TG Telegram Group Link
Channel: Doctor Alle 8809/ዶክተር አለ 8809
Back to Bottom
#የጭንቀት #ምንጮች #ምንድን #ናቸው?

👉👉የጭንቀት ምክኒያቶች በርካታ ናቸው፡፡ ሆኖም በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች ለይቶ ማየት ይቻላል፡-
1. ስነ ልቦናዊ መንስሄዎች
2. አካላዊ

1.#ከስነ #ልቦናዊ #ምንጮች፦ በስራ ቦታ በሚፈጠር የሥራ ጫና፣ የሥራ አሰራር ግልፅነት ማጣት፣ ከሚወዱት ሰው ጋር የሚፈጠር ችግር፣ መሰረታዊ የኢኮኖሚ ግዴታዎችን መወጣት አለመቻል፡- ለምሳሌ የቤት ኪራይ፣ አስቤዛ፣ ወርሃዊ የመብራት ክፍያ ወዘተ…፣ ለአዳዲስ ነገሮች መዘጋጀት፡- ለምሳሌ ልጅ መወለድ፣ አዲስን ስራ መያዝ፣ የትራፊክ መጨናነቅ፣ ከፍተኛ ድምፅ…

2. #አካላዊ #መንስሄዎች፦ ህመም፣ ከፍተኛ የአየር ሁኔታ፡- ለምሳሌ ከባድ ሙቀት ወይም ከባድ ቅዝቃዜአካላዊ ህመም፣ እንቅልፍ ማጣት፣ ከመጠን ያለፈ አልኮል መጠጣትና ሲጋራ ማጨስ በሰውነት ላይየሚፈጥሩት ጫና ወዘተ ናቸው።

👉👉የጭንቀት ውጤቶች ምንድን ናቸው?

የሰውነት ድካም
ከፍተኛ የራስ ምታት
ብስጭት
የምግብ ፍላጎት መዛባት
የማስታወስ ችሎታ መቀነስ
ለራስ የሚሰጥ ዋጋ ወይም ክብር መቀነስ(low self-esteem)
ከማህበራዊ ህይወት መገለል
የ ደም ግፊት መጨመር
ትንፋሽ ማጠር
የወሲብ ፍላጎት መቀነስ
የእንቅልፍ መዛባት
የጨጓራና አንጀት ስርዓት መዛባት
የልብ ህመም
የቆዳ ችግር (skin disorders)

