TG Telegram Group & Channel
Andu Getachew .( Poems ) ግጥሞች | United States America (US)
Create: Update:

እውነቱ ይሄ ነው ላልሽኝ '
.
መቼም ተስፈኛ ሰው እንብርት የለውም' ፤ ብለሽ ነው እውነቱን ያጋትሽኝ?
መራር ቅጠል እንደተቀባ የእናት ጡት፣ ከለመድኩት ያስጣልሽኝ ?
በሲቃ አስጨንቀሽ፣ በእንግብግቢት የወጠርሽኝ ?
የአንዱ ሃቅ፣ለሌላው ሚናቅ ለሚሆን፣
ለኔ እውነቱ ይነገራል አሁን ?!
.....
በኛ የህይወት ጥያቄ ስር፣
አለ አንድ ባዶ መስመር፣ _____?

(ከላይ ያለውን ) ባዶ ቦታውን፣ በራሳችን ብንሞላውስ? አንዳንዴ፤ ባዶ ቦታውን መተው መልስ ቢሆንስ?
.
አንቺ አውራ-- እውነት፤ የሃቅ ቆጥ ላይ የወጣሽው
'እውነቱ ይኼ ነው' ብለሽ …. ፣ ውስጤን አትዘዥው.
እውነት ማለት ….
በራስ ምላስ፣ ለራስ የሚያወጉት አይደል?
ያንቺን ካንቺው ያዥው፡፡.
.
እንደኔ እንደኔማ ዝምታው ይሻላል፤ ወይ ውሸቱ ይበጃል፤ ክፍቱን ቢያረጉትም፣
ከ'ሳት ቢያወርዱትም፣
ዓመት ቢያቆዩትም፣ ክፋት ካሰቡበት ሃቅ ልብ ይፈጃል::

አንቺ ዳሞትራ፣
ራቁት ህልሜን በሃቅ ድር አሰርሽው፤
ፀዳል ተስፋዬን፤በእድፌ አጠብሽው፤
በሰቀቀን አጨለምሽው:: .
የአንዱ እውነት ለሌላው ትፋት ለሚሆን
ምናለ ዝም ብትይ አሁን ?
.

እውነቱ ይሄ ነው ላልሽኝ '
.
መቼም ተስፈኛ ሰው እንብርት የለውም' ፤ ብለሽ ነው እውነቱን ያጋትሽኝ?
መራር ቅጠል እንደተቀባ የእናት ጡት፣ ከለመድኩት ያስጣልሽኝ ?
በሲቃ አስጨንቀሽ፣ በእንግብግቢት የወጠርሽኝ ?
የአንዱ ሃቅ፣ለሌላው ሚናቅ ለሚሆን፣
ለኔ እውነቱ ይነገራል አሁን ?!
.....
በኛ የህይወት ጥያቄ ስር፣
አለ አንድ ባዶ መስመር፣ _____?

(ከላይ ያለውን ) ባዶ ቦታውን፣ በራሳችን ብንሞላውስ? አንዳንዴ፤ ባዶ ቦታውን መተው መልስ ቢሆንስ?
.
አንቺ አውራ-- እውነት፤ የሃቅ ቆጥ ላይ የወጣሽው
'እውነቱ ይኼ ነው' ብለሽ …. ፣ ውስጤን አትዘዥው.
እውነት ማለት ….
በራስ ምላስ፣ ለራስ የሚያወጉት አይደል?
ያንቺን ካንቺው ያዥው፡፡.
.
እንደኔ እንደኔማ ዝምታው ይሻላል፤ ወይ ውሸቱ ይበጃል፤ ክፍቱን ቢያረጉትም፣
ከ'ሳት ቢያወርዱትም፣
ዓመት ቢያቆዩትም፣ ክፋት ካሰቡበት ሃቅ ልብ ይፈጃል::

አንቺ ዳሞትራ፣
ራቁት ህልሜን በሃቅ ድር አሰርሽው፤
ፀዳል ተስፋዬን፤በእድፌ አጠብሽው፤
በሰቀቀን አጨለምሽው:: .
የአንዱ እውነት ለሌላው ትፋት ለሚሆን
ምናለ ዝም ብትይ አሁን ?
.


>>Click here to continue<<

Andu Getachew .( Poems ) ግጥሞች




Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)