TG Telegram Group Link
Channel: 🇪🇹 ኢትዮ Students
Back to Bottom
እስራኤል ሌሊቱን ኢራንን ስትመታ አድራለች‼️

በዚህም የኢራን በርካታ የጦር ጀነራሎችና የኢራን የኑክሌያር ጣቢያዎች ተመተው አድረዋል። ኢራን ከፍተኛውን የጦር ጀነራል ሁሴን ሳሊሚም ጭምር መገደላቸውን አለም አቀፍ ሚዲያዎች ዘግበዋል።
እስራኤል ጥቃቱን የፈፀመችው በአምስት ዙር ነው። እስራኤል እና ኢራን ወደ ሙሉ ጦርነት መግባታቸው አይቀሬ ሆኗል። ኢራን እስራኤል ከባዱን ዋጋ ትከፍላላች የሚል ማስጠንቀቂያ ስትሰጠ እስራኤል በበኩሏ ጥቃቱ ሊቀጥል እንደሚችል አጠንቅቃለች።

እስራኤል ማንንም አልሰማም ብላለች አለም ወደከፋ ጦርነት መግባቷ አይቀሬ እየሆነ ነው 🙄

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
አሁን በወጣ መረጃ የኢራን የጦር ሃይሎች ዋና አዛዥ በእስራኤል ጥቃት መገደሉን የኢራን ምንጮች አረጋገጡ

የኢራን ይፋዊ የዜና ማሰራጫዎች የጦር ሃይሎች ዋና አዛዥ ሞሃመድ ባገሪ በእስራኤል መገደላቸውን አስተባብለው የነበረ ቢሆንም አሁን ግን የጦር አዛዡ መገደሉን በርካታ ምነጮች እያረጋገጡ ይገኛሉ ሲል አልጀዚራ አስነብቧል።

ነገር ግን የቴህራን መንግስት በይፋ ያለው ነገር የለም።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
ኢራን ገና መዓት ይዘንብባታል:-ትራምፕ‼️

ይህ የእስራኤል ጥቃት ጅማሮ ነው፣እስራኤል በሚቀጥሉት ቀናት ከዚህ የባሰ ከባድ ጥቃት ትፈፅማለች ብለዋል።
ምርጡንና እጅግ የረቀቀ አውዳሚ የጦር መሳሪያ አምራች¹ ሃገር አሜሪካ መሆኗን ለማስታወስ እወዳለሁ። በአሜሪካ እጅ የሚገኙ ምርጥ የጦር መሳሪያዎች በእስራኤል እጅ ውስጥ ይገኛሉ፤ እንዴትና መቼ መጠቀም እንዳለባቸውም ያውቃሉ።
ኢራን ከአሜሪካ ጋር የኑክሌያር ጣቢያ እንዳይኖራት ስምምነት ለመፈፀም ትክክለኛው ጊዜ አሁን ነው ብለዋል።
"ካልሆነ ግን የኢራን ኢምፓየር ታሪክ ሊሆን ይችላል"ብለዋል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
ሰበር: እስራኤል ከኢራን የተወነጨፉ ሚሳኤሎችን መመልከቷን አስታወቀች

የእስራኤል ጦር ከኢራን የተወነጨፉ ሚሳኤሎችን በራዳሩ ላይ ከተመለከተ በኋላ እስራኤላውያን በተከለሉ ቦታዎች መቆየት አለባቸው ሲል አስታውቋል።

"ከተከለለው ቦታ መውጣት የሚፈቀደው ግልጽ መመሪያዎችን ከተላለፉ በኋላ ነው" ሲል በወታደራዊው መግለጫ ይፋ አድርጓል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
🛑 አለም ወደለየለት እልቂት እያመራች ትገኛለች ።

