቁትና ላልተረዱት በሚገባ ለማስረዳትና ወደ እውነተኛው የክርስቶስ ማንነት እንዲመጡ ለማድረግ

3. በዘመናች ኢየሱስ ክርስቶስን በተመለከተ ሰዎች ያላቸው አስተሳሰብ አራምባና ቆቦ ስለሆነ ጥያቄዎችንም ስለሚጠይቁን ለእነርሱ መልስ ለመስጠት ነው።

4- ዋናው ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስን ማወቅ የዘለዓለም ህይወት ነው!! የሐ17-2፤4

ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም በተመላለሰበት ጊዜ ሰዎች አውቀውት ተረድተውት እንደሆነ ይጠይቅ ነበር። ለምሳሌ በፊሊጶስ ቂሳርያ ሐዋርያቱን ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደሆነ ይሉታል ብሎ ጠይቋቸው ነበር። ሐዋርያቱም ክብር ይግባውና ሰዎች የሚሉትን ተርከውለታል ።ማቴ 16፡18፤ማር 8 ። በዚያ ዘመን የሚኖሩ ሰዎች ክርስቶስን ኤልያስ ነው፤ሙሴ ነው፤ ዩሐንስ ነው፡ ኤርሚያስ ነው ከነዚህም ካልሆነ ከነቢያት አንዱ ነው ይሉ ነበር። ሌሎቹም
ጋኔል አለበት ብለውታል የሐ 10፤20 ኢየሱስ ክርስቶስ ግን የነቢያት አምላክ ነበር ሰዎች ባይረዱትም ቅሉ።
ሌሎቹም ካስተማራቸው ትምህርት የተነሳ ይህ ማን ነው የጸራቢው የየሴፍ ልጅ የማርያምስ ልጀ አይደለምን? ወንድሞቹ .. እህቶቹም በእኛ ዘንድ አይደሉምን? እያሉ ተሰነካከሉበት።ሉቃ 4፤16-22
ሆኖም ሁሉም ባያውቁትም ሐዋርያቱ ግን በሚገባ ተረድተውት ነበር ለዚህ ነው ሐዋርያው ቅዱሰ ጴጥሮስ አንተ የህያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ ብሎ የመለሰው። ቅዱሰ ጴጥሮስም አንተ የህያው እግዚአብሔር ልጀ ነህ በማለቱ ብጹዕ ተባለ፤የቤተ ክርስቲያን አለት እንዲባል ሆነ።

ወገኖቸ በዛሬው ጊዜ ኢየሱስን አንዱ ፍጡር/ነብይ/ ሌላው መልአክ ሌላም ሌላም እያሉ ይሳለቁበታል በእርግጥ እኛ አውቀነው ይሆንን?

ለመሆኑ ይህ ኢየሱስ ማን ነው?
ኢየሱስ ክርስቶስ ትንቢት ሳያናግር ሱባኤ ሳያስቆጥር እንዲሁ ከሰማያት የወረደ አይደለም። ይልቁንም ትንቢት አናግሮ ሱባኤ አስቆጥሮ ከሰማየ ሰማያት ወረደ እንጂ። ኢየሱስ ክርስቶስ ሱባኤ አስቆጥሮ ቢመጣም እንኳን ሱባኤውን እንቆጥራለን የሚሉ
አይሁድ ማወቅ አልቻሉም እርሱ የመጣው በደካማ ስጋ ነበርና።

ዛሬም ሰዎች ክርስቶስ በደካማ ስጋ መምጣቱን ተመልክተው ብዙዎች እርሱን በሚገባ ለማመንና ለማዎቅ አቃታቸው። ክብር ለእርሱ ይሁንና እርሱ ኢየሱስ ማን ነው። እርሱ የማሰናከያው ድንጋይ እርሱ የማዕዘኑ ድነጋይ፤ ያ ከአለት የፈሰሰው እና በጥም
የነበሩትን በበረሃ የተቃጠሉትን ያረካው ኢየሱስ ክርስቶስ ማን ነው?