👉👉ጭንቀት ለስነልቦናዊ ቀውሶች ለምሳሌ፡- ለፍርሃትና ለድብርት ይዳርጋል፡፡

👉👉 ጭንቀትን ለመቆጣጠር የሚከተሉትን መፍትሄዎች ይጠቀሙ።
በውስጣችን የሚያቆጠቁጠውን የተስፋ ቢስነት ስሜት ማወቅ
የቁጣ ስሜቶቻችንን መለየት
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ
ማኅበራዊ ሕይወት ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ
የሚወዱትን ሥራ መሥራት
አስቂኝ ፊልሞችንን መመልከት
ራስን አለማማረር
ባለሙያ ማማከር
0911233656/0911799754
✍️ #ጭንቀት እና #ችግሮቹ
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
♥️♥️#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥️♥️
♥️♥️ውድ የዶክተር አለ ተከታታዮች ዛሬ ይዘን የቀረብነው ፁሁፍ ስለ ጭንቀት ሲሆን ማንም ሰው በህይወት ዘመኑ ሳይጨነቅ ሙሉ ህይወቱን ሊቀጥል አይችልም ፡፡ ጭንቀት የኑሮ አካል ነው፤ ነገር ግን ጭንቀት የበዛና ተደጋጋሚ ሲሆን ጤናን ወደሚያሰጋ ደረጃ ሊቀይር ይችላል። ከጭንቀት ጋር በተያያዘ ከስነ-ልቦና ባለሙያ ጋር ማማከር ከፈለጉ ዶክተር አለ 8809 ላይ እየደወሉ መፍትኤውን እንመካከር፡፡
🔵 በጭንቀት ምክንያት ስለችግሩ ማሰላሰል መፍትሄ ላይ እንድንደርስ ምክንያት ሊሆን ይችላል። ነገር ግን በጭንቀት ምክንያት ማከናወን የምንፈልጋቸውን ነገሮች መፈጸም እንኳ ስንቸገር ለጤና ችግር እንጋለጣለን።
🔵 #ጭንቀት #እና #ፍርሃት #የሚከተሉትን #ባህሪዎች #ሊያስስትሉ #ይችላል
🔹 በቂ እንቅልፍ አለማግኘት
🔹 ነጭናጫ መሆን (የባህሪ ለውጥ)
🔹 ስራን በአግባቡ አለመስራት
🔹 መጠጣት እና ማጨስ
🔹 የአመጋገብ ስርአት መዛባት
🔵 #በጭንቀት ግዜ የሰውነት ሲምፓታቲክ ነርቭ ስርአት ስራት ይጀምራል። ይህም የሚከተሉት
የሰውነት ለውጦች ያስከትትል ፡-
🔹 የልብ ምት መጨመር
🔹 በፍጥነት መተንፈስ
🔹 የትንፋሽ እጥረት
🔹 ማዞር
🔹 ራስ ምታት
🔹 ማቅለሽለሽ
🔹 የጡንቻ ውጥረት
Follow my tic toc page
#በተደጋጋሚ #በሆድ #ጥገኛ #ትላትል #እጠቃለሁ #ምን #ይሻላል?
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን
#የሆድ ጥገኛ ትላትሎች በየትኛዉም የእድሜ ክልል የሚከሰቱ ሲሆኑ በዋናነት ክብ እና ጠፍጣፋ በመባል በሁለት ይከፈላሉ፡፡የሆድ ጥገኛ ትላትሎች ወደ ሰዉነት የሚገቡት በቆዳ፣ በአፍንጫ እና በአፍ በኩል በእንቁላል መልኩ ሲሆን ወደ ሰዉነታችን ከገቡ በኃላ በአንጀታችን ላይ ይራባሉ፡፡
#ለሆድ #ጥገኛ #ትላትል #መንስኤዎች
🔹 በንፅህና ያልተዘጋጁ ምግቦችን መመገብ
🔹 የተበከለ ዉሃ
🔹 በደንብ ያልበሰለ ምግብ መመገብ
🔹 በባዶ እግር መሄድ
🔹 የግል ንፅህና አለመጠበቅ
🔹 የበሽታ መከላከል አቅም መቀነስ
🔹 በጥገኛ ትላትሎች ከተያዙ የቤት እንስሳ ጋር መኖር
#ምልክቶች
🔹 የሆድ ድርቀት ወይም ተቅማጥ
🔹 የምግብ ፍላጎት መቀነስ/መጨመር
🔹 ማቅለሽለሽና ማስመለስ
🔹 የሆድ ህመም/ቁርጠት
🔹 በሰገራ ላይ የሆድ ጥገኛ ትላትሎችን መታየት
🔹 የሆድ መነፋት እና ጋዝ መብዛት
🔹 በፊንጢጣ ወይም ብልት ዙሪያ ማሳከክ
#የሆድ #ጥገኛ #ትላትሎችን #መከላከል #መንገዶች
🔹 ፍራፍሬዎች ከመመገብ በፊት በደንብ ማጠብ
🔹 ከመመገብ በፊት ምግብን በደንብ ማብሰል
🔹 ፈልቶ የቀዘቀዘ ወይም የተጣራ ዉሃ መጠቀም
🔹 ንፅህና መጠበቅ
🔹 ከመመገብ በፊት፣ ምግብ በሚያበስሉበት ወቅትና ከመፀዳጃ ቤት መልስ እጅን በዉሃና ሳሙና መታጠብ፤ እንዲሁም የቤት እንስሳዎችን ከነኩ በኋላ እጅን በደንብ መታጠብ፡፡
🔹 በባዶ እግር አለመሔድ እና ንጽህናዉ በተጠበቀ/በታከመ ገንዳ ዉስጥ መዋኘት
#ህክምና
🔹ለሆድ ጥገኛ ትላትሎች መኖራቸዉ በሰገራ ምርመራ ከተረጋጋጠ በኋላ ለተገኘዉ የትላትል አይነት መድሐኒት እንዲወስዱ ይደረጋል፡፡
👉 👉 የሆድ ጥገኛ ትላትሎች በአግባቡ ካልታከመ እና አመጋገብ ካላስተካከልን ከፍተኛ የአንጀት ጉዳት ያስከትላል፡፡
✍️ እውቁ ፀሐፊ ፓውሎ ኪሊዮ እዲህ ይላል፤