እየተወሳሰበ የመጣው የቀይ ባህር ጉዳይ‼️
ከደቂቃዎች በፊት  የኢራን ብሔራዊ ቴሌቪዥን በአወጣው  መረጃ  ኢራን ኢትዮጵያን በቀጥታ አደጋ ውስጥ ሊከት የሚችለውን እርምጃ ወስዳለሁ ስትል ማስጠንቀቂያ ሰጥታለች።
በዚህም መሰረት ኢራን "እስራኤልን እንዳላጠቃ ለመከላከል የሚሞክሩትን   አሜሪካ ፣ዩኬ፣ የኢዩ ሀገራትን  ወታደራዊ ጣቢያዎችንና መርከቦቻቸውን  በቀጥታ ማጥቃት እጀምራለሁ"  ስትል  ይፋዊ  መግለጫ የሰጠች ሲሆን ፤እንደሚታወቀው  ሁሉም የተጠቀሱት ሀገራት የወታደራዊ ጣቢያና ባህር ሃይላቸው በአንድ ላይ ተከማችተው  የሚገኙት እና የሚተላለፉባት የበሬ ግንባር የምታክለውና የ120 ሚሊየን ኢትዮጵያዊያን  ህልውና የኪራይ ወደባችን  በሆነችው ጂቡቲ  ነው። 
ኢራን እንዳለችውምበ ጅቡቲ የሚገኘውን የአሜሪካ የጦር ቤዝ  ለማጥቃት በቀጥታ የጦር ቀጠና ምታደርጋት ከሆነ  ያለ አንዳች ጥርጥር ለኢትዮጵያ ከባድ ከባድ አደጋ ይዞ ይመጣል።
አሁን ላይ ኢራን በጅቡቲ በሚገኘው የአሜሪካ የጦር ቤዝ ላይ ጥቃት የመፈፀም እቅድ እንዳላት የታወቀ ነገር የለም።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
ሰበር ዜና‼️
የኢራን መንግስት ቲቪ ከደቂቃዎች በፊት እንደዘገበው ኢራን በእስራኤል ላይ "ከባድ እና አውዳሚ" አጸፋዊ ጥቃት በሰአታት ውስጥ ይጠበቃል"ሲል አስደምጧል።
የመካከለኛው ምስራቅ ጉዳይ አሳሳቢ ሆኗል።


@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
ኢራን ተኮሰች‼️
እስራኤል ለዜጓቿ ማስጠንቀቂያ ሰጥታለች።
የኢራን ጥቃት መቃረቡን ተከትሎ እስራኤል ዜጎቿን ለደህንነታቸው በማያሰጉ ቦታዎች እንዲቀመጡ፣እንቅስቃሴ እንዲቀንሱ እንዲሁም በጋራ ከመሰብሰብ እንዲቆጠቡ ትዕዛዝ አስተላልፋለች።
ኢራን ወደ እስራኤል ከደቂቃዎች በፊት ሚሳኤሎችን ተኩሳለች።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
ሁለት ሰበር መረጃዎች‼️
የእስራኤል ጦር ቴህራንን ልቀቁ ብሏል‼️
የእስራኤል ጦር በኢራን በሚገኙ ሁሉም የኒውክሌር ፋሲሊቲዎች እና የጦር መሳሪያ ማምረቻ ባሉ አካባቢዎች የሚገኙ ሁሉም ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ/evacuation/ የመጀመሪያውን ትዕዛዝ አስተላልፏል።
ነዋሪዎቹ ለቀው ከወጡ በኋላ አዲስ ትዕዛዝ እስከሚሰጥ ድረስ እንዳይመለሱ አዟል። እስራኤል በኢራን የኑክሌር ጣቢያዎች እና በመሳሪያ ማምረቻ ተቋማት ላይ ከፍተኛ ጥቃት ለመፈፀም እየተዘጋጀች ነው።
🎯የኢራኑ ጠቅላይ መሪ አሊ ካሜኔይ ምክትል ሃላፊ አሊ አስጋር ሄጃዚ በእስራኤል ጥቃት ሁኔታው ​​ከተባባሰ የኢራን መሪዎችና እና ቤተሰቦቻቸው ወደ ራሺያ የሚወጡበትን መንገድ ለማግኘት ከሩሲያ ባለስልጣናት ጋር ድርድር ላይ መሆናቸውን ኢራን ኢንተርናሽናል ከአንድ ከፍተኛ የኢራን አመራር መረጃ ማግኘቱን ዘግቧል።


