TG Telegram Group Link
Channel: Tech news📱📲
Back to Bottom
[ Photo ]
የኮምፒዩተር ኮድ በመጻፍ ከሰዎች ጋር የሚፎካከረው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓት

አልፋኮድ የተባለ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓት የኮምፒዩተር ኮዶችን በመጻፍ በተደረገ ውድድር አበረታች ውጤት ማስመዝገቡ ተገለፀ፡፡

ሥርዓቱ ኮድፎርስ ተብሎ በሚታወቀው የኮምፒዩተር ፕሮግራሚንግ የውድድር መድረክ ላይ ከሰዎች ጋር በመፎካከር ጥሩ ውጤት ካስመዘገቡት ሃምሳ አራት በመቶ ቀዳሚ ተፎካካሪዎች ውስጥ መካተት መቻሉን የዲፕ ማይንድ ድረ-ገፅ አስነብቧል፡፡

በመድረኩ በተመረጡ አስር ፉክክሮች ላይ የተሳተፈው አልፋኮድ በመካከለኛ ሁኔታ በሚመደብ የተፎካካሪነት ደረጃ መገኘት መቻሉ ተገልጿል፡፡ ይህም ለፉክክር የበቃ የመጀመሪያው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኮድ አመንጪ ሥርዓት እንደሚያደርገው ዘገባው ያስረዳል፡፡

ይህ ሥርዓት የኮምፒዩተር ኮዶቹን ለማመንጨት ትራንስፎርመር ቤዝድ ላንጉዬጅ የተባለውን ስልት እንደሚጠቀም መረጃው ጠቁሟል፡፡

ሥርዓቱ የበለፀገው በጉግል ባለቤትነት በሚተዳደረው ዲፕማይንድ ኩባንያ ነው፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩ ተወዳዳሪዎች የሚሳተፉበት ይህ መድረክ በጥልቀት ማገናዘብን፣ አመክንዮን፣ ስልተቀመሮችን፣ ኮድ እና ተፈጥሯዊ ቋንቋን አዋህዶ መረዳትን ይጠይቅ እንደነበር ተመላክቷል፡፡
የፌስቡክ አካውንትዎን ደህንነት ለመጠበቅ ሊወሰዱ የሚገቡ የጥንቃቄ እርምጃዎች❗️

1. የይለፍ-ቃልዎን ደህንነት ማረጋገጥ

#_የፌስቡክ አካውንቶን ለሌላ ማንኛውም የኦንላይን አገልግሎት ላይ አይጠቀሙ፤

#_ የይለፍ-ቃልዎን በፍፁም ለሌላ ሰው አያጋሩ፤

#_የሚጠቀሙበት የይለፍ-ቃል ለመገመት አዳጋች የሆነ፣ በፍጹም የእርሶን ስም እና የተለመዱ ቃላትን ያልያዘ ሊሆን ይገባል፤

#_የይለፍ-ቃልዎ ፣ኢ-ሜይልዎን፣ የስልክ ቁጥሮን ወይም የልደት ቀንዎን በፍፁም የሚጠቀም መሆን የለበትም፤

2. የሚያስሱትን ድረ-ገጽ መረጃ በፍጹም አያጋሩ

#_አጥቂዎች ፌስቡክ የሚመስል የሐሰት ገጽ ፈጥረው በኢ-ሜይል አድራሻዎና በይለፍ ቃልዎ እንዲገቡ ሊጠይቁዎ ይችላሉ፤

#_ሁልጊዜም መረጃ የሚያስሱበትን ድረ-ገጽ URL ትክክለኝነት ያረጋግጡ፤
አጠራጣሪ ነገር ሲያጋጥሞ www.facebook.com በማፈላለጊያው ላይ በመጻፍ ወደ ትክክለኛው የፌስቡክ ገጽ ለመመለስ ይሞክሩ፤

