TG Telegram Group Link
Channel: ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ
Back to Bottom
የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ከ1.5 ትሪሊዮን ብር በላይ ጉዳትና ኪሳራ ማድረሱን መንግሥት ይፋ አደረገ

-ሦስት ሚሊዮን ነዋሪዎች የከፋ ድህነት ውስጥ ናቸው ተብሏል

-ከአጠቃላይ የአካባቢዎቹ ነዋሪዎች አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት መጎዳታቸው ተገልጿል

በሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች በተለይም ማዕከሉን በትግራይ ክልል አድርጎ ለሁለት ዓመታት በተካሄደውና በሌሎች የተወሰኑ አካባቢዎች በነበረው ጦርነት፣ ከ1.5 ትሪሊዮን ብር በላይ የሚገመት ጉዳትና ኪሳራ በአገር ላይ መድረሱን ገንዘብ ሚኒስቴር ይፋ አደረገ።

ግንቦት 9 ቀን 2015 ዓ.ም. የገንዘብ ሚኒስቴርን የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያቀረቡት ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ፣ ተቋማቸው በሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች በተካሄደው ጦርነት የደረሰውን ጉዳትና የመልሶ ግንባታ ፍላጎት የተመለከተ የዳሰሳ ጥናት (Damage and Needs Assessment) በማከናወን፣ የጥናት ውጤቱን ለመንግሥት እንዳቀረበ ተናግረዋል።

በጥናት ግኝቱ መሠረትም ያጋጠመው አጠቃላይ ጉዳትና የኢኮኖሚ ኪሳራ በአጠቃላይ 28 ቢሊዮን ዶላር እንደሚሆን ሪፖርታቸው አመላክቷል። ይህም በወቅቱ የውጭ ምንዛሪ ተመን ከ1.5 ትሪሊዮን ብር በላይ ነው።

ለቋሚ ኮሚቴው ያቀረቡት ሪፖርት ላይ ከተቀመጠው መረጃ መረዳት እንደተቻለው፣ ‹‹22 ቢሊዮን ዶላር ወይም ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት (GDP) 20.4 በመቶ የሚገመት ጉዳት›› ደርሷል።

በዚሁ ምክንያት የደረሰው የኢኮኖሚ ኪሳራ ደግሞ፣ ‹‹ስድስት ቢሊዮን ዶላር ወይም ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት (GDP) 5.5 በመቶ የሚገመት የኢኮኖሚ ኪሳራ (Economic Loss)›› መድረሱን ሪፖርቱ ያመለክታል።

ግጭትና ጦርነት በነበረባቸው አካባቢዎች ከሚገኙ ጠቅላላ ነዋሪዎች ውስጥ አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት በጦርነቱ በቀጥታ የተጎዱ መሆናቸውን፣ ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ ሦስት ሚሊዮን የሚሆኑት የአገሪቱ ዜጎች በጦርነቱ ምክንያት የከፋ ድህነት ውስጥ መግባታቸውንም አስረድተዋል።

ሚኒስትሩ ባቀረቡት ሪፖርት የተቀመጠው የጉዳት መጠን፣ ኢትዮጵያ ባለፉት በርካታ ዓመታት ከውጭ አበዳሪዎች ለኢኮኖሚ ልማት ተበድራ ካልመለሰችው አጠቃላይ የውጭ ዕዳ ጋር እኩል መሆኑን መረዳት ይቻላል። የገንዘብ ሚኒስቴር በየሩብ ዓመቱ ይፋ በሚያደርገው የዕዳ ሁኔታ መግለጫ መሠረት፣ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ያለባት አጠቃላይ የውጭ ዕዳ መጠን 28 ቢሊዮን ዶላር ነው።

በጦርነቱ የደረሰውን ጉዳት ለመቀልበስና ከጦርነት በፊት ወደነበረበት ሁኔታ ለመመለስ እንዲቻል ለአምስት ዓመታት (እ.ኤ.አ. ከ2023 እስከ 2028 ድረስ) የሚቆይ የመልሶ ማቋቋምና ግንባታ አገራዊ የዕቅድ ማዕቀፍ (Ethiopia Resilient Recovery and Reconstruction Planning Framework) መዘጋጀቱን አስረድተዋል።

