TG Telegram Group Link
Channel: Mental wellness የአእምሮ ጤና
Back to Bottom
ከሚያስገርሙኝ ሀኪሞች-ግብፃዊው ዶ/ር አብዱልረዛቅ ከድር
==========================
ጅማ ዩኒቨርሲቲ ህክምና ትምህርት ቤት የሚያስተምሩ ግብፃውያን መምህራን ነበሩ። በተለይ የሚያስተምሩት ከሆስፒታል በፊት ያሉትን ሳይንሶች (Pre-clinical sciences) ነው። አብዛኞቹ በጣም ጎበዞች ነበሩ። በተለይ ዶ/ር አብዱልረዛቅ ለማስተማር ያለው ፍቅር፣ የሚሰጣቸው ምሳሌዎች፣ ጨዋታ አዋቂነቱ፣ ፅንሰ ሀሳብ ብቻ ሳይሆን ተግባራዊ ፋይዳ (Clinical implications) እያስደገፈ ፊዚዮሎጅን (Human physiology) ሲያስተምር ያለው ሁኔታ ከስንት አመታት በኋላ አሁንም አይረሳኝም።

ዶ/ር አብዱልረዛቅ አንደኛው ክፍል ሲያስተምር ሌላኛው ግብፃዊ( ስሙ ጠፋኝ) ደግሞ ሌላኛውን ክፍል ያስተምር ነበር። ሌላኛው አስተማሪ ለተማሪዎች ከረሜላ ይሰጥ ነበር። ዶ/ር አብዱረዛቅ በነገር ሸንቆጥ ሲያደርገው "እኔ የማስተምረው አንደ አንዳንድ አስተማሪዎች ከረሜሎ-Vascular ሳይሆን ካድዲዮ ቫስኩላር (Cardio vascular ) ነው።" ይል ነበር።

በነገራችን ላይ ህክምና ትምህርት ቤት በየዲፓርትመንቱ ጎበዝ የሆኑ ነገር ግን የማይዋደዱ ሲንየሮች አሉ። እደግመዋለሁ በየዲፓርትመንቱ!!!!! (እሱን ሌላ ጊዜ በዝርዝር 'የዝሆኖቹ ትግልና የሬዚደንቶች መከራ' በሚል ርእስ እመለስበታለሁ።😂😂)

ዶ/ር አብዱልቃድር ፊዚዮሎጂን ፈትፍቶ ነው የሚያስተምረው። እሱ አቴንዳንስ አይዝም። የሱን ትምህርት ብትቀር አንተ ይጎልብሀል። ፊዝዮሎጂን ብዙዎች እንዲወዱ ያደረገ መምህር ነው። የምታስታውሱ እስቲ ጨምሩበት።

Fond rememberances!!!!!
ረጅም እድሜ ከጤና ተመኘሁ!!!
ወርሃዊው የሜንታል ሄልዝ አዲስ መርሃ ግብር ቅዳሜ ታህሳስ 26 ቀን 2017 ዓም አትላስ አካባቢ በሚገኘው በአዶር አዲስ ሆቴል ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ ይደረጋል::

የዚህ ወር ርዕስም፡- “ቦርደርላይን ፐርሰናሊቲ ዲስኦርደርን መረዳት” የሚል ሲሆን የዚህ ወር እንግዳችን አቶ ጴጥሮስ ሃጎስ ናቸው፡፡

ለመታደም ይህን መስፈንጠሪያ ይጫኑና ይመዝገቡ፡፡
https://forms.gle/ErdfV7uCCR2Y3Lzs8

የማስታወሻ መልእክት እና የቦታውን አቅጣጫ ምልክት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይከተሉ፡፡
https://hottg.com/mhaddisababa
ወርሃዊው የሜንታል ሄልዝ አዲስ መርሃ ግብር ቅዳሜ ጥር 24 ቀን 2017 ዓም አትላስ አካባቢ በሚገኘው በአዶር አዲስ ሆቴል ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ ይደረጋል::

የዚህ ወር ርዕስም፡- “ናርሲስቲክ ፐርሰናሊቲ ዲስኦርደርን መረዳት” የሚል ሲሆን የዚህ ወር እንግዳችን አቶ ጴጥሮስ ሃጎስ ናቸው፡፡

ለመታደም ይህን መስፈንጠሪያ ይጫኑና ይመዝገቡ፡፡
https://forms.gle/mNTB3tYLfjXekzPu6

የማስታወሻ መልእክት እና የቦታውን አቅጣጫ ምልክት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይከተሉ፡፡
https://hottg.com/mentaladdis
We're thrilled to announce that Ease mind care a facility providing in person and online mental health services has made it to the finals of the Great Rift Valley Summit competition!
• Vote for Ease mind care
Please take a moment to vote for us at: https://vote.grvsummit.com/
Every vote brings us closer to making a bigger impact in a mental healthcare and achieving our vision. Thank you for your continued support together, we can make this happen!
የሰይፉ ህመም ምንድነው?
=================
ሰይፉ ፋንታሁን ከዶ/ር ፈቃደስላሴ ጋር ያደገው ቃለመጠይቅ ብዙ ቁምነገሮች የተነሱበት ነው። ሊያልቅ አካባቢ ሰይፉ "የሚጨንቀኝ ነገር አለ። እዚሁ ልታከም።" አለ። ቀጠለና "የኔ ችግር ምን መሰላችሁ? ሰዎች የሆነ ህመም ከታመሙ ይጋባብኛል። የሆነ ሰው በኩላሊት ህመም ሞተ ሲባል ኩላሊቴን ያመኛል። የሆነ ሰው 'ካንሰር አለብኝ፤ ሲጀምሬኝ ድዴ ይደማል ነበር።'ሲለኝ ማታውኑ ጥርሴን ስፍቅ ድዴ ደማ። ሰዎች የሚነግሩኝ ነገር ወዲያው ይጋባብኝና ያንን እነሱ ያሉኝን ስሜት አደምጠዋለሁ። ህመሜ ምንድነው?" ብሏል።

