TG Telegram Group Link
Channel: Dr. Eyob Mamo
Back to Bottom
ደረጃ በደረጃ!

አንድን እስከ ወዲያኛው ልትሰሩ የምትፈልጉት ነገር ስትጀምሩ፣ በትልቁ ጀምራችሁ ምናልባት በጠበቃችሁት ፍጥነት አልሄድ ካላችሁ ቅነሳ ከምታደርጉ፣ መጀመሪያውኑ በጥቂቱ ጀምራችሁ ቀስ በቀስ ብታድጉ ይሻላል፡፡

ከጅማሬ ግለት የተነሳ በትልቁ ጀምራችሁ እንደገና መውረድ፣ በራስ መተማመናችሁ አብሮ እንዲወርድ ያደርገዋል፣ ከዚያ ጋርም ሰዎች በእናንተ ላይ የሚኖራቸውንም አመኔታም ወረድ ያደርገዋል፡፡

https://hottg.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
ሌሎች ሰዎች በእናንተ ውስጥ ሲኖሩ!

ሌሎች ሰዎች በእናንተ ውስጥ እየኖሩ እንደሆነ ለማወቅ . . .

• የእናንተና የእነሱ ግንኙነት አልቆለት እንኳን፣ ትምህርትና ስራ ላይ ማተኮር እስከማትችሉ ድረስ በፍጹም መርሳት የማትችሏቸው ሰዎች ካሉ፤ ሰዎቹ በእናንተ ውስጥ እየኖሩ ነው፡፡

• ጥቃቅን ውሳኔዎችን እንኳን ሳይቀር ከእነሱ ውጪ ምንም አይነት ውሳኔ ማድረግ የማትችሏቸው ሰዎች ካሉ፤ ሰዎቹ በእናንተ ውስጥ እየኖሩ ነው፡፡

• እነሱ ለሚሰማቸው ስሜትና ከዚያ ስሜታቸው ጋር በየቀኑ ለሚለዋወጠው በህሪያቸው የጥፋተኝነትን ስሜት የምትሸከሙት እናንተ ከሆናችሁ፤ ሰዎቹ በእናንተ ውስጥ እየኖሩ ነው፡፡

• እነሱና እናንተ ብቻ የምታውቁትን “አሳፋሪ” ወይም “አስፈሪ” ምስጢራችሁን እንዳያወጡባችሁ ስትሉ መንቀሳቀስ እስከማትችሉ ድረስ በእነሱ ቁጥጥር ስር ያደረጓችሁ ሰዎች ካሉ፤ ሰዎቹ በእናንተ ውስጥ እየኖሩ ነው፡፡

• ላጠፉት ጥፋት ተገቢውን ይቅርታ አድርጋችሁ ወደፊት ከመሄድ ይልቅ ቂም የያዛችሁባቸው ሰዎች ካሉ፤ ሰዎቹ በእናንተ ውስጥ እየኖሩ ነው፡፡

• በሰራችሁት ጥፋት ምክንያት ሰዎች ይቅርታ ነፍገዋችሁ ቂም ስለያዙባችሁ ብቻ ካለማቋረጥ በጭንቀት ውስጥ የምትኖሩ ከሆነ፤ ሰዎቹ በእናንተ ውስጥ እየኖሩ ነው፡፡

ፈጣሪ የራሳችሁን ሕይወት የሰጣችሁ እናንተው እንድትኖሩት እንጂ ሌላው ሰው በውስታችሁ ሆኖ እንዲኖር አይደለምና የሚከፈለውን ዋጋ ከፍላችሁ ተገቢውን ማስተካከያ አድርጉ፡፡ አለዚያ የእድሜ ልክ ዋጋ ትከፍላላችሁ፡፡

https://hottg.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
ስልጠናው የቀረው ሁለት ቀናት ብቻ !!!

የስልጠው ርእስ፡- “የገንዘብ አስተዳደር ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Money Management Skills and Discipline)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- ሰኔ 19, ሰኔ 26፣ ሐምሌ 3, ሐምሌ 10 እና ሐምሌ 17 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል

@DrEyobmamo

እናመሰግናለን!
ጥያቄ፡-

ስለገንዘብ አስተዳደር ለመማር ገንዘብ ሲኖረኝ ባስብ
አይሻልም?


