መታዘዝ
"አቤቱ ጌታ ሆይ:- አንተ ወደዚህ ዓለም መጥተሃል::ለእናትህ ለቅድስት ድንግል ማርያምና ለቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ ትታዘዝላቸው ነበር:: አንተ ራስህ ፈጣሪ ሆነህ ሳለህ ለፈጠርሃቸው ሰዎች በፍቅር ትታዘዝላቸው ነበር:: አንተ እኮ ሰማይና ምድር የሚታዘዙልህ አምላክ ነህ! መታዘዝህ ሥልጣንህን አያጠፋውም:: መታዘዝን በእኔ ውስጥ ቀድስ ከመታዘዝ ሩጬ እንዳላመልጥ ከአንተ ጋር እሰረኝ:: እኔ በአንተ መታዘዝ ውስጥ ተካፋይ መሆኔ ይታወቀኝ ዘንድ ትእዛዝህን እቀበላለሁ:: በእኔ ዐይኖች ፊት እንደመገረፍ ስለሚቆጠር መታዘዝ ለእኔ መራራ ነው:: ከአንተ ጋር ከሆንኩኝ ግን እጅግ ጣፋጭ ነው:: የአንተን የመታዘዝ ልምድ ለእኔ አስተምረኝ፣አለማምደኝ አድለኝም:: ይህን ካደረግህልኝ እውነተኛ ትዛዥ የሆንኸው አንተን በእኔ ውስጥ ስትሰራ እመለከታለሁ::ጽድቅን ለመፈፀም ታዛዥ የሆንኸው አንተ ለእኛ ምሳሌ ነህ::" /ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ
@dmse_tewado
>>Click here to continue<<
![](https://photo.hottg.com/u/cdn4.cdn-telegram.org/file/IgTQrmxXLbcWeEFpDu5oxj-0x21QwBOKIhUHPv7T6ZaGbvdA9b1QzP12_hMeH04eYEX30C8kTlj0yGYOW-7CYlt8OoWxYg5rUJB8VOqxqaSMUrDIokNhESEAdgdoxBdFDj5R8z2DthUvoAWfnCCxfGd2brUQ3k5sjZ5pS9xCpphz9SE8ouwP8mYelc2Xs4BaffTfPLSHjSYwRf1IjMHA-121wJZLkRvHLhdSxP3kRmKQFvjP9Rf8wPLdE4ImFdGO6szJPFhP5h7QChBw6quqFsuk2pKPvwwmSOUgVNC6XEB-iU6CEit2cbLjpEaIrDPUzLTBcCXKe-zbzqjTF2rGWw.jpg)