ጥያቄ፡-
ስለገንዘብ አስተዳደር ለመማር ገንዘብ ሲኖረኝ ባስብ
አይሻልም?
መልስ፡-
ይህ አመለካከት ብዙዎች የሚሳሳቱበት አመለካከት ነው፡፡
የገንዘብ መኖር የገንዘብ አስተዳደር ብስለትን አያመጣም፡፡ ይህ ቢሆን ኖሮ በተለያዩ አጋጣሚዎች ገንዘብን ያገኙ ሰዎች ከሚወስዷቸው ጥበብ-የለሽ ምርጫና ውሳኔዎች የተነሳ ባላጡት ነበር፡፡
በተቃራኒው አንድ ሰው በእጁ ምንም ባይኖረው ወይም ጥቂት ኖሮት እንኳን በገንዘብ አስተዳደር ክህሎት ሲበስል፣ ገንዘብን የማግኘት፣ የማባዛትም ሆነ አጠቃቀሙን የማወቅን ብልህነትን ስለሚያዳብር ለእድገቱ ገደብ አይሮረውም፡፡
ለዚህ ነው ገንዘብን ለማምጣት፣ ለማባዛትም ሆነ በትክክለኛው መንገድ ለመጠቀም መጀመር ያለብን የአስተዳደር ክህሎቱንና ዲሲፕሊኑን በማዳበር ሊሆን የሚገባው፡፡
ለስልጠና ፈላጊዎች
ለስልጠናው መረጃ ለማግኘት ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገልጹ መረጃው ይላክሎታል
@DrEyobmamo
>>Click here to continue<<