ኢየሱስ በብሉይ ኪዳን፦

           ይቀጥላል............
Forwarded from 🎤ድምፀ ተዋህዶ🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
ህይወትህን በሙሉ ለምድራዊ ነገር አሳልፈህ ከሰጠህ ምድር መቃብርን ትሰጥሃለች፤ ነገር ግን ህይወትህን ለመንግስተ ሰማያት አሳልፈህ ብትሰጥ ግን መንግስተ ሰማያት ዙፋንን ትሰጥሃለች።
ምክረ አበው
Forwarded from 🎤ድምፀ ተዋህዶ🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
ህይወትህን በሙሉ ለምድራዊ ነገር አሳልፈህ ከሰጠህ ምድር መቃብርን ትሰጥሃለች፤ ነገር ግን ህይወትህን ለመንግስተ ሰማያት አሳልፈህ ብትሰጥ ግን መንግስተ ሰማያት ዙፋንን ትሰጥሃለች።
ምክረ አበው
Forwarded from 🎤ድምፀ ተዋህዶ🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
ባንተ ነው ክርስቶስ

ይህ ሁሉ ወፈ ሰማይ በልቶ የሚያድረው ባንተ ነው። ይህ ሁሉ ሆደ ባሻ ጨርቁን ጥሎ ያልሄደው፣ ይህ ሁሉ ምስኪን እንባው የሚታበሰው ባንተ ነው። አፍቅሮ ጥላቻን፣ አምኖ ክህደትን የሚያስተናግደው እንደገና ወደ ቀልቡ የሚመለሰው ባንተ ነው። ለቤተ ሠሪው ምሰሶውን የምትይዝለት ፣ ጠባቂውን የምትጠብቅለት፣ ለአፍቃሪው ፍቅር የምትሰጠው፣ ሰውን ለልጁ ደግ ያደረግኸው ...ይህ ሁሉ ባንተ ነው። በአደጋ ውስጥ በሰላም የምጓዘው፣ በድካም ሕይወት ዛሬም አለሁ የምለው ባንተ ነው። ድሀ አደጉ የማይሞተው፣ ጎዳና የወደቀው እንቅልፍ የሚያገኘው ባንተ ነው። የጨለመው ቀን እየፈካ፣ ተስፋ እንደገና የሚያበራው ባንተ ነው። ያለአጥር የምጠበቀው፣ ያለ በር በምከለለው አማኑኤል ባንተ ነው ። አንተ የሰጠኸኝን ማንም አይነጥቀኝም፣ አንተ ከልክለኸኝ ማንም አይሰጠኝም። ይህንንም የምናገረው ባንተ አቅም ነው። የሰጠኸኝን ዘመን ለበረከት አድርገው!


ይቱብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ🙏
https://youtu.be/No-mmpKMgN0
https://youtu.be/No-mmpKMgN0
Forwarded from 🎤ድምፀ ተዋህዶ🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
መታዘዝ

"አቤቱ ጌታ ሆይ:- አንተ ወደዚህ ዓለም መጥተሃል::ለእናትህ ለቅድስት ድንግል ማርያምና ለቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ ትታዘዝላቸው ነበር:: አንተ ራስህ ፈጣሪ ሆነህ ሳለህ ለፈጠርሃቸው ሰዎች በፍቅር ትታዘዝላቸው ነበር:: አንተ እኮ ሰማይና ምድር የሚታዘዙልህ አምላክ ነህ! መታዘዝህ ሥልጣንህን አያጠፋውም:: መታዘዝን በእኔ ውስጥ ቀድስ  ከመታዘዝ ሩጬ እንዳላመልጥ ከአንተ ጋር እሰረኝ:: እኔ በአንተ መታዘዝ ውስጥ ተካፋይ መሆኔ ይታወቀኝ ዘንድ ትእዛዝህን እቀበላለሁ:: በእኔ ዐይኖች ፊት እንደመገረፍ ስለሚቆጠር መታዘዝ ለእኔ መራራ ነው:: ከአንተ ጋር ከሆንኩኝ ግን እጅግ ጣፋጭ ነው:: የአንተን የመታዘዝ ልምድ ለእኔ አስተምረኝ፣አለማምደኝ አድለኝም:: ይህን ካደረግህልኝ እውነተኛ ትዛዥ የሆንኸው አንተን በእኔ ውስጥ ስትሰራ እመለከታለሁ::ጽድቅን ለመፈፀም ታዛዥ የሆንኸው አንተ ለእኛ ምሳሌ ነህ::" /ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ/

በYoutube subscribe አድርገው ያግኙን :-


https://youtu.be/E1beypZbKX4
https://youtu.be/E1beypZbKX4
Forwarded from 🎤ድምፀ ተዋህዶ🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን !!!