ለዚህ ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ 20 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ በዕቅድ ማዕቀፉ መመላከቱንም ገልጸዋል።

በዓለም ባንክና በኢትዮጵያ መንግሥት መካከል በተደረገ የዕርዳታ ስምምነት፣ ፕሮግራሙን ወደ ሥራ ለማስገባት እንደ መነሻና መንደርደሪያ የሚሆን 300 ሚሊዮን ዶላር ተመድቦ ወደ ሥራ መገባቱንም ጠቁመዋል። በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥም የደረሰውን ጉዳት መጠንና የመልሶ ግንባታ ፍላጎት የሚገልጽ ዝርዝር መረጃ ይፋ እንደሚደረግ ሚኒስትሩ አክለዋል።

የተለያዩ የውጭ የልማት አጋሮች በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለመገንባትና ነዋሪዎችን ለማቋቋም የተለያዩ ድጋፎችን ለማድረግ ይሁንታ እየሰጡ ሲሆን፣ መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሥር የሚገኙ ኤጀንሲዎች ባለፉት ሁለት ሳምንታት ጉዳት በደረሰባቸው ክልሎች በመገኘት ከክልሎቹ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ጉዳት የደረሰባቸውን ማኅበረሰቦች ለማቋቋምና ለመደገፍ የሚውል 2.3 ቢሊዮን ዶላር በጀት ለመመደብ መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።

በጀቱ ለሁለት ዓመታት የሚተገበሩ የማገገሚያ ፕሮጀክቶችን ለማከናናወን የሚውል ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ አመዛኙ በጀት በትግራይ ክልል ለሚተገበሩ ፕሮጀክቶች ወጪ እንደሚደረግም ታውቋል።

የፕሮጀክት ትገበራውን በመጪው ወር ለመጀመር የወሰኑ ሲሆን፣ ወደ ትግበራ ለመግባት የሚያስፈልግ 250 ሚሊዮን ዶላር በጀት ከተመድ የፋይናንስ ምንጮች ለማስፈቀድ ንግግር ላይ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።(ሪፖርተር)

(ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ)
- በቴሌግራም :- https://bit.ly/3jHql5q
- በፌስቡክ ፡- https://bit.ly/3jIjJ6
- በትዊተር ፡- https://bit.ly/37MJGzf
- በዌብሳይት :- https://bit.ly/3KOpzz8
- በዩትዩብ፦https://youtube.com/@originsbusiness2203
ይቀላቀሉና ቤተሰብ ይሁኑን እናመሰግናለን
የኮንስትራክሽን ዘርፍ በውጭ ኮንትራክተሮች በመያዙ የአገር ውስጥ ኮንትራክተሮች ከዘርፉ ውጭ እየሆኑ ነው ተባለ

ባንኮች ለኮንስትራክሽን ግንባታ ዋስትና የሰጡት ገንዘብ ከ90 ሚሊዮን ብር በላይ መድረሱ ተጠቁሟል

የኮንስትራክሽን ዘርፉ በውጭ ሥራ ተቋራጮች ወረራ በሚባል ደረጃ በመያዙ፣ የአገር ውስጥ ኮንትራክተሮች ከጨዋታ ውጪ እየሆኑ መምጣታቸውን፣ የኢትዮጵያ ኮንትራክተሮች ማኅበር አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ኮንትራክተሮች ማኅበር ፕሬዚዳንት አቶ ግርማ ሀብተ ሥላሴ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በአሁኑ ጊዜ አጠቃላይ የአገሪቱ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ችግር ውስጥ ከመሆኑም በላይ፣ ለውጭ ኮንትራክተሮች የተከፈተላቸው የዕድል በር እነሱን እያፈረጠመ የአገር ውስጥ ኮንትራክተሮችን እየጎዳ ነው፡፡