@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
ሰበር‼️ ትራምፕ :- ቴህራንን አሁኑኑ ልቀቁ

ኢራን የኑክሌያር ስምምነቱን መፈረም ነበረባት፣እንዲፈርሙ ነግሬያቸው ነበር። ይህ በጣም አሳፋሪ ነው። ኢራን የኑክሌር ጦር መሳሪያ አይኖራትም። ይሄን በተደጋጋሚ ብዬዋለሁ። አሁን ሁሉም ኢራናዊያን የኢራንን ዋና ከተማ ቴህራንን በአስቸኳይ ለቀው መውጣት አለባቸው "ሲሉ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አጭር መልዕክት አስተላልፈዋል።
ይህን ተከትሎ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከ G7 ሀገራት ስብሰባ ቀደም ብለው በመውጣት ወደ  Situation room ሊያመሩ መሆኑ ታውቋል ።
አሜሪካን በይፋ ወደ ጦርነቱ የተቀላቀለች ይመስላል። በዚህም በዛሬው እለት ግዙፉ የአሜሪካ አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ  USS Nimitz ከነበረበት የደቡብ  ቻይና ስትራቴጂካዊ ቦታ ለቆ  ወደ መካከለኛው ምስራቅ እያመራ ከመሆኑም በተጨማሪ መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ድጋፎችን ለእስራኤል አድርጋለች።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
WW III ????

አሜሪካ ኢራን ላይ የአየር ጥቃት ሰነዘረች

አሜሪካ ፎርዶውን ጨምሮ ኢራን ውስጥ በሚገኙ 3 የኒውክሌር ተቋማት ላይ ጥቃት ማድረሷን ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ተናግረዋል።

አሜሪካ በፎርዶ፣ ናታንዝ እና ኢስፋሃን በሚገኙ የኢራን የኒውክሌር ጣቢያዎች ላይ “በጣም የተሳኩ” ጥቃቶችን ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትሩዝ ገፃቸው “የቴህራን የኒውክሌር መርሃግብር  ዘውድ” የሆነው ፎርዶው ጠፍቷል ሲሉ ጽፈዋል። ትራምፕ ኢራን ለመልሶ ማጥቃት ከተነሳች መዘዙ ከባድ መሆኑን አስጠንቅቀዋል። "አስታዉሱ ቀሪ ኢላማዎች አሉን" ሲሉ ኢራንን አስፈራርተዋል።

ኢራንም በፎርዶው የኒውክሌር ጣቢያ ጥቃት መድረሱን አረጋግጣለች። በጥቃቱ የዩኤስ ቢ-2 ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች ተሳትፈዋል ተብሏል።

ሃማስ "በኢራን ላይ የአሜሪካ ወረራ አደገኛ  ነው ብሏል።  ግልጽ የሆነ የአለም አቀፍ ህግ መጣስ ነው" ሲልም አክሏል።

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የትራምፕን ዉሳኔ “ድፍረት የተሞላበት ውሳኔ” መሆኑን አወድሰው፣ እስራኤል እና አሜሪካ የፈጸሙት “በሙሉ ቅንጅት” ነው ብለዋል።

የዩኤስ የጦር መሳሪያ ቁጥጥር ማህበር የአሜሪካ ጥቃቶችን "ህገ-ወጥ" ሲል አውግዟል። ድርጊቱ ኢራንን እና ሌሎች ሀገራትን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ የመፈለግ አደጋን ይጨምራልም ብሏል።