✍️ ሰዎች እንዲረዱህ ከመጠን በላይ አትድከም ሰዎች እንደሆኑ የሚሰሙት መስማት የሚፈልጉትን ብቻ ነውና።

✍️ አንድቀን ከእንቅልፍህ ስትነቃ ጊዜህ አልቆ ልታገኘው ትችላለህ፤ ስለዚህ ልታደርገው የምትፈልገውን ነገር አሁኑኑ አድርገው።

✍️ ስኬታማ ለመሆን ከፈለክ አንድ ሕግ አክብር ፈጽሞ ራስህን አትዋሽ።

✍️ የህይወት ምስጢሩ ሰባት ጊዜ ወድቆ ስምንት ጊዜ መነሳት ነው።

✍️ ሕልምህ እንዳይሳካ የሚያደርግ አንድ መጥፎ ነገር አለ "አይሳካልኝም" የሚል ፍርሃት።


✍️ በዓለም ላይ ያለ ማንኛውም ሰው ሊገባው የሚችለው ቋንቋ አለ "ፍቅር "!


✍️ ስትሸነፍ አይደለም የተሸነፍከው በቃኝ ብለህ ስታቆም እንጂ!

✍️ ምንም ምክንያት ከማያሻቸው ነገሮች አንዱ ማፍቀር ነው።

✍️ አንድ ነገር አስታውስ ልብህ ያለበት ቦታ ሀብትህም ተቀምጧል።

🙌መልካም ቀን፤ ቸር ያሰማን፤
✍️ #ለጸጉሮት #ቀለም #ይጠቀማሉ? #እንግዲውስ #እነዚህን #ልብ #ይበሉ!
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹

#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን

የተከበራችሁ የገጻቸን ቤተሰቦች በአሁን ጊዜ ጸጉርን ለማሳመር ሲባል ብዙዎች ቀለም ይቀባሉ ወንድም ይሁን ሴት ሆኖም ግን ያለውን የጎንዮሽ ጉዳ ያተዋሉት አይመስልም እኛም እንደጤና ባለሙያ ግዴታችን ነውና እስኪ አውቃችሁ ትጠነቀቀቁ ዘንድ እነሆ አልን፡፡

📌 ሽበት፡- የጸጉር ቀለሞች በብዛት አሞኒያ እና ፐርኦክሰሳይድ ንጥረ ነገሮች ይይዛሉ፡፡ እነዚህ ኬሚካሎች ደግሞ የጸጉር ተፈጥሯዊ ቀለምን በማሳጣት ሽበት እንዲከሰት እንዲሁም ጸጉር ሳስቶ እንዲሰባበር ያደርጋል፡

📌 የቆዳ አለርጂ፡- የጸጉር ቀለሞች ፓራፌናይልዲአሚን የሚባል አለርጂ አምጪ ንጥረ ነገር ይይዛሉ ይህ ደግሞ ቆዳን እንዲቆጣ፣ እንዲያሳክክ እንዲሁም ቀልቶ እንዲያብጥ ያደርጋል፡፡

📌 በእርግዝና ወቅት፡ ነብሰጡር ሴት በፍጹም የጸጉር ቀለም መጠቀም የለበትም ምክንያቱም ጽንሱን ከማስወረድ ጀምሮ እስከ ካንሰር መከሰት ስለሚዳርግ