‹‹በቅርቡ በተደረገ ጥናት እንዳየነው ትልልቅ ከሚባሉ የመንግሥት ሜጋ ፕሮጀክቶች መካከል፣ የአገር ውስጥ ኮንትራክተሮች ድርሻ ሦስት በመቶ ብቻ ነው፤›› ያሉት አቶ ግርማ፣ በመንገድ፣ በሕንፃ፣ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታና በመሳሰሉት የውጭ ኮንትራክተሮች በተለይ የቻይና ኮንትራክተሮች ሥራውን በሞኖፖል ይዘውታል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን ሊሠሩት የሚችሉዋቸው ሥራዎች ሳይቀሩ ለውጭ ኮንትራክተሮች እየተሰጡ መሆናቸውን የገለጹት አቶ ግርማ፣ አሁንም የተለያዩ የግንባታ ሥራዎች በከፍተኛ ዋጋ አንዳንዴም ያለ ጨረታ ለውጭ ኮንትራክተሮች እየተሰጡ ስለሆነ የአገር በቀል ኮንትራክተሮችን ችግር ማባባሳቸውን አስረድተዋል፡፡

‹‹በተለይ በመንገድ ሥራ ዘርፍ የቻይና ኩባንያዎች ገበያውን ይዘውታል፡፡ ከኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ያገኘነው ወቅታዊ መረጃ እንደሚያመለክተው፣ በአሁኑ ወቅት በውጭ ኮንትራክተሮች እጅ ከሚገኙ 71 የመንገድ ፕሮጀክቶች ውስጥ 90 በመቶው በቻይና ኮንትራክተሮች የተያዘ ነው፤›› ሲሉ አቶ ግርማ የችግሩን ግዝፈት ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ መንገድ ሥራ ከተሰማሩት 31 የውጭ ኮንትራክተሮች ውስጥ 25ቱ የቻይና ኮንትራክተሮች እንደሆኑ፣ ከቻይና ኩባንያዎች ውስጥ ደግሞ ሲሲሲሲ፣ ሲሲኢሲሲ እና ቻይና ሬልዌይ ሰባተኛ ግሩፕ 77 ግንባታዎችን በመውሰድ ቀዳሚዎቹ እንደሆኑ ይነገራል፡፡

ሲሲሲሲ ሰባቱን መንገድ እየሠራ ያለው ከሃያ ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ሲሆን፣ ሲሲኢሲሲ ደግሞ ከአሥር ቢሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸውን ሥራዎች ወስዶ እየሠራ መሆኑን፣ የአገር ውስጥ ኮንትራክተሮች ግን በመንገድ ሥራ ላይ ያላቸው ተሳትፎ እጅግ አነስተኛ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

በአብዛኛው ጨረታዎች ሲወጡ ለጨረታው እንደ መሥፈርት የሚቀመጡ መመዘኛዎች የአገር በቀል ኮንትራክተሮችን ተሳትፎ አናሳ እንዳደረገው ፕሬዚዳንቱ አብራርተዋል፡፡ በትልልቅ ጨረታዎች አገር በቀል ኮንትራክተሮች እንደሚሳተፉ የሚቀመጠው መሥፈርትም፣ የውጭዎቹ ኩባንያዎች ያለ ችግር ጨረታውን አሸንፈው ሥራውን ለመረከብ እያስቻላቸው ነው ብለዋል፡፡

‹‹አንዳንድ ፕሮጀክቶች የአገር ውስጥ ኮንትራክተሮች እንዳይገቡባቸው የተፈለገ ይመስላል፤›› ሲሉ ሪፖርተር ያነጋገራቸው ኮንትራክተሮች ተናግረዋል፡፡ ለምሳሌ በኤርፖርት ማስፋፊያ ውስጥ ወደ 12 ከሚሆኑ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ውስጥ ሰባት ያህሉ ለቻይናው ሲሲሲሲ ኮንትራክተር ተሰጥቷል ብለዋል፡፡ እነዚህ ወደ 800 ሚሊዮን ዶላር የሚጠይቁ ፕሮጀክቶች መሆናቸውን፣ አሁንም በቀላሉ በአገር ውስጥ ኮንትራክተሮች ሊከናወኑ እንደሚችሉ፣ ቀሪ ፕሮጀክቶችንም ይኸው የቻይና ኮንትራክተር ይሥራ ከተባለ የአሠራር ችግር መኖሩን የሚያሳይ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የቻይና ኮንትራክተሮች በኮንስትራክሽን ዘርፉ ውስጥ በትሪሊዮን ብር የሚገመት ሥራ ያከናወኑና እያከናወኑ መሆናቸውን የገለጹት ኮንትራክተሮች፣ ያለውን ችግር በመረዳት አገር በቀል ኮንትራክተሮችን የሚደግፉ ሕግጋትን ማውጣትና ያሉትንም ማሻሻያ ማድረግ የአገር ውስጥ ኮንትራክተሮች በአጭር ጊዜ ይጠፋሉ ብለዋል፡፡