እንኳን ለቅድስት ሥላሴ  በዓል  እንዲሁም ለሌሎች ቅዱሳን መታሰቢያ በዓል  በሰላም በጤና አደረሳችሁ፤ አደረሰን።

የአብርሐምን ቤት የባረኩ ሥላሴ እኛንም በህይወታችን በኑሮዋጭን በአገልግሎታችን  በትዳርአችን በትምርታችን በሥራችን ይባርኩን ።

ሥሉስ ቅዱስ ለሚታምን ሁሉ እምነትን በረከትን ሀገራችን ኢትዮጽያን ሰላም ያድርጉልን አሜን ::

#መልካም እለተ  ይሁንልን

     #መልካም ቀን

 
Forwarded from 🎤ድምፀ ተዋህዶ🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
#ደጉ እና ሩሩህ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ወርሀዊ በዓል እንኳን አደረሳቹ።

"ቅዱስ ሚካኤል ኾይ"

እንደ ፀሐይ ሥነ ጸዳል የሚያንጸባርቁ በሰማይ ላይ ለሚንበለበሉ አክናፎችኽ ሰላም እላለኹ

የእግዚአብሔር ልዩ መልእክተኛ ሚካኤል ኾይ ከላይ ከሰማይ ተመልክተኽ በምትመጣበት ጊዜ ኹሉ በሲዖል የሚኖሩ ግዞተኞች ሚካኤል ኾይ መጣኽልን ደረስክልን እያሉ ደስታቸውን ይገልጻሉ።"

#መልክአ ቅዱስ ሚካኤል

" የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።"

#መዝሙረ ዳዊት 34:7፤)

"በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል፤ ሕዝብም ከሆነ ጀምሮ እስከዚያ ዘመን ድረስ እንደ እርሱ ያለ ያልሆነ የመከራ ዘመን ይሆናል፤ በዚያም ዘመን በመጽሐፉ ተጽፎ የተገኘው ሕዝብህ ሁሉ እያንዳንዱ ይድናል። "

#ትንቢተ ዳንኤል 12:1

" የፋርስ መንግሥት አለቃ ግን ሀያ አንድ ቀን ተቋቋመኝ፤ እነሆም፥ ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ፤ እኔም ከፋርስ ነገሥታት ጋር በዚያ ተውሁት። "

   #ትንቢተ ዳንኤል 10:13

" ነገር ግን በእውነት ጽሑፍ የተጻፈውን እነግርሃለሁ፤ በዚህም ነገር ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር ማንም የሚያጸናኝ የለም።
"
#ትንቢተ ዳንኤል 10:21፤)ዐ

"የመላእክት አለቃ ሚካኤል ግን ከዲያብሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ ስለ ሙሴ ሥጋ ሲነጋገር። ጌታ ይገሥጽህ አለው እንጂ የስድብን ፍርድ ሊናገረው አልደፈረም።"

#የይሁዳ መልእክት 1:9

✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞
Forwarded from 🎤ድምፀ ተዋህዶ🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
አክተሩ
1ኛ ሸሚዝ አልቀየረም
2ኛ  ፍሪዝ ነው ጸጉሩ መኖክሴ ፍሪዝ አያረግም
3ኛ የኦርቶዶክስ መምህር አይደለም
4ኛ ፓስተሩ ይህንን ድራማ  ሲሰራ ከባድ ስህተት ሰርቶል።

በውሸት የሚነግስ ሴጣን እንጂ ጌታ የለም ።

“እኛስ ያየነውንና የሰማነውን ከመናገር ዝም ማለት አንችልም አሉአቸው።”

  — ሐዋርያት 4፥20

“እውነት እውነት እልሃለሁ፥ የምናውቀውን እንናገራለን ያየነውንም እንመሰክራለን፥ ምስክራችንንም አትቀበሉትም።”
 
— ዮሐንስ 3፥11
Forwarded from 🎤ድምፀ ተዋህዶ🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
ፆመ ነነዌ  ከሰኞ - ዕሮብ (ከየካቲት 18 -20 )