📌 አስም፡- ልክ እንደአስም አይነት የመተንፈሻ አለርጂ ችግር ያለባቸው ሰዎች የጸጉር ቀለምን ማሶገድ የግድ ይላቸዋል ምክንያቱም በውስጣቸው የሚይዙት ኬሚካሎች ሳንባን በከባድ ሁኔታ ስለሚጎዳ ነው፡

📌 እርግዝናን ማዘግየት፡- በእርግጥ በዚህ ዙሪያ ብዙ የተደረጉ ጥናቶች ባይኖሩም ነገር ግን እንዳንዶች እንደሚያሳዩት የጸጉር ቀለም እርግዝና ለሚጠብቁ ጥንዶች የማዘግየት ሁኔታ እንዳለው ጠቁመዋል፡፡

📌 የአይን ደም ስሮች መቆጣት፡- አይናችን በብዙ ነገር የተከለከለ ቢሆንም ግን አሁንም ቢሆን ከሰደጋ የጸዳ አይደለም በመሆኑም የአይናችን ደም ስሮች ከሚጎዱበት ዋነኛም ምክንያቶች መሀከል የጸጉር ቀለም ዋነኛው ነው፡፡

📌 ካንሰር፡- አንዳንድ የጸጉር ቀለም የቆዳ ካንሰር አምጪ የሆኑ ኬሚካሎችን በውስጣቸው ስለሚይዙ ጥንቃቄ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡

👉👉 በማንኛውም የጤና ጉዳይ ባለሙያ ማማከር ከፈለጉ የዶክተር አለ 8809 ሀኪሞችን ላይ እየደወሉ የየዕለቱን የጤና ላይ ለውጦችዎን በማማከር ነገ ከሚከሰት የጤና ችግር አስቀድመው ራስዎንና ቤተሰብዎን ይጠብቁ ይንከባከቡ::