የውጭ ኮንትራክተሮች ተፅዕኖ ብቻ ሳይሆን በክልል አስተዳደሮች በባለቤትነት የተቋቋሙ የኮንስትራክሽን ድርጅቶችም፣ በግል ለተቋቋሙ የአገር በቀል ኮንትራክተሮች ጫና እየፈጠሩባቸው እንደሆነ አቶ ግርማ ሳይጠቅሱ አላለፉም፡፡ ለክልል የኮንስትራክሽን ድርጅቶች በቀጥታ የግንባታ ሥራዎችን በመስጠት፣ ኮንትራክተሮች ተወዳድረው ሥራ እንዳያገኙ እያደረገ በመሆኑ ብዙ አገር በቀል ኮንትራክተሮች ከጨዋታ ውጪ እየሆኑ መሆኑንም አቶ ግርማ አስረድተዋል፡፡(ሪፖርተር)

(ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ)
- በቴሌግራም :- https://bit.ly/3jHql5q
- በፌስቡክ ፡- https://bit.ly/3jIjJ6
- በትዊተር ፡- https://bit.ly/37MJGzf
- በዌብሳይት :- https://bit.ly/3KOpzz8
- በዩትዩብ፦https://youtube.com/@originsbusiness2203
ይቀላቀሉና ቤተሰብ ይሁኑን እናመሰግናለን
ቅዳሜ ጠዋት ግንቦት 12 ቀን 2015 ዓም በኢትዮ የንግድ እና ኢንቨስትመንት መድረክ

-በቢዝነስ ቅኝት የሰሞኑ የቢዝነስ ዜናዎች ቀርበዋል።

-በእንግዳ ሰዐት የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ስላስጀመረው Customized Forward Trade ( ወደፊት የሚፈፀም ግብይት ) ምንነት ተነጋግረናል።

- ወደፊት የሚፈፀም ግብይት ምን ማለት ነው? አሁን ያስፈለገበት ምክንያት ምንድነው ? ስራውስ ምን ደረጃ ላይ ይገኛል ? በሚለው ዙሪያ ተወያይተናል።

እንግዳችን የኢትዮጵያ ምርት ገበያ የመጋዘን ኦፕሬሽን መምሪያ ሃላፊ አቶ በሃይሉ ንጉሴ ናቸው።

ከአቶ በሃይሉ ንጉሴ ጋር ያደረግነውን ቆይታ ከታች ያለውን ሊንክ ተጭነው እንዲያደምጡን ተጋብዘዋል።

https://soundcloud.com/user-953568/12-9-15a?si=2f230469f5c2448db3607711ff3f58f6&utm_source=clipboard&utm_medium=text&utm_campaign=social_sharing

ኦሪጅንስ ሚዲያ ከኢትዮ ኤፍኤም 107.8 ጋር በመተባበር።

ኢትዮ ቴሌኮም እና አማራ ባንክ የፕሮግራማችን የክብር ስፖንሰር ናቸው። እናመሠግናለን።


(ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ)
- በቴሌግራም :- https://bit.ly/3jHql5q
- በፌስቡክ ፡- https://bit.ly/3jIjJ6
- በትዊተር ፡- https://bit.ly/37MJGzf
- በዌብሳይት :- https://bit.ly/3KOpzz8
- በዩትዩብ፦https://youtube.com/@originsbusiness2203
ይቀላቀሉና ቤተሰብ ይሁኑን እናመሰግናለን
የዕለቱ የምንዛሪ ተመን
ሰኞ ምሽት ግንቦት 14 ቀን 2015 ዓም በኢትዮ የንግድ እና ኢንቨስትመንት መድረክ

-የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አሜሪካ አትላንታ ጆርጂያ በሳምንት 4 ቀናት በረራ መጀመሩ ይታወሳል።

ከአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተነስቶ አትላንታ ሃርትፊልድ ጃክሰን ባረፈው በቦይንግ 787 ድሪም ላይነር አዉሮፕላን የበረራ ቁጥር 518 ከተሳፈሩ ሰዎች መካከል ባልደረባችን ቃለኢየሱስ በቀለ አንዱ ነው።

ስለ በረራው አጠቃላይ ሁኔታ ከአትላንታ ጆርጂያ በስልክ መስመራችን ላይ ተገኝቶ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥቶናል።

-እንዲሁም በእንግዳ ሰዓት ስለ ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ የስራ እንቅስቃሴ ተወያይተናል ።

እንግዳችን የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ አ.ማ መስራች እና ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ፍሰሐ እሸቱ ናቸዉ፡፡

ኩባንያዉ በግብርና ስራ ፣ በግብርና ምርቶች አቅርቦት እና በኢኮሜርስ የስራ መስኮች የተሰማራ አገር በቀል አክሲዮን ኩባንያ ነዉ፡፡

ኩባንያዉ ከምስረታዉ ጀምሮ ስላከናወናቸዉ የግብርና እና የንግድ እንቅስቃሴዎች ዙሪያ ከዶ/ር ፍሰሐ እሸቱ ጋር ተወያይተናል ።

ከታች ያለውን ሊንክ ተጭነው የመጀመሪያውን ክፍል እንዲያደምጡን ተጋብዘዋል፡፡

https://soundcloud.com/user-953568/14-9-15a-3?si=f3fd8d3f8ef94c52bbe33d61332667dc&utm_source=clipboard&utm_medium=text&utm_campaign=social_sharing

ኦሪጅንስ ሚዲያ ከኢትዮ ኤፍኤም 107.8 ጋር በመተባበር፡፡

ብርሃን ባንክ የፕሮግራማችን የክብር ስፖንሰር ነው፡፡ እናመሰግናለን፡፡

(ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ)
- በቴሌግራም :- https://bit.ly/3jHql5q
- በፌስቡክ ፡- https://bit.ly/3jIjJ6
- በትዊተር ፡- https://bit.ly/37MJGzf
- በዌብሳይት :- https://bit.ly/3KOpzz8
- በዩትዩብ፦https://youtube.com/@originsbusiness2203
ይቀላቀሉና ቤተሰብ ይሁኑን እናመሰግናለን
የዕለቱ የምንዛሪ ተመን
ዘመን ባንክ በ1.5 ቢሊየን ብር ወጪ ሲያስገነባው የነበረው ባለ 36 ወለል ግዙፍ  ሕንፃ ተጠናቀቀ

፦ግዙፉንና ዘመናዊውን አዲሱን የዋና መስሪያ ቤቱን ሕንጻ ዛሬ ግንቦት 19 2015 ዓም ያስመርቃል

፦ባንኩ ባለፉት 5 ዓመታት ያስመዘገበው ውጤት በኢትዮጵያ ባንክ ኢንዱስትሪ ከቀዳሚዎቹ ተርታ አሰልፎታል፡፡

እ.ኤ.አ በ 2008 በአንድ የባንክ ማዕከል፤ በ 87.2 ሚሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል የኢትዮጵያን የባንክ ኢንዱስትሪ የተቀላቀለው ዘመን ባንክ ወደ 15 አመት በሚጠጋ ስኬታማ ጉዞው የአገልግሎት አድማሱን በማስፋት የባንክ ማዕከላቱን ቁጥር በመጨመር ተደራሽነቱን እያሰፋ ይገኛል፡፡