ሰይፉ ከገለፀው ምልክት ጋር ተቀራራቢ የሆነው ህመም Illness Anxiety Disorder ይባላል። ይሄ ህመም ያለባቸው ሰዎች በዋናነት በሽታ ቢኖርብኝ ወይም ቢይዘኝስ የሚል ለረጅም ጊዜ (ቢያንስ ለ6 ወራት) የሚቆይ ፍርሀት አለባቸው። በዚህ የተነሳ አንዳንዶቹ ተደጋጋሚ ምርመራ ለማድረግ የተለያዩ ዶክተሮች ጋር ይሄዳሉ። Doctor shopping ይባላል። አንዳንዶቹ ደግሞ "ተመርምሬ የሆነ በሽታ አለብህ ብባልስ?" ብለው ስለሚፈሩ ሀኪም ጋር መታየትም ሆነ ምርመራ ማድረግ አይፈልጉም። እነዚህኞቹ "Care avoiding type" ይባላሉ።

የምንቀርባቸው ሰዎች ከባድ ህመም ሲያጋጥማቸው እነሱ ሲሰማቸው የነበሩት ስሜቶች ለተወሰነ ጊዜ መሰማት ወይም ያመማቸው ህመም "ቢኖርብኝስ?" ብሎ መፍራት እስካልተደጋገመ ድረስ ኖርማል ነገር ነው።

ሰይፉ በቃለመጠይቁ ላይ የገለፀው ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ስሜት እንጂ ስራና ማህበራዊ ህይወት ላይ ተፅእኖ የሚያመጣ ጭንቀት አይደለም። በተጨማሪም ከጭንቀቱ የተነሳ አላስፈላጊ ተደጋጋሚ ምርመራዎች ስላላደረገ ወይም ከፍርሀቱ የተነሳ ተገቢውን የColonscopy ምርመራ ፈርቶ ስላልተወ Illness Anxiety Disorder ወይም ሌላ ህመም አለበት ማለት የሚያስችል መረጃ አልገለፀም።

ይልቁኑ ከ50 አመት በኋላ Colonoscopy ማሰራት እንደሚያስፈልግ በተግባር ማስተማሩ የሚያስመሰግን ነው። ዶ/ር ፈቃደስላሴም ጊዜውን አጣብቦ ስለሚያስተላልፋቸው በጣም ጠቃሚ መረጃዎች ምስጋና ይገባዋል።

ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው
ከሚያስገርሙኝ ሀኪሞች- ዶ/ር ሰይፉ አለሙ
===========================
ጅማ ዩኒቨርሲቲ ህክምና ስንማር ዶ/ር ሰይፉ ቀዶጥገና 'ስፔሻላይዝ' እያደረገ ነበር። ዶ/ር ሰይፉ ሁልጊዜ ፅድት ብሎ ነው ሆስፒታል የሚመጣው። የሚሰራው ቀዶጥገናም እንደአለባበሱ ፅድት ያለ (Neat) ነው። የአጥንት ቀዶ ጥገና ስንማር እንወራረድ ነበር። POP ወይም (በተለምዶ ጄሶ የሚባለው) ከተሰራላቸው ታካሚዎች መካከል ፅድት ብለው (Neat ሆነው) የተሰሩትን እናይና ሄደን የሰራው ሀኪም የፃፈውን መረጃ (Procedure note) ስንመለከት ብዙ ጊዜ ዶ/ር ሰይፉ ነው የሰራቸው። በቃ አይተህ ትለያቸዋለህ።

ዶ/ር ሰይፉ ለጥቃቅን ነገሮች ሳይቀር ትኩረት የሚሰጥ (Meticulous) የቀዶጥገና ሀኪም ነው። የቀዶ ጥገና ሰፔሻላይዜሽኑን ካጠናቀቀ በኋላ በህፃናት ቀዶ ጥገና ሰብስፔሻላይዝ አድርጎ በጅማ ዩኒቨርሲቲ እያገለገለ ይገኛል። His precision and gentle hands are what pediatric surgery needs. ቀዶጥገና ለመስራት ይቅርና መርፌ ለመውጋት እንኳን የሚያሳሱት ህፃናት በእሱ እጆች እንደሚታከሙ ሳስብ ደስ ይለኛል።

ዘንድሮ በተካሄደው የኢትዮጲያ ህፃናት ቀዶህክምና ማህበር ዶ/ር ሰይፉ ለዘርፉ ላበረከተው አስተዋፅኦ ሽልማት አበርክቶለታል።

እንኳን ደስ አለህ!!!!! Well deserved!!!!!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው
HTML Embed Code:
2025/06/26 08:12:06
Back to Top