በአሁኑ ሰዓት በእየሩሳሌም እና ቴላቪቭ የፍንዳታ ድምፅ እየተሰማ እና የእስራኤል የቅድመ ማስጠንቀቂያ ድምጽ ለዜጎቿ እያሰማች መሆኑም ተዘግቧል።

ኡራን በተደጋጋሚ አሜሪካ ወደ ጦርነቱ እንዳትገባ ስታስጠነቅቅ የቆየች ቢሆንም አሜሪካ በይፋ ጦርነቱን ተቀላቅላለች። በቀጣይ የኢራን ምላሽ ይጠበቃል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
" የ12ቱ ቀናት ጦርነት ማብቃቱ ይበሰራል " - ዶናልድ ትራምፕ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እስራኤል እና ኢራን የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ መስማማታቸውን ገለጹ።

" እስራኤል እና ኢራን አሁን የያዟቸውን የመጨረሻ ተልእኮዎች ካጠናቀቁ በኃላ በ6 ሰዓታት ውስጥ  ለ12 ሰዓታት የሚቆይ የተሟላ የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ ሙሉ በሙሉ ተስማምተዋል " ብለዋል።

በዚህም ጦርነቱ እንደተጠናቀቀ እንደሚቆጠር ትራምፕ ገልጸዋል።

" ኢራን በስምምነቱ መሰረት ስምምነቱን ተኩስ አቁሙን በይፋ ትጀምራለች " ያሉት ትራምፕ " እስራኤል በ12ኛው ሰዓት ትከተላለች " ብለዋል።

በ24ኛው ሰዓት " የ12 ቀናት ጦርነቱ " ማብቃቱን ለዓለም ህዝብ በይፋ እንደሚበሰር ፤ ሁለቱም ወገኖች ለስምምነቱ መከበር ተከባብረው እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

" ይህ ጦርነት ለዓመታት ሊቆይ መላው መካከለኛውን ምስራቅ ሊያጠፋ ይችል ነበር " ያሉት ዶናልድ ትራምፕ " ግን በፍጹም አልሆነም አይሆንም " ብለዋል።

" አምላክ እስራኤልን ይባርክ፣ አምላክ ኢራንን ይባርክ፣ አምላክ መካከለኛውን ምስራቅን ይባርክ፣  አምላክ አሜሪካን ይባርክ፣ እንዲሁም አምላክ መላው ዓለምን ይባርክ " ሲሉ ገልጸዋል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
🇪🇹 ኢትዮ Students
ድብድብ‼️😁 በአዲስ አበባ ከተማ የትራፊክ ፖሊስ እና አሽከርካሪ ሲደባደቡ ተመልክተናል። ይህ ክስተት የተከሰተው ሳሊተ ምህረት አካባቢ ነው ብለውናል። @ETHIOSTUDENTS @ETHIOSTUDENTS
ግለሰቡ የ25 ቀናት እስር ተፈረደበት‼

ከላይ በቪድዮ ይመለከታል ።

በቅርቡ የትራፊክ ፖሊስ እንዲሁም የመንግስት ስራተኛ የሆነ ግለሰብ የደበደበው ተከሳሽ ታማኝ አስማማው አንዳርጌ 3 ዓመት የተፈረደበት ሲሆን ነገር ግን ተከሳሹ አረንጓዴ አሽራ በችግኝ ተከላ አስተዋጽኦ ያደረገ ስለሆነ፣የቤተሰብ አስተዳዳሪ ስለሆነ፣ ታማሚ ስለሆነ ፣ ከዚህ በፊት ምንም አይነት የወንጀል ክስ የሌለበት እና ፀባዩ በጣም ጥሩ የሆነ ግለሰብ ስለሆነ ከሌላ የተዘርዘሩትን በሙሉ ታይተው ከ3 ዓመት ወደ 25 ቀን ወርዶ ተከሳሽ " ታማኝ አስማማው አንዳርጌ " የ25 ቀን እስር እንዲታሰር እንደተፈረደበት ተሰምቷል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
HTML Embed Code:
2025/06/28 20:38:40
Back to Top