Warning: mkdir(): No space left on device in /var/www/hottg/post.php on line 59

Warning: file_put_contents(aCache/aDaily/2025-07-19/post/Dreyob/--): Failed to open stream: No such file or directory in /var/www/hottg/post.php on line 72
የማይሞላው ቀዳዳ @Dr. Eyob Mamo
TG Telegram Group & Channel
Dr. Eyob Mamo | United States America (US)
Create: Update:

የማይሞላው ቀዳዳ

በሰጣችሁት ቁጥር የማይሞላ፣ የማይጠግብና ተጨማሪ የሚጠይቅ አመለካከት ያለው ሰው አጋሟችሁ ከሆነ ብቻችሁ አይደላችሁም፡፡

አንዳንድ በሕይወታችን የሚገኙ ሰዎች ፈቅደንና ወደን ማፍሰስ የምንችለውን ነገር ሁሉ በእነሱ ላይ እናፈሳለን፡፡ ቢደክመንም፣ ቢሰለቸንም አምነንበት እንደሸክማችንና እንደግዴታችን ስለተቀበልናቸው የፍቅራችን ጥልቀትና የደስታችን ብዛት ከሸክሙ ክብደት ስለሚልቅ እንገፋበታለን፡፡

አንዳንድ ጊዜ ግን በፍጹም ግዳጅና ሃላፊነት የሌለብንን ሰዎች የማይጠግብ ፍላጎት በመመገብ እንዝላለን፡፡ እንዳንገፋበት ዝለናል፣ እንዳናቆመው የውሸት ሃላፊነት ስሜት፣ ይሉኝታና “ሰዎችን እንዳላስቀይም” የሚሉ ትብታቦች ይይዙናል፡፡

ከሚከተሉት አይነት በሰጣችኋቸው ቁጥር የጥፋተኝነት ስሜት እየተሰማችሁ ጨምራችሁ እንደትሰጧቸው ከሚጫኗችሁ ሰዎች ዛሬ ፈታ እንድትሉ ላደፋፍራችሁ፡፡ (በቅድሚያ ግን ምናልባት እኛው ራሳችን ላይ እነዚህ ባህሪዎች እንዳሉና እንደሌሉ መመልከታችንን አንዘንጋ)

1. ለማስደሰት በጣራችሁ ቁጥር ፈጽሞ የማይደሰቱና “ተጎድቻለሁ” የሚያበዙ፣

2. ገንዘብና ቁሳቁስ በሰጣችኋቸው ቁጥር ልክ ግዴታ እንዳለባችሁ ሳያመሰግኑ ሌላ የሚፈልጉ

3. ይቅርታ በጠየቃችኋቸው ቁጥር ሌላ ክስ፣ ፍርድና ኩነኔ ይዘው የሚመጡ፣

4. ትኩረት በሰጣችኋቸው ቁጥር ሁል ጊዜ በቂ ጊዜ እንዳልተሰጣቸው የሚነጫነጩ፡፡

የማይረካ ፍላጎት (Appetite) ያለበት ሰው በሰጠነው ቁጥር ፍላጎቱ እየጨመረ ስለሚሄድ ከዚህ ቀውስ የሚድነው ሲከለከል ብቻ ነው፡፡ ምናልባት ለእንደዚህና ለመሰል አይነት ሰዎች መድሃኒቱ፣ ለእነሱ ያለንን ፍቅርና አክብሮት ሳንለቅ አምጡ አምጡ የሚለውንና በፍጹም የማይረካውን ፍላጎታቸውን አንደኛውን ከልክሎ በማስራብ እንዲሞት ማድረግና ወደጤናማው የፍላጎት ልክ እንዲመለሱ ማገዝ ሳይሆን አይቀርም፡፡

https://hottg.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

78👍32

>>Click here to continue<<

Dr. Eyob Mamo

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)

Warning: Undefined array key 3 in /var/www/hottg/function.php on line 115

Fatal error: Uncaught mysqli_sql_exception: Can't create/write to file '/tmp/#sql-temptable-a06e-533113-206f.MAI' (Errcode: 28 "No space left on device") in /var/www/hottg/function.php:216 Stack trace: #0 /var/www/hottg/function.php(216): mysqli_query() #1 /var/www/hottg/function.php(115): select() #2 /var/www/hottg/post.php(351): daCache() #3 /var/www/hottg/route.php(63): include_once('...') #4 {main} thrown in /var/www/hottg/function.php on line 216