ከዚህ ተነስቶ በፍጥነት እያደገ የሚገኘው ዘመን ባንክ እንደ ስያሜው የዘመነ የባንክ ቴክኖሎጂዎችን በሀገሪቱ ቀድሞ በማስተዋወቅና በመተግበር ግንባር ቀደም ባንክ ሲሆን ለአብነትም የኤቲኤም፤ የኢንተርኔትና የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎትን በአንድነት አጣምሮ የያዘው ኦምኒ ቻናል አገልግሎትን እንዲሁም በዚሁ ዘርፍ ማስተር ካርድ የተሰኘውን አለምአቀፍ የክፍያ ካርድ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በማስተዋወቅ አለም አቀፍ አገልግሎትን እየሰጠ ይገኛል፡፡

ዘመን ባንክ በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ደንበኞች ያለማንም እገዛ ጥሬ ገንዘብ ወደ ሂሳባቸው በአውቶማቲከ ገንዘብ መቀበያ ማሽን አማካኝነት በቀጥታ ማስገባት እንዲችሉ ያስቻለ ባንክ ነው፡፡ አሁን በሁለት ቅርንጫፎች የሚሰጠውን ይህን አገልግሎቱን በርከት ባሉ ቅርንጫፎች ለመስጠት የማሽን ግዥዎችን አከናውኖ የተከላ ሂደቱን በማከናወን ላይ ይገኛል ተብሏል፡፡


ሕንጻው TIER-3 የደህንነት ደረጃ ያለው የዳታ ሴንተር ያካተተ ነው፡፡ ይህ የዳታ ሴንተር ከከፍተኛ የደህንነት ብቃቱ በተጨማሪ አስፈላጊውን ቴክኖሎጂ ያሟላ ሲሆን የኃይል አቅርቦትና የማቀዝቀዣ ቴክኖሎጂዎችን ያሟላ ነው፡፡ ሕንጻው ባለው ተጨማሪ የኃይል አቅርቦት፤ በዓለም አቀፍ የደረጃ መስፈርት መሰረትም የኃይል መቆራረጡ በጣም ዝቅተኛ ወይንም ለዜሮ የቀረበ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡


ይህም ማንኛውም በሕንጻው የሚሰጥ አገልግሎት በማንኛውም ጊዜና ሁኔታ እንዳይስተጓጎል በተዘረጋለት ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ስርዓት ከሰው ንክኪ ውጪ (Automated) በሆነ ስርዓት ስራዎች እንዲቀጥሉ የሚያስችል ነው፡፡

ዘመን ባንክ ከማስተር ካርድ ጋር ባለው የስራ ግንኙነት የጉዞ ቅድመ - ክፍያ ማስተርካርድ ደንበኞች ለውጭ ሀገር ጉዟቸው አስቀድመው የሚያስፈልጋቸውን ወጪ በመገመት፣ ሊያከናውኑ ያቀዷቸውን ተግባራት በቀላሉ መፈጸም እንዲችሉ የተዘጋጀ የካርድ አገልግሎት ተግባራዊ አድርጓል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የባንኩን የክፍያ ሂደት ከሌሎች አገልግሎት ሰጪዎች አንደ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ ሳፋሪኮም የመሳሰሉት ጋር በማስተሳሰር ማህበረሰቡ በዲጂታል የክፍያ ስርዓት አገልግሎት ማግኘት የሚችልበትን ስርዓት ዘርግቷል፡፡

በእነዚህና መሰል የዲጀታል አገልግሎቶች ዘመናዊ አሰራሩን እያስፋፋና እያስተዋወቀ የሚገኘው ዘመን ባንክ ባለፉት አምስት አመታት በሁሉም ክንውኖቹ ውጤታማ ሲሆን በተለይም አጠቃላይ ትርፉ፤ ወረቱንና (ካፒታሉን) አንጡራ ሐብቱን የትርፍ ድርሻ ክፍፍል መጠኑ ከፍተኛ እድገት አስመዝግቧል፡፡

ዘመን ባንክ ባለፉት አመታት ባስመዘገበው ተከታታይ ዕድገት እነሆ ዛሬ የደረሰበትን ዕድገት ማሳያ የሆነውን ዘመናዊ ሕንፃም አስገንብቶ አጠናቋል፡፡ ግንባታውን ያከናወነው ተቋራጭ China Wu Yi CO, LTD የተሰኘ የቻይና መንግስት ተቋራጭ ኩባንያ ሲሆን ግንባታውም አምስት አመታትን የፈጀ ነው፡፡