የነነዌን ህዝብ ጸሎት የሰማ አምላክ የኢትዮጵያንም ህዝብ ልመና ለቅሶ ችግር ይሰማ ዘንድ ቅዱስ ፍቃዱ ይሁን አሜን፡፡

           ፆመ ነነዌ

ዮናስ ማለት 'ርግብ: የዋህ' ማለት ሲሆን ከ12ቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ ነው::በሰራፕታ ተወልዶ ያደገው ነቢዩ በልጅነቱ ታሞ ሙቶ ነበር:: ታላቁ ነቢይ ኤልያስ ግን 7 ጊዜ ጸሎት አድርጐ ከሞት አስነስቶታል::እናቱ የሰራፕታዋ መበለትም ደግ ሴት ነበረች::
    ቅዱስ ዮናስ በእድሜው ከፍ ሲል የቅዱስ ኤልያስ ደቀ መዝሙር ሆነ:: የነ ኤልሳዕና አብድዩም ባልንጀራ ነበረ:: ነቢየ እግዚአብሔር ኤልያስ ካረገ በሁዋላ: ቅ.ል.ክርስቶስ በ፰፻ ዓመት አካባቢ የነነዌ ሰዎች ኃጢአት ከመሥፈርቱ በማለፉ የእግዚአብሔር ቃል ወደ አማቴ ልጅ ወደ ዮናስ መጣ::

  ሒድና ለነነዌ ሰዎች ንስሃን ስበክላቸው" አለው:: ከነቢያት ወገን ከሙሴና ከዳዊት ቀጥሎ የዮናስን ያህል የዋህ ገራገር የለምና እንቢ አለ ሰምቶ ዝም አለ:: እግዚአብሔር እየደጋገመ ሲናገረው ግን "እንዲህ የሚዘበዝበኝ ከፊቱ ብቀመጥ አይደል!" ብሎ ወደ ተርሴስ ኮበለለ።
     ወገኖቼ አንድ ነገርን ልብ እንበል:: እንኩዋን ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዮናስ እኛ ክፉዎችም ከጌታ ፊት መሸሽ እንደማይቻል ጠንቅቀን እናውቃለን:: ታዲያ ለምን ሸሸ ቢሉ:- ጥበበ እግዚአብሔር በውስጡ ስለ ነበረበት ነው::

   ምክንያቱም ዮናስ በአሣ አንበሪ ሆድ 3 ቀን ሌሊት ኖሮ: ሙስና ጥፋት ሳያገኘው መውጣቱ ለጌታ ትንሳኤ ጥላ ምሳሌ ነው:: ለዚህም ምስክሩ ራሱ ጌታችን ነው:: "ወበከመ ነበረ ዮናስ ውስተ ከርሠ አንበሪ ሠሉሰ ዕለተ ወሠሉሰ ለያልየ: ከማሁ ይነብር ወልደ እጉዋለ እመ ሕያው ውስተ ልበ ምድር ሠሉሰ ዕለተ: ወሠሉሰ ለያልየ" እንዲል:: ማቴ. 12:39

   ቅዱስ ዮናስ በገንዘቡ ዋጅቶ ወደ መርከብ በገባ ጊዜ ታላቅ ማዕበል ሆነ:: የእምነት ሰው ነውና እንዲያ እየተናወጡ እርሱ በእርጋታ ተኝቷል:: እነርሱ ግን ቀስቅሰው ቢጠይቁት እጣ ወድቆበታልና የእኔ ጥፋት ስለ ሆነ ወደ ማዕበሉ ጣሉኝ" አላቸው::
     እያዘኑ ቢጥሉት ታላቅ ጸጥታ ሆነ:: እነዚያ አሕዛብም እግዚአብሔርን በመስዋዕትና በስዕለት አከበሩ:: ዮናስ ግን በማዕበልና በአሣ አንበሪ ሆድ ውስጥ ለ3 ቀናት ጸለየ:: አሣ አንበሪው በ3ኛው ቀን ወደ ነነዌ ተፋው::ቅዱሱም "እስከ ሠሉስ ዕለት ትትገፈታእ ነነዌ ዐባይ ሃገር" እያለ ንስሃን ሰበከ::

የነነዌ ሰዎች ኃጢአታቸውን አምነው ቢጸጸቱ ከሰማይ ወርዶ ከደመና ደርሶ የነበረው የእሳት ማዕበል ተመልሶላቸዋል::
    የነቢዩ ትንቢት ግን አልቀረምና ታላቁዋ ነነዌ ከ፫፻ ዓመታት በኃላ ጠፍታለች:: ቅዱስ ዮናስ ግን በቀሪ ዘመኑ ፈጣሪውን እያገለገለ ኑሯል:: ጠቅላላ እድሜውም 170 ዓመት ነው::