#_ ከሜታ /Meta/ ወይም ፌስቡክ የሚላክሎትን ኢ-ሜይል በፍጹም ለሌላ ሰው አያጋሩ፣ በተለይም ስለ አካውንቶ ምስጢራዊ መረጃዎችን የያዙ ከሆነ፤

#_ስለፊሺንግ ጥቃት እና ጠንካራ የይለፍ-ቃል አጠባበቅ ላይ ያለዎትን እውቀትና ግንዛቤ በየጊዜው ያሳድጉ፤

3. ኮምፒውተርዎን ለሌላ ሰው የሚያጋሩ ከሆነ የፌስቡክ አካውንቶን ዘግተው መውጣትዎን /Log Out/ ማድረግዎን አይዘንጉ፤

#_ኮምፒውተርዎን ዘግተው ሳይወጡ ወይም መሣሪያዎን ያዋሱ ከሆነም ከርቀት እንዴት መውጣት /Log Out Remotely/ እንደሚችሉ ይወቁ፤

#_ከርቀት ሆነው ለሌላ አካል ካዋሱት ኮምፒውተር ላይ ለመውጣት(log out) ለማድረግ ወደ ፌስቡክ "Security and Login Setting" ሲገቡ ከዚህ በፊት ይገቡባቸው የነበሩ መሣሪያዎችን ዝርዝር የሚያቀርብልዎ ሲሆን ከዚህ ውስጥ የሚፈልጉት መሣሪያ ላይ "Logout" የሚለውን ትዕዛዝ በመጫን መውጣት ይችላሉ፤

4. ከማያውቋቸው ሰዎች የጓደኝነት ጥያቄ ሲላክልዎ አይቀበሉ

#_ጠላፊዎች ሰዎችን ለማጥመድ ሲፈልጉ ሀሰተኛ አካውንት ሊፈጥሩ ይችላሉ፤

#_የጠላፊዎች ጓደኛ መሆን ምን አልባት የእርሶን የፌስቡክ የፊት ገጽን /Timeline/ ሊበክሉ፣ የተለያዩ ጉዳዮችን በገጾ ላይ ሊያጋሩ ወይም በካይ መልዕክቶችን በመልዕክት መቀበያዎ ሊልኩብዎ ይችላሉ፤

5. ከበካይ ሶፍትዌሮች እራሶን ይጠብቁ

#_አጥፊ ሶፍትዌሮች ኮምፒውተሮች፣ ሰርቨሮች /Server/ ወይም የኮምፒውተር ኔትወርክ ላይ ጉዳት ሊጥሉ ይችላሉ፤

#_የተበከለ ኮምፒውተር ወይም መሣሪያ ምን ዓይነት ባህሪያት እንደሚያሳዩ እና እነዚህን በካይ ሶፍትዌሮችን እንዴት ማስወገድ እንደሚችሉ በሚመለከት ያለዎትን እውቀት ያዳብሩ፤

#_ማፈላለጊያዎትን በየጊዜው ያዘምኑ፣ አጠራጣሪ መተግበሪያዎችን እና የማፈላለጊያ ማስታወቂያዎችን ያስወግዱ፤

6. አጠራጣሪ ማስፈንጠሪያዎችን /Links/ ከሚያውቁት ጓደኛ ወይም ድርጅት እንኳ ቢላክልዎ ከመክፈት ይቆጠቡ

#_እነዚህ በፌስቡክ ወይም በኢ-ሜይል የሚላኩ ማስፈንጠሪያዎች /Links/ ሊሆኑ ይችላሉ፤

#_ፌስቡክ ወይም Meta የይለፍ-ቃሎን በኢ-ሜይል እንዲያስገቡ በፍጹም እንደማይጠይቅዎ ይወቁ፤

#_አጠራጣሪ ማስፈንጠሪያ ሲያጋጥሞ ለፌስቡክ ሪፖርት /report it/ ያድረጉ፤

7. ተጨማሪ የደህንነት መጠበቂያ መንገዶችን ይተግብሩ

#_ከማይታወቁ አድራሻዎችና መሣሪያዎች ወደ አካውንትዎ የመግባት ሙከራ ሲደረግ የጥቆማ መረጃ እንዲደርሶ /get alerts about unrecognized logins/ ያድረጉ፤