👉👉 ከጧት 2 ሰዓት እስከ ማታ 1 ሰዓት ከሰኞ እስከ ሰኞ ቢደዉሉ የዶክተር አለ ሀኪሞች ሊያማክሩዎ በመስመር ላይ ይገኛሉ!!!
✍️ #ስለ #ማር #ማወቅ #ያለብዎ #ነገሮች
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
♥️♥️#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥️♥️
ንቦች እንዴት ነው ማር የሚሰሩት?
🔺 አጀማመሩ ንብ ከአበባ ኔክታር ስትመጥ ነው። ኔክታሩን ሃኒኮምብ ወደሚባል ክፍል ወስዳ ታጠራቅማለች። እዛው በተቀመጠበት ዙሪያ ሌሎች ንቦች ሲበሩ የሚፈጥሩት የመርገብገብ ነፋስ ኔክታሩን በማድረቅ ወደ ማር ይቀይረዋል። ኔክታሩ ወደ ማር እንደተቀየረ የተቀመጠበት ሴል በሰም ይደፈናል። ንቦች አንድ ፓውንድ ማር ለማምረት 2ሚልየን አበባ መቅሰም አለባቸው።
ማር ወይስ ስኳር?
🔺 ማር ይሻላል ወይስ ስኳር አከራካሪ ርእስ ነው። ነገር ግን ማር ከስኳር የሚሻልባቸው ገጽታዎች አሉት። ማር በውስጡ ጸረኦክሲዳንቶች፣ አሚኖ አሲዶች እና ቫይታሚኖችን ይይዛል። አንድ የሻይ ማንኪያ ማር 21 ካሎሪ ሲኖረው አንድ ሻይ ማንኪያ ስኳር 16 ካሎሪ ይይዛል።
ማር ሳይበላሽ ምን ያህል ግዜ ይቆያል?
🔺 ማር ረጅም ህይወት አለው። ሳይንቲስቶች ቢበላ ችግር የማያመጣ ለሺህ አመታት የተቀመጠ ማር ማግኘት ችለዋል። ማር በተዘጋ እቃ ውስጥ ከተቀመጠ በቀላሉ አይበላሽም። ማር በተፈጥሮ እርጥበቱ ዝቅተኛ ነው፣ ጠንካራ አሲዳማ ይዘት አለው፣ እንዲሁም ጸረ ባክቴሪያ ንጥረነገሮችን የያዘ ነው። በተዘጋ እቃ ደረቅ ቦታ ውስጥ በማስቀመጥ ከመበላሸት መከላከል ይቻላል።
ማር ምን ምን የጤና ጥቅሞች አሉት?
🔺 የብርድ ስሜትን ያጠፋል፡- የተለያዩ ጥናቶች እንደሚናገሩት ማር የብርድ ስሜትን ለመከላከል እንደሚጠቅም ነው። በልጆች ላይ ሳል ለመቀነስ እንዲሁም የተሻለ እንቅልፍ እንዲያገኙ ይረዳል።
🔺 ቁስልን ያድናል:- ማርን ቁስል እና ቃጠሎ ላይ መቀባት የተለያዩ ቦታዎች እንደ ባህላዊ መድሃኒት ይቆጠራል። ጥንትዊ ግብጽ ውስጥ እንደ መድሃኒት ይውል ነበር። ማር ውስጡ ባክቴሪያ የሚዋጉ፣ ቁስል የሚያድኑ፣ ኢንፌክሽን የሚከላከሉ እና እብጠትን የሚቀንሱ ንጥረነገሮችን የያዘ ነው። ነገር ግን ለጥንቃቄ ሲባል በመድሃኒት መልክ የተዘጋጀ ማርን ገዝቶ መጠቀም ይመከራል። ቁስሉ ከባድ ከሆነ ዶክተርን ማማከር ይመከራል።
🔺 የንብ መነደፍ ሲያጋጥም፡- ህመሙን ለመቀነስ እና እብጠቱን ለመቀነስ ይረዳል፡፡
🔺 የልብን ጤንነት ይጠብቃል፡- አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ማር የደም ግፊትን እና የደም ቅባትን መጠንን ይቀንሳል፤ የልብ ምትን ይቆጣጠራል፤ የጤነኛ ሴሎችን ሞት ይከላከላል፡፡
🔺 በህፃናት ላይ የሚከሰት ሳልን ይቀንሳል፡- ከ 1 አመት በላይ ለሆኑ ህጻናት ማር እንደ ተፈጥሯዊ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የሳል ህክምና ሊያገለግል ይችላል፡፡
🔺 በቀላሉ በአመጋገብ ስርአታችን ውስጥ መጨመር ይቻላል፡- ማርን በመጠቀም እርጎን ወይም መጠጦችን ለማጣፈጫነት በመጠቀም፣ በብዙ የምግብ አዘገጃጀት ውስጥ እንደ አንድ ንጥረ ነገር በመጨመር፣ ከሻይ ጋር በመጠጣት እና እንዲሁም ብቻውን በመዋጥ መጠቀም ይቻላል፡፡
አንድ አመት ያልሞላቸው ልጆች ማር መመገብ የለባቸውም። ማር በውስጡ ህጻናትን የሚያሳምም ቦቱሊዝም የተባለ ንጥረነገር ሊይዝ ይችላል፡፡
ማር ዘርፈ ብዙ የጤና ጥቅሞች ቢኖሩትም የስኳር አይነት መሆኑን ግን አስታውሱ፤ ስለዚህ እሱን መጠቀም የደምዎን የስኳር መጠን እንዲጨምር ያደርጋል፡፡
በተጨማሪም ከፍተኛ መጠን ያለው ማር ለረጅም ጊዜ ያለማቋረጥ መመገብ ለክብደት መጨመር አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡ እንደ ዓይነት 2 የስኳር በሽታ ወይም የልብ ሕመም ያሉ በሽታዎችን ይጨምራል። ስለዚህ, ከዝቅተኛ እስከ መካከለኛ አወሳሰድ ይጠቀሙ፡፡
HTML Embed Code:
2024/04/20 10:42:58
Back to Top