መልስ፡-

ይህ አመለካከት ብዙዎች የሚሳሳቱበት አመለካከት ነው፡፡

የገንዘብ መኖር የገንዘብ አስተዳደር ብስለትን አያመጣም፡፡ ይህ ቢሆን ኖሮ በተለያዩ አጋጣሚዎች ገንዘብን ያገኙ ሰዎች ከሚወስዷቸው ጥበብ-የለሽ ምርጫና ውሳኔዎች የተነሳ ባላጡት ነበር፡፡

በተቃራኒው አንድ ሰው በእጁ ምንም ባይኖረው ወይም ጥቂት ኖሮት እንኳን በገንዘብ አስተዳደር ክህሎት ሲበስል፣ ገንዘብን የማግኘት፣ የማባዛትም ሆነ አጠቃቀሙን የማወቅን ብልህነትን ስለሚያዳብር ለእድገቱ ገደብ አይሮረውም፡፡

ለዚህ ነው ገንዘብን ለማምጣት፣ ለማባዛትም ሆነ በትክክለኛው መንገድ ለመጠቀም መጀመር ያለብን የአስተዳደር ክህሎቱንና ዲሲፕሊኑን በማዳበር ሊሆን የሚገባው፡፡

ለስልጠና ፈላጊዎች

ለስልጠናው መረጃ ለማግኘት ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገልጹ መረጃው ይላክሎታል

@DrEyobmamo
ጥያቄ፡-

የተዘጋጀው ስልጠና ምንም የመነሻ ገንዘብ ለሌለን ሰዎች በምን ይጠቅመናል?

መልስ፡-

ይህ ሃሳብ በስልጠናው ውስጥ ከምንመለከታቸው እውነታዎች መካከል አንዱ ነው፡፡

የሃብት መነሻው የገንዘብ በእጃችን መኖር ብቻ እንዳልሆነ ነው፡፡ ምንም እንኳን የገንዘብ ሃብት ባይኖረንም፣ የጊዜ ሃብት፣ የእውቀት ሃብት፣ የሰው ሃብት እና የመሳሰሉት ሃብቶች በበቂ ሁኔታ ያሉን ሰዎች አለን፡፡

እነዚህን ሃብቶች በትክክል ስንጠቀምባቸው የገንዘብን ገቢ እንድናገኝ መንገዱን እንደሚጠርጉልን እና እንዴት እንደምንጠቀምባቸው መሰልጠን ይኖርብናል፡፡

ለስልጠና ፈላጊዎች

ለስልጠናው መረጃ ለማግኘት ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገልጹ መረጃው ይላክሎታል፡፡

@DrEyobmamo
#Temer real estate

09-46-14-24-08

ፒያሳ ሊይሴ ገ/ማርያም ትምህርት ቤት አጠገብ 3ኛ ሳይታችን ሽያጭ ጀምረናል።

➢ ሙሉ ክፍያ ከ6.9 ሚሊዮን ብር ጀምሮ

➢ ከባለ 1 እስከ ባለ 3 መኝታ ቤቶች

➢ ከ63 ካሬ እስከ 146 ካሬ

👉ቅድመ ክፍያ 10% ብቻ

ከ 30% ጀምሮ ለሚከፍሉ ደንበኞቻችን 25% ቅናሽ ያገኛሉ።

በተጨማሪም የንግድ ሱቆች ፒያሳ አድዋ00 ፊት ለፊት ከ3.9ሚሊዮን ብር ጀምሮ

👉 በተለያዪ አካባቢዎች የመኖሪያ ቤቶች እና ሱቆች አሉን ።

1ኛ  ሳር ቤት አፍሪካ ህብረት ፊት ለፊት ሳይት

2ኛ  አያት ፈርስ ቤት ሳይት

3ኛ  ጋርመንት አፍሪካ CDC ፊት ለፊት ሳይት

4ኛ  አያት አደባባይ ፊት ለፊት ሳይት

5ኛ  አያት ሎማያድ ሳይት

6ኛ  ሱማሊ ትራ ሳይት ለሽያጭ አውጠናል

👉 ማሳሰቢያ ፤- ምንም አይነት የዋጋ ጭማሬ አናደርግም ።

ለበለጠ መረጃ

09-46-14-24-08
ጥያቄ፡-

በድህነት አድገው እኛንም በድህነት ባሳደጉን ቤተሰቦች ስር አድገን እንዴት በገንዘብ አቅም መሻሻል እንችላለን?

መልስ፡-

በአለም ላይ በገንዘብ አቅማቸው ከፍተኛ ደረጃ ላይ በደረሱ ሰዎች መካከል የተደረጉ ጥናቶች የሚጠቁሙን፣ 80% ባለሃብቶች ከዜሮ የተነሱ (first generation) ባለሃብቶች እንደሆኑ ነው፡፡ ለዚህ ያበቃቸውም ከገንዘብ ውጪ የሆኑ የባህሪይ፣ የዲሲፕሊን፣ የአዎንታዊ አመለካከትና የመሳሰሉት ሃብቶቻቸው ናቸው፡፡

በችግረኛ ሕብረተሰብና ቤተሰብ ስር ማደግ በትክክል ከተጠቀምንበት ያበረታናል፣ ለእድገት ያነሳሳናል፣ እንዲሁም በቁርጠኝናት እንድንሰራ ያነሳሳናል፡፡