#_ባለሁለት ደረጃ የማንነት ማረጋገጫ ዘዴ /Set up two-factor authentication/ ይጠቀሙ፤

#_ሌሎች የደህንነት ጉዳዮችን በተመለከተ የፌስቡክ Help & Support ላይ በመግባት ያለዎትን ግንዛቤ በየጊዜው ያሳድጉ፤
አልጄሪያዊው /Hacker/ "ሃምዛ ቢንድላጅ"

በአለም ላይ አሉ ከሚባሉት እጅግ አደገኛ አስር የኮምፒውተር ሃከሮች አንዱ የሆነው አልጀሪያዊው ሃምዛ ቢንድላጅ ኮምፒውተሮችን ሃክ ለማድረግ የሚረዳ ቫይረስ ሰርቶ ኦንላይን መሸጥ ከጀመረበት ግዜ አንስቶ የአሜሪካኑ FBI ከኢንተርፖል ጋር በመተባበር በጥብቅ ሲፈለገው ቆይቶ 2013 ታይላንድ ውስጥ ተይዞ ነበር ወደአሜሪካ የተላከው!

ይህ ወጣት የፔንታገኑን ምክርቤት ቢሮም ሆነ የእስራኤሉን የስለላና የደህንነት ቢሮ ኮምፒውተሮች ሳይቀር ሃክ እንዳደረገና አሜሪካኖች ቀይ መስመር (Red line) የሚሉትን መስመር እንዳለፈ ነው የሚነገረው!

ከዚህ በተጨማሪም ይህ ተአምረኛ ወጣት እስራኤልና አሜሪካ ፍልስጤም ላይ ያላቸውን የተንሸዋረረ አቋም በፅኑ ከመቃወሙም ባለፈ የባንኮቻቸው ኮምፒውተር ውስጥ እንዳሻው እየገባ ከ 4 ቢሊየን ዶላር በላይ በመዝረፍ ለአልጄሪያውያንና ለፍልስጤም የእርዳታ ድርጅት አከፋፍሏል! (4 ቢሊዮን የአንዲት ደሃ አገር አመታዊ በጀት እንደሆነ ልብ ይሏል)

ከዚህ በተጨማሪም የተለያዩ የአውሮፓ ሃገራት ኤምባሲዎችን ሃክ በማድረግ ለአልጄራውያን ወጣቶች ቪዛ በመስጠት የተለያዩ የአውሮፓ ሃገሮች ላይ መኖር እንዲችሉ አድርጓል!

ይህ ወጣት ከ 8 ሺህ በላይ የፈረንሳይ ዌብሳይቶች ፣ ከ1.4 ሚሊየን በላይ ኮምፒውተሮችንና ከ217 በላይ የባንክ አካውንቶችን ሃክ ከማድረግ አልተመለሰም! ራሱም ቢሆን የፈለገበት ሃገር ውስጥ እንደፈለገ እየገባና እየወጣ እንደኖረ ነው እየተነገረ ያለው!

በዚህና በመሰል ከፍተኛ ወንጀሎቹ አማካኝነት ነው የአሜሪካው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሞት የፈረደበት! አልጄሪያውያን ግን ሃምዛን ብሄራዊ ጀግናና የአሜሪካውያንና የእስራኤል የቁም ቅዠት ነው በማለት በማህበራዊ ሚዲያዎች ያሞግሱታል !