ይህ ዘመናዊ ሕንጻ ሁሉንም የግንኙነት አማራጮችን በቴክኖሎጂ ያቀፈ፤ የመረጃ መሰብሰቢያና ማደራጃ እንዲሁም መተንተኛ ማዕከላት ያሉት፤ የአደጋ ጊዜ የነፍስ አድን የኤሌክትሪክ መሳሪያዎች የተገጠሙለት፤ ተለዋዋጭ የዓየር ሁኔታን የሚያመጣጥኑ፤ የሚቋቋሙና የሚያላምዱ መሰረተ ልማቶች የተዘረጉለት ነው::

እንዲሁም ዘመናዊ የጽዳትና የንጽህና መጠበቂያ እንዲሁም የአካል ብቃት ማጎልበቻ ክፍሎችን፤ እስከ 2 መቶ ተሳታፊዎችን የመያዝ አቅም ያላቸው ስብሰባ አዳራሾች፤ እያንዳንዳቸው 13 ተሳፋሪዎችን የሚያጓጉዙ 6 አሳንሰሮች፤ 200 ተሽከርካሪዎችን ማቆየት የሚያስችል የምድር ቤትና ፎቅ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎችን ይዟል፡፡ ሕንጻው በ 2300 ካሬ ሜትር ስፋት ላይ ያረፈ ሲሆን ከፊልና ሙሉ ምድር ቤቱን ጨምሮ 36 ወለሎች አሉት፡፡


(ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ)
- በቴሌግራም :- https://bit.ly/3jHql5q
- በፌስቡክ ፡- https://bit.ly/3jIjJ6
- በትዊተር ፡- https://bit.ly/37MJGzf
- በዌብሳይት :- https://bit.ly/3KOpzz8
- በዩትዩብ፦https://youtube.com/@originsbusiness2203
ይቀላቀሉና ቤተሰብ ይሁኑን እናመሰግናለን
ኢትዮ ቴሌኮም ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ስማርት የመማሪያ ክፍል (SMART CLASSROOM) በአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ በማቋቋም በይፋ ሥራ አስጀመረ

ኩባንያዉ ለሃገራችን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እድገት አስቻይ የሆኑ፣ በቴክኖሎጂ የተደገፉ እንዲሁም ለማህበረሰቡ የዕለት ከዕለት የኑሮ እንቅስቃሴ ትልቅ ፋይዳ ያላቸው በርካታ ስትራቴጂያዊ እቅዶችን ነድፎ ተግባራዊ በማድረግ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ ለሃገራችን ፈርቀዳጅ የሆነውን ስማርት የመማሪያ ክፍል ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ አራት ኪሎ ካምፓስ በመገንባት በትናንትናዉ ዕለት በይፋ ሥራ ላይ እንዲውል አድርጓል፡፡

በመሆኑም ኩባንያዉ አካታች እና ጥራት ያለው ትምህርት ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ የተያዘውን እቅድ በቴክኖሎጂ ለመደገፍ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የስማርት የመማሪያ ክፍል በመገንባት ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስረክቧል፡፡

ኩባንያዉ በትምህርት ዘርፉ ግንባር ቀደም ተዋናይ ከመሆኑም ባሻገር በሃገር አቀፍ ደረጃ የትምህርት ዘርፉን ለማሻሻል እና የዲጂታል ኢትዮጵያን ራዕይ እውን ለማድረግ የተያዘውን እቅድ ለማሳካት፣ የመማር ማስተማሩ ሂደት በቴክኖሎጂ እንዲታገዝ ለማድረግ እንዲሁም እየተከናወኑ የሚገኙ ሁለገብ ሀገራዊ ጥረቶች ይበልጥ ፍሬ እንዲያፈሩ የበኩሉን ከፍተኛ ድርሻ በመወጣት ላይ ይገኛል ተብሏል፡፡