በትክክል ካተጠቀምንበት ግን መራራ ወደመሆን ይወስደናል፣ ወደተሳሳቱ የገንዘብ ማግኛ መንገዶች ይመራናል፣ እንዲሁም ገንዘብ ለማውጣትና ኢንቨስት ለማድረግ እንድንፈራ ያደርገናል፡፡

ስለዚህ ተስፋ ሳንቆርጥ በንዘብ ለማደግ የሚስችለንን ክህሎት እና ዲሲፕሊን ማዳበር አማራጭ የሌለው መንገድ ነው፡፡

ለስልጠና ፈላጊዎች

ለስልጠናው መረጃ ለማግኘት ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገልጹ መረጃው ይላክሎታል

@DrEyobmamo
ጥያቄ፡-

ብዙዎቻችን ከእምነታችን አስተመህሮም ሆነ ከቤተሰባችን፣ ገንዘብ የክፉ ነገር ሁሉ ምንጭ እንደሆነ ሰምተን ስላደግን በገንዘብ ስለማደግ ስናስብ ከክፋት ጋር ስለሚገናኝብን እንሸሸዋለን፡፡ ይህ ሁኔታ እንዴት ይታያል?

መልስ፡-

ጥሩ ጥያቄ ነው፡፡

ገንዘብ በራሱ ክፉም ደግም አይደለም፤ ገንዘብ ጋለልተኛ (neutral) ነው፡፡

ገንዘብን በትክክለኛው መንገድ ስናገኘውና ለትክክለኛው ነገር ስናውለው አዎንታዊና ጤናማ ውጤት አለው፡፡

በተቃራኒው ገንዘብን በጠማማ መንገድ ለማግኘት ከሞከርንና የምናገኘውንም ገንዘብ ለአጉል ነገር ከተጠቀምንበት አሉታዊ ውጤት ይኖረዋል፡፡

ያም ሆነ ይህ ከገንዘብ አስፈላጊነት እና ጣልቃ ገብነት ውጪ የሆነ ሕይወት ስለሌለን አንደኛችንን ጤናማውን ክህሎትና ዲሲፕሊን ማዳበሩ ተመራጭ ነው፡፡

ለስልጠና ፈላጊዎች

ለስልጠናው መረጃ ለማግኘት ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገልጹ መረጃው ይላክሎታል

@DrEyobmamo
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
የብዙ ሰዎች ጥያቄ!

ቁጥራችሁ ብዙ የሆናችሁ ሰዎች በዚህ ቻናል ላይ የምለቃቸውን መርሆች ከክርስትና እምነት (መጽሐፍ ቅዱስ) አንጻር መማር እንደምትፈልጉ inbox እያረጋችhuልኝ በመሆኑ ይህንን መልስ እሰጣለሁ፡፡

በአጠቃላይ የምሰጣቸው ትምህርቶች አቀራረባቸው በሁለት ይከፈላል፡-

1. እምነት-ተኮር (Faith-Based)

2. እሴት-ተኮር (Value-based)

እንደምታዩት ሁሉ፣ በዚህ ቻናል ላይ የምለቃቸው ትምህርቶች እሴት-ተኮር (Value-based) ናቸው፡፡

ይህ ማለት የማንኛውም እምነት ተከታይ የሆነ ሰው ለሕይወቱ የሚጠቅሙ ተግባራዊ መመሪያዎችን የሚያገኝባቸው ትምህርቶች ናቸው፡፡

እምነት-ተኮር ትምህርቴን ለምትፈልጉ ወጣቶች በተለይ ለወጣቶች በቅርቡ የጀመርኩት የmentorship network ስላለና ለእሱም ቻናል ስለከፈትኩ እዚያ በመቀላቀል ያንን ትምህርት መከታተልና ወደፊትም በአካል የሚሰጡ ስልጠናዎች ላይ መካፈል ትችላላችሁ፡፡

ከዚህ በታች ባለው link በመጠቀም ቻናሉን join አድርጉ፡፡

https://hottg.com/impactyouthmentorship

Dr. Eyob Mamo
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
ስልጠናው የቀረው ሁለት ቀናት ብቻ !!!

የስልጠው ርእስ፡- “የገንዘብ አስተዳደር ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Money Management Skills and Discipline)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- ሰኔ 19, ሰኔ 26፣ ሐምሌ 3, ሐምሌ 10 እና ሐምሌ 17 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል

@DrEyobmamo

እናመሰግናለን!
እርምጃ ውሰዱ እንጂ !!!
እርምጃ ውሰዱ እንጂ !!!