የሞት ፍርድ የተፈረደበት የሃያ ሰባት አመቱ ሳቂታው ሃምዛ ቢንድላጅም የታይላንድ ፖሊሶች እጅ ሲገባ እንዲህ ነበር ያለው «I am not a terrorist!»
[ Photo ]
የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ አይነቶች

የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓቶች ማከናወን በሚችሉት ተግባር ጥልቀት እና ስፋት መሰረት ጠቅለል ባለ መልኩ በሦስት ምድቦች ይከፈላሉ፡፡ እነዚህም፡-

#Artificial_Narrow_Intelligence (ANI)
#Artificial_General_Intelligence (AGI)
#Artificial_Super_Intelligence (ASI)

በዚህ ጽሁፍ Artificial Narrow Intelligence (ነጠላ-ተግባር ተኮር አስተውሎት) ወይም በግርድፍ ትርጉሙ ጠባብ አስተውሎት የተባለውን በአጭሩ ለመዳሰስ እንሞክራለን፡፡

የሰው ልጅ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ምርምር እና ትግበራን ከጀመረ አንስቶ በስኬት ተግባር ላይ ያዋለው ይህን የነጠላ-ተግባር ተኮር አስተውሎት መሆኑ ይነገራል፡፡

ሚዲየም በተባለው ድረ-ገጽ ሀተታ መሰረት ነጠላ-ተግባር ተኮር አስተውሎት ትኩረቱ በአንድ ነጠላ ተግባር ላይ ብቻ ነው፡፡ በዚህ አይነቱ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ማሽኖች በተቀመጠላቸው መለኪያ መሰረት በገደብ የሚንቀሳቀሱ በመሆናቸው "ደካማ" አስብሏቸዋል፡፡

ነጠላ-ተግባር ተኮር አስተውሎት በማሽን ለርኒንግ እና ዲፕ ለርኒንግ ታግዞ ባለፉት አስርት ዓመታት በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገብ ችሏል፡፡

ለዚህ የሰው ሰራሽ አስተውሎት አይነት ሲሪ፣ ጎግል አሲስታንት፣ ኮርታና፣ ቼዝ የሚጫወቱ ስልተ ቀመሮች፣ የፊት ገፅታ መታወቂያ ስርዓቶች (facial recognition) እንዲሁም የድምፅ መታወቂያ ስርዓቶች (speech recognition) አይነተኛ ምሳሌ መሆን ይችላሉ፡፡
🔐የAndroid ሚስጢራዊ ኮዶች🔐🗝

1️⃣. Phone information code: *#*#4636#*#*

2️⃣. Factor data reset code: *#*#7780#*#*

3️⃣. Format android phone code:*2767*3855#

4️⃣. Phone camera update code:*#*#34971539#*#*
-Update camera firmware in image
-Update camera firmware in SD card
-Camera firmware version
-Firmware update count