አምላከ ቅዱስ ዮናስ እድሜ ለንስሃ: ዘመን ለፍስሃ አይንሳን:: ከበረከቱም ይክፈለን::
በጾመ ነነዌ ስለ ሃገርና ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት መጸለይ ይገባል::
  ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል:: ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም:: ዮናስ በአሣ አንበሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ: እንዲሁ የሰው ልጅ(ጌታችንን) በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል:: የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነስተው ይፈርዱበታል:: በዮናስ ስብከት ንስሃ ገብተዋልና:: እነሆም ከዮናስ የሚበልጥ ከዚህ አለ::
                    ማቴ. 12:39
ለሀገራችን ሰላም ለምድራችንም በረከትን ያድልልን!!
       ወስብሐት ለእግዚአብሔር
        ወለ ወላዲቱ ድንግል
         ወለመስቀሉ ክብር

https://hottg.com/dmse_tewado
Forwarded from 🎤ድምፀ ተዋህዶ🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
​​"4 ተገድለው 1 ጠፍተዋል፤ ገዳሙን እና እኛን ለማዳን እነሱ ተሰው፤ የእኛንም በደል እነሱ ከፈሉ"
የደብረ ከዋክብት ዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አባቶች
++++++++++++++++++++++++++++++

የገዳሙን መጋቤ እና ዋና ጸሐፊ ጨምሮ የደብረ ከዋክብት ዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም 4 መነኮሳት በታጣቂ ኃይሎች መገደላቸውን ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን የደረሰው መረጃ ያመላክታል።

ከገዳሙ በስልክ ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው የካቲት 12/2016 ዓ.ም የታጠቁ ሰዎች ወደ ገዳሙ በመግባት ሁለት መነኮሳት መውሰዳቸውን እነሱ ይመለሳሉ ብለው ሲጠብቁ በማግስቱ የካቲት 13/2016 ዓ.ም ታጣቂዎቹ ድጋሚ መጥተው ለውይይት እንፈልጋችኋለን በማለት 3 መነኮሳትን ወደ "ጂዳ ተክለ ሃይማኖት" ወስደዋል ብለዋል።

መነኮሳቱ "ለውይይት" ሲባሉም "ችግር የለውም እናንተ አባቶች እዚህ ቆዩ እኛ አነጋግረናቸው እንመጣለን፤ ተረጋጉ" ብለው ታጣቂዎቹን ተከትለው ከገዳሙ ሂደዋል።

ቀኑን ሙሉ ስልካቸው ክፍት እንደነበረ አመሻሽ ማግኘት ባለመቻላቸው ተጨንቀው የአካባቢውን ምእመናን ሲያጠያይቁ 4ቱ መገደላቸውን እንደነገሯቸው አንደኛው አባት ግን ተለቀዋል ቢባልም እስካሁን ያሉበት እንዳልታወቀ አባቶቹ ለጣቢያችን በእንባ ተናግረዋል።

በታጣቂዎቹ የተገደሉት አባቶች

፩ አባ ተክለ ማርያም አሥራት (የገዳሙ መጋቤ)

፪ አባ ኪዳነ ማርያም ጥላሁን (የገዳሙ ዋና ጸሐፊ)

፫ አባ ገብረ ማርያም አበበ (ቀዳሽ ካህን፣የመጽሐፍ መምህርና የገዳሙ አስተዳደር አባል)

፬ ባህታዊ ኃ/ማርያም ስሜ (የገዳሙ የአስተዳደር አባል)
ሲሆኑ
እስካሁን ያሉበት ያልታወቀው ደግሞ አባ ኪዳነ ማርያም ገ/ሰንበት ናቸው።

ገዳሙ በተደጋጋሚ በታጠቁ ሰዎች ዐይነተ ብዙ ጥቃት እንደሚደርስበት ነገር ግን መፍትሔ እንዳላገኙ በመግለጽ የአሁኑ ጥቃት ግን በቃላት የማይገለጽ ነው ብለዋል።

"ገዳሙን እና እኛን ለማዳን እነሱ ተሰው፤ የእኛንም በደል እነሱ ከፈሉ፤ ጻድቁን አገልግዬ እዚሁ አርፋለሁ ሲሉ ደመ ከልብ ሆነው ዐፈራቸውንም ሳይቀምሱ ቀርተዋል" ሲሉም መረጃ የሰጡን አባቶች በከፍተኛ ሐዘን ገልጸዋል።
HTML Embed Code:
2024/05/31 23:38:22
Back to Top