አንድ ሰው አጠገቡ ለነበሩ ሰዎች በጨዋታ መልክ እንዲህ ሲል ጥያቄን አቀረበ፡-

“በአንድ መሬት ላይ በተጋደመ ትልቅ ግንድ ላይ ሶስት እንቁራሪቶች በመደዳ ቆመው ነበር፡፡ አንደኛዋ እንቁራሪት ቆመው ከነበረበት ግንድ ላይ ወደ መሬቱ ለመዝለል ወሰነች፡፡ ስንት እንቁራሪቶች ግንዱ ላይ ቀሩ?”

ይህንን ጥያቄ የሰሙት በሙሉ መልሳቸው፣ “ሁለት” የሚል ነበር፡፡ ሰውየውም መልሳቸው ትክክል እንዳልሆነ ገለጸላቸው፡፡ “አንዷ እንቁራሪት የመዝለል ውሳኔ አደረገች እንጂ አልዘለለችም፡፡ ስለዚህ አሁንም የቀሩት ሶስት እንቁራሪቶች ናቸው” ነበር ማብራሪያው፡፡

“አያችሁ”፣ አለ በመቀጠልም፣ “ይህ የሚያመለክተው ውሳኔን ከተግባር ጋር የማምታታት ዝንባሌያችንን ነው፡፡ አንድ ውሳኔ ወደተግባር እስኪለወጥ ድረስ ከውሳኔው በፊት ከነበርንበት ሁኔታና ደረጃ ትንሽም እልፍ አያደርገንም”፡፡ አብዛኛውን ጊዜ አንድን ነገር ለማድረግ ብዙ ካወጣን፣ ካወረድንና ከወሰንን በኋላ ልክ እንዳደረገ ሰው ኑሯችንን እንቀጥላለን፡፡ ውሳኔ ግን ያው ውሳኔ እንጂ ተግባር ማለት አይደለም፡፡

ለዚህ አይነቱ አደገኛ ልምምድ አጋልጠው ከሚሰጡ ሁኔታዎች መካከል . . .

1. ፍርሃት

አንድን ነገር ገና ሳንጀምረው፣ “ባይሳካስ” የሚል ፍርሃት የሚያጠቃን ከሆነ፣ ሁኔታው ቢሳካ የምናገኘውን ጥቅም ሳይሆን ባይሳካ የሚደርስብንን ጉዳት፣ ሃፍረትና የመሳሰሉት ነገሮች ነው የምናሰላስለው፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ ያሰብነውን ነገር ከመጀመር ይገታናል፡፡

መፍትሄው፡- ጥንቃቄ በተሞላው እና ትርፍና ኪሳራን ባመዛዘነ መልኩ ፍርሃትን መጋፈጥ ነው፡፡

2. ለነገ አስተላላፊነት

ለነገ የማስላለፍ ልማድ አንዳንድ ጊዜ ከፍርሃት ጋር ቢገናኝም ሌሎች ምክንያቶች ግን አሉት፡፡ ለምሳሌ፣ ለመጀመር ባሰብነው ነገር ላይ በቂ ክህሎት እንደሌለን ማሰብና በራስ አለመተማመን፣ የዲሲፕሊን ችግር፣ የሰዎችን ሃሳብ እየሰሙ ሃሳብን መለዋወጥ፣ በወቅቱ ስሜትና “ሙድ” ተጽእኖ ስር መውደቅ እና የመሳሰሉት፡፡

መፍትሄው፡- አንድን ነገር እንድናስተላለፍ የሚያደርግን ችግራችን ምን እንደሆነ መለየትና በማንበብ፣ በመሰልጠንና በመሳሰሉት መንገዶች መቅረፍ፡፡

3. ዓላማ ቢስነት

አንድ ለመጀመር ወይም ለማድረግ የምንፈልገው ነገር በመጨረሻ ከአንድ ማከናወን ከምንፈልገው ዋና ዓላማ ጋር የተነካካ ካልሆነ በውስጣችን ግለትና ጉጉት ስለሚጎድለን እርምጃን የመውሰድ አቅም አይኖረንም፡፡ ይህ የሚሆንበት ምክንያት ዋነኛው የመነቃቃት (Motivation) ምንጭ የሕይወት ዓላማ ማወቅ ስለሆነ ነው፡፡

መፍትሄው፡- የምናደርጋቸውን ነገሮች በሙሉ ከዋናው የሕይወታችን ዓላማ ጋር ወይም ከአንድ ወሳኝ ግብ ጋር መያያዙን እርግጠኛ መሆን፡፡

https://hottg.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
ስልጠናው የቀረው አንድ ቀን ብቻ !!!

የስልጠው ርእስ፡- “የገንዘብ አስተዳደር ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Money Management Skills and Discipline)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- ሰኔ 19, ሰኔ 26፣ ሐምሌ 3, ሐምሌ 10 እና ሐምሌ 17 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል

@DrEyobmamo

እናመሰግናለን!
HTML Embed Code:
2025/06/25 04:14:56
Back to Top