5️⃣. End call power
code:*#*#7594#*#*

6️⃣. File copy for creating backup code:*#*#273283*255*663282*#*#

7️⃣.Service mode code:*#*#197328640#*#*
•*#*#232338#*#* show Wi-Fi Mac address
•*#*#1472365#*#* GPS test
•*#*#1575#*#* another GPS test
•*#*#232337#*#* show Bluetooth device
•*#*#232331#*#* bluetooth test
√ Firmware version information code:
*#*#4986*2650468#*#*
•*#*#1234*#*# PDA and phone
•*#*#1111#*#* FTA SW version
•*#*#2222#*#* FTA HW version
√ Code to launch various factory test
•*#*#0283#*#* packet loop back
•*#*#*0*#*#* LED test
•*#*#0673#*#* or *#*#0283#*#* melody test
•*#*#0842#*#* Device test (vibration and backlight test)
•*#*#2663#*#* Touch screen version
•*#*#2664#*#* Touch screen test
•*#*#0588#*#* Proximity sensor test
•*#*#3264#*#* RAM
information
so these are some working android hack.
የኮምፒውተር 32 ቢት እና 64 ቢት ሲፒዮ ልዩነት እና ጥቅም
ምንድነው?
=======================================
ዛሬ በ32ቢት እና በ64 ቢት ፕሮሰሰር መሃል ያለውን ልዩነት
ይዘን
ቀርበናል ይህ ጽሁፍ ኮምፒውተር ለምትገዙ፤ የምትጠቀሙበትን
ኮምፒውተር/ላፕቶፕ የተጫነበትን ኦፕሬቲንግ ሲስተም ከፍ
(አብግሬድ) ለማድረግ እንዲሁም የምትጭኑትን ሶፍትወዌር
ለመወሰን
ያግዛል፡፡ የኮምፒውተር ሲፒዩ በሁለት አይነት 32 እና 64 ቢት
በሚል
የሚከፈል ሲሆን የፕሮሰሱ አይነት በኮምፒውተር ላይ ምንም
አይነት እክል
የማይፈጥር ቢሆንም የምንጭናቸው ኦፕሬቲንግ ሲስተምና
ሶፍትዌሮች
ይወስኑታል፡፡
1. 32 ቢት ፕሮሰሰር
32 ቢት ፕሮሰሰር ከ1990 ጀምሮ በሁሉም ኮምፒውተሮች ላይ
የሚገኘው ሲሆን የፕሮሰሰር አምራች የሆኑት ኢንቴል እና
ኤኤምዲ እየሰሩ
ለገበያ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ ፡፡ ኦፕሬቲን ሲስተም እና
ሶፍትዌር የሚሰሩ ድርጂቶች 32 ቢት
ፕሮሰሰርን መሰረት በማድረግ ሲሰሩ ከነዚህም ውስጥ
ማይክሮሶፍት ዊንዶውስ 95፣
98 እና ኤክስፒን ሁሉም 32 ቢት ኦፕሬቲንግ ሲስተም ተደርገው
የተሰሩ ናቸው፡፡
32 ቢት ፕሮሰሰር የሆነ ኮምፒውተር 64 ቢት የሆነ ኦፕሬቲንግ
ሲስተም
መጫን የማንችል ሲሆን ምንጊዜም 32 ቢት ፕሮሰሰር መጫን
የሚችለው
32 ቢት የሆነ ኦፕሬቲን ሲስተም እና ሶፍትዌሮች ብቻ ነው፡፡
2. 64 ቢት ፕሮሰሰር
64 ቢት ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር በ1961 አካባቢ
አይቢኤም IBM
7030 Stretch supercomputer የሚባል የሰራ ቢሆንም
እስከ 2000
ድረስ ለቤት መጠቀሚያ ተብለው በሚሰሩ ኮምፒውተሮች ላይ
አልነበረም:: ማይክሮሶፍት 64
ቢት ፕሮሰሰርን የሚጠቀም 64 ቢት ዊንዶ ኤክስፒ ኦፕሬቲንግ
ሲስተም ለገበያ አቀረበ
በመቀጠል ዊንዶ ቪስታ፣ ዊንዶ 7፣ ዊንዶ 8 እና ዊንዶ 10 64
ቢት ፕሮሰሰር የሚጠቀሙ
ባለ 64 ቢት ኦፕሬቲንግ ሲስተም ለገበያ ቀርበዋል፡፡ 64 ቢት
ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር
64 ቢት እና 32 ቢት ኦፕሬቲንግ ሲስተም መጫን የሚችል
ሲሆን 32 ቢት ፕሮሰሰር 64 ቢት የሆነን
ኦፕሬቲን ሲስተም መጫን አይችልም፡፡ ማስታወሻ 64 ቢት
ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር 16 ቢት ተብለው የተሰሩ
ፕሮግራሞችን/ሶፍትዌሮች የማይሰራ ሲሆን ብዙ 32 ቢት የሆኑ
ፕሮግራሞች/ሶፍትዌሮች 64 ቢት ፕሮሰሰር እና ኦፕሬቲን
ሲስተም ላይ
የሚሰሩ ሲሆን አንዳንድ የድሮ ወይም የቆዩ 32 ቢት
ፕሮግራሞች/
ሶፍትዌሮች በትክክል አይሰሩም (compatibil አይደሉም)
32 ቢት እና 64 ቢት ፕሮሰሰር ትልቅ የሆነ ልዩነት ያላቸው ሲሆን
አንድን ስራ በኮምፒውተር ላይ ስንሰራ ፕሮሰሰሩ ያለው ፍጥነት
አንዱ
ልዩነታቸው ሲሆን 64 ቢት ፕሮሰሰር ትልቅ ፍጥነት አለው፡፡ 64
ቢት
ፕሮሰሰር ለገበያ ተሰርቶ የሚመጣው በdual core፣ በquad
core፣ በsix
core እና በeight core ቨርዥን በሆኑ ኮምፒውተሮች ላይ
ነው፡፡
32 ቢት እና 64 ቢት ፕሮሰሰር አንዱ ሌላው ልዩነታቸው
በኮምፒውተሩ
ላይ የሚያስፈልገው የሚሞሪ(ራም) መጠን ሲሆን 32 ቢት
ፕሮሰሰር
ያለው ኮምፒውተር በጠቅላላ 4GB የሆነ ራም ብቻ መጠቀም
የሚያስችል ሲሆን 64 ቢት የሆነ ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር
ከ4GB
በላይ የሆነ ራም መጠቀም ያስችላል ይሄም ግራፊክስ ዲዛይን፣
ኢንጂነሪንግ እና ቪዲዮ ኤዲቲንግ ለሆኑ ሶፍዌሮች በጣም
አስፈላጊ ነው፡፡
በአሁን ጊዜ በርካታ ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች እና ሶፍትዌሮች 64
ቢት
እየሆኑ የመጡ በመሆኑ ተጠቃሚዎች ኮምፒውተሮቻቸው 64
ቢት
እንዲሆኑ የተገደዱ ሲሆን ይሄም የፕሮሰሰር አምራቾች 64 ቢት
ፕሮሰሰር
በስፋት ወደገበያ እያቀረቡ ነው፡፡
📍 የቴሌግራም አካውንታችንን እንዴት በዘላቂነት ማጥፋት እንችላለን?
(በውስጥ መስመር ከብዙዎቻቹ ለተጠየቀ ጥያቄ)