የስማርት የመማሪያ ክፍሉ የተለያዩ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች የተሟሉለት በመሆኑ የመማር ማስተማሩን ሂደት በቀላሉ ለማከናወን ያስችላል የተባለ ሲሆን፣ በተለይም የትምህርት ተቋማት የትምህርት ዘርፍን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዕውን ለማድረግ፣ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል፣ የማስተማሪያ ወጪዎችን ለመቀነስ በተለይም ለቤተሙከራ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ለመግዛት የሚውሉ ወጪዎችን ለመቀነስ፣ የትምህርት መረጃዎችን በቀላሉ ለማግኘት እና የዲጂታል ቴክኖሎጂውን በሚጠቀሙ እና በማይጠቀሙ መካካል ያለውን ክፍተት ለማጥበብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለዉ ተገልጿል፡፡

ይህ በትናንትናዉ ዕለት በይፋ ሥራ የጀመረው ስማርት የመማሪያ ክፍል ሌሎች ተመሳሳይ የስማርት መማሪያ ክፍሎችን በሃገራችን በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ለመገንባት እንደናሙና የሚያገለግል ይሆናልም ነዉ የተባለዉ፡፡
በተጨማሪ የስማርት የመማሪያ ክፍሉ መምህራን በቀላሉ ማስተማር እንዲችሉ፣ የንድፈ ሃሳብትምህርቶችን በቴክኖሎጂ ቤተ-ሙከራ እንዲደገፉ፣ የትምህርት አሰጣጡን ከሁኔታዎች ጋር ለማጣጣም፣የተማሪዎቹን ሁኔታ ለመከታተል፣ የምዘና ፈተናዎችን ለማረም እና ውጤቶችን ወዲያውኑ ለማሳወቅእንዲሁም የተማሪዎችን የትምህርት መረጃዎች በቀላሉ ለማግኘት ያስችላቸዋል፡፡

በተጨማሪም ተማሪዎች ከልማዳዊ ትምህርት አንጻር በተግባራዊ ተሞክሮ የበለጸገ እና የተሻለ የትምህርት ተሞክሮ እንዲኖራቸው፣በየትኛወም ጊዜና ቦታ እንዲማሩ በተለይም በአካል ተገኝተው መማር የማይችሉ ተማሪዎች በቀላሉ በቨርችዋል ክላስ ትምህርታቸውን መከታተል እንዲችሉ ትልቅ ፋይዳ አለው፡፡

ኩባንያዉ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በተለይም ያለንበት ዘመን የዲጂታል ዘመን እንደመሆኑ መጠን ለትምህርት ዘርፉ ልዩ ትኩረት በመስጠት የተለያዩ የትምህርት ግብዓቶችን ከማቅረብ እና የቴክኖሎጂ ድጋፎችን ከማድረግ ባሻገር በትምህርት ዘርፉ ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ በማድረግ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ ለአብነትም ባለፈው ዓመት በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች 66 የዲጂታል መማሪያማዕከላትን (digital learning centers) በመገንባት እና ሙሉ ግብዓቶችን በማሟላት ማስረከብ መቻሉ የሚታወስ ነዉ፡፡

ኩባንያዉ እንደ አንድ ሀገራዊ ተቋም የትምህርት ዘርፉን በመደገፍ እና የተሻለ ትውልድ ለመገንባትየሚደረገውን ጥረት ለማገዝ እንዲሁም በማህበረሰቡ ሁለንተናዊ የእድገት እንቅስቃሴ ላይ በቀጥታ በመሳተፍ ሀገራዊ አለኝታነቱንና ማህበራዊ ኃላፊነቱን መወጣቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡


(ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ)
- በቴሌግራም :- https://bit.ly/3jHql5q
- በፌስቡክ ፡- https://bit.ly/3jIjJ6
- በትዊተር ፡- https://bit.ly/37MJGzf
- በዌብሳይት :- https://bit.ly/3KOpzz8
- በዩትዩብ፦https://youtube.com/@originsbusiness2203
ይቀላቀሉና ቤተሰብ ይሁኑን እናመሰግናለን
HTML Embed Code:
2024/06/08 04:19:03
Back to Top