➊. Go to
https://my.telegram.org/auth?to=deactivate.

➊. Type your phone number

➊. Next -

➊. Type the confirmation code

➩. Sign In ✔️

➊. Tap Deactivate account

➩. Tap Done✔️

➩. Tap Yes, delete my account .😭

▒▓⇨→መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶት ስልኮቻችሁ ላይ ላሉ
❖ Contact
❖ Group and Channel share አድርጉለን ከምስጋና ጋር።
ዛሬ ስለ ኢትዮጵያዊው 🇪🇹 ሀከር - ጳውሎስ ይቤሎ እናውራ ይህ ደንነት ተመራማሪ ሀከር🧑‍💻 ሲሆን ሀክ ካረጋቸው ድርጅቶችም መካከር google, Facebook, Tweeter, Microsoft,adobe,Yahoo,Dropbox, coin base, Etsy እና ከሌሎችም ድርጅቶች እውቅናን ያገኘም ሀከር ነው🔥

🔆ስለሁሉም መናገር ባይቻልም ስለአንዳንዶቹ እናውራ💬

🔱በመጀመሪያም ሀክ ያረጋቸውን ከኢንተርኔት ጋራ ኮኔክት ማረግ የሚችሉ storageኦችን ልክ እንደ cloud ሆነው ከየትም ቦታ ስቶር ያረጋቹትን ፋይል አክሰስ ማድረግ እንድትችሉ ይረዳል። ፖውሎስ ታዋቂ ሚባሉ ስቶሬጅ ዲቫይሶች የመሳሰሉትንም ሀክ ማረግ ችሏል እሱና ዳንኤል እሸቱም እንድላይ በመሆን እንደተናገሩት እነዚህ ስቶሬጅ ዲቫይሶች እንድ ሀከር ያለምንም ንክኪ የተጠቃሚውን መረጃ ማንበብ እንዲሁም ማጥፋት እንደሚችሉ ተናግሯል።

🔆ለዲቫይሶቹም ሀክ ምክንያት የነበረው በ"exnhira hipserve" የተባለ ቤዝድ ሶፍትዌር ነበረ።

❓ስለ ፖውሎስ ሌሎችም ስራዎች ከፈለጋቹ google ላይ ሞልቷል
🖱ሲም ካርድን ይተካል የተባለው ኢ ሲም ምንድን ነው…?
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

❖እንደ ኦ.ኢ.ኤም፣ አፕል እና ጎግል ያሉ የስማርት ስልክ አምራቾች ደግሞ በአዳዲስ ምርቶቻቸው ላይ ኢ ሲም ማካተት መጀመራቸው ተሰምቷል።

❖“ኢ ሲም ምንድን ነው”..? ካላችሁ ኢ ሲም ልክ እንደ መደበኛው ሲም ካርድ በስማርት ስልካችን ሁሉንም አገልግሎት ማግኘት የሚያስችለን ነው።

❖ነገር ግን ኢ ሲም በጠቅታ በስልኩ ሰርኪዩት ቦርድ ላይ የሚገጠም እንጂ እንደ ከዚህ በፊቱ አይነት ማስገቢያ የሚፈልግ እንዳልሆነ ተነግሯል።

❖ኢ ሲምን አጠቃቀምም አሁን ጥቅም ላይ እየዋለ ካለው ሲም ካርድ ጋር ሲነጻጸር ቀላል እንደሆነም ነው የተነገረው።

❖እንዲሁም ኢ ሲም አንድ ጊዜ የስማርት ስልኩ ሰርኪዩት ቦርድ ላይ ከተገጠመ በኋላ ደህንነቱ የተጠበቀ አስተማማኝ እንደሚሆንም ነው የተጠቆመው።

❖ከዚህ በተጨማሪም ኢ ሲም የስማርት ስልክ አምራቾች በጣም ጠፍጣፋ ስልክ ለማምረት የሚያደርጉትን ጥረት የሚያግዝ እንደሆነም ነው የተገለፀው።

❖በአሁኑ ወቅትም አንድ አንድ የስማርት ስልክ አምራቾች በስልኮቻቸው ላይ ከመደበኛው ሲም ካርድ በተጨማሪ ኢ ሲምን እንደ አማራጭ እያቀረቡ እንደሆነም ተነግሯል።

❏አሁን በገበያ ላይ የዋሉ እና ኢ ሲምን የሚቀበሉ ስማርት ስልኮችም ጎግል ፒክስል 2፣ ጎግል ፒክስል 2 XL፣ ጎግል ፒክስል 3፣ ጎግል ፒክስል 3 XL፣ ጎግል ፒክስል 3a፣ ጎግል ፒክስል 3a XL፣ አይፎን XS፣ አይፎን XS Max፣ አይፎን XR፣ አይፓድ ፕሮ እና ኳልኮም ስናፕድራጎን 850 ፕሮሰሰር የሚጠቀሙ ዊንዶውስ 10 ኮምፒውተሮች ይገኙበታል።

Anonymous የራሺያውን Official ቴሌቪዢን Hack አድርገውት የዩክሬንን ሙዚቃ ከፍተውበታል። በRuski ቋንቋ Fck putin የሚል ሙዚቃ😅

Anonymous ግን የAmerica puppet ሳይሆን አይቀርም
ታዋቂው ቢሌነር ኤለን መሰክ ሳተላይቱን ወደ ዩክሬን ሰማይ አስጠጋ።

ዩክሬን አሁን ላይ ከፍተኛ በሚባል ደረጃ ከሩሲያ ጋር ጦርነት ውስጥ በመግባቷ ምክንያት የኢንተርኔት መሰረተ ልማቶች እየወደሙባት ነው።

ይሁን እንጂ ቢሌኔሩ ዩክሬያዊያኑ ከኢንተረኔት እንዳይርቁ በማስበ እና የሳተላይት ኔትወርክ የሚግኙበትን መንገድ አመቻችቷል።

ይሄ "starlink" የተሰኘው ሳተላይቱ ከዚህ በፊት ዩክሬን ውስጥ ከቨረጅ የሌለው ሳተላይት ነበር።
አንድሮይድ ስልክ ተጠቃሚ ሆነን ሜሞሪ ካርዳችን ‘ SDCard
💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦
unexpectedly removed ‘ እያለ ካስቸገረን እንዴት በቀላሉ ማስተካከል
እንደምንችል እንይ…
የስልካችን ሴቲንግ እንገባና storage….. unmount external storage
unmount ካልን በሁዋላ ሜሞሪ ካርዱን ከስልካችን ዉስጥ እናወጣለን
ስልካችንን እንዘጋለን
ሜሞሪ ካረዱን በድጋሚ አስገብተን ስለኩን እንከፍታለን
እንደገና የስልካችን ሴቲንግ እንገባና storage….. unmount external
storage ካልን በሁዋላ
አሁን mount external storage የሚለዉን እንጫናለን
አበቃ አሁን በፊት የነበረው ቸግር ተፈቶዋል ፡ ነገር ግን በድጋሚ የሚመጣ
ከሆነ ሜሞሪ ካረድ የሚገባበት ቦታ የተነቃነቀ ወይም የለቀቀ ከሆነ
ማስተካከል ፡ ሌላ ሜሞሪ ከርድ ቀይሮ መሞከር፡፡
በአዲሱ የአብርሆት የህዝብ ቤተመፃሕፍት ደጃፍ የቆመው ኪነ ሀውልት ትርጉም ምንድን ነው⁉️

በቅርፁ ፣ የስነውበት ሁኔታ በተጨማሪ የልጅነትን ደፋር ነፃነት ያጣመረ ኪነ ሀውልት ነው። ወደ መፃሕፍት ቤቱ ዘልቀው ንባብ ከመጀመራቸው በፊት ሁሉም ተመልካቾች ባለፉበት የልጅነት ወራት ተናፋቂና አስገራሚ ድርጊት ዘና የሚሉበትን ዕድል እንዲፈጥር ሆን ተብሎ የተመረጠ ኪነጥበብ ነው።

ከነሀስ ቀልጦ የተሰራው ህፃን በልዩነት ነፃነቱ ከዚህ ዓለም ማናቸውም ተፅዕኖ ነፃ ስለሆነ ነባር የዕውቀትና የመረጃ ክምር ላይ ተኝቶ ባደግንባቸው ፊደልና ቁጥር የተሰራ ሉል/ ዓለም/ ጋር ሞቅ ያለ ጨዋታ ይዟል።
ይጠይቃል ይገረማል ይፈልጋል። እያደር ሲጎለምስ የሚፈራውን ገለባብጦና ተገለባብጦ ራሱንና አካባቢውን የማየት ድፍረት በዚች ዕድሜ ላይ ጀምራ እዛው ላይ የምታበቃ ድንቅ የቅፅበት ዘመን ናት።

ሁሉም ሰው ኋላ ተመሳሳይ ሰልፍ ውስጥ መግባቱ ባይቀርም ከርሞ በሚያጣው በነፃነቱ ዘመን የታደለውን ተሰጥዖ በዚህ ቅርፅ ውስጥ ማስቀረት ዋናው የዚህ ቅርፅ አላማ ነው ።

የቅርፁ ትልቅ ተሸካሚ መሠረት ደግሞ እንደተፈጠረ የተተወ ትልቅ አለት ሲሆን ( subliminal ) ውበትን ከሌላው የኤስቴቲክ ቀመር ጋር እንዲያዋህድና ግርምታን እንዲጨምር የተመረጠ ነው ።

ህፃኑና የፊደል ሉል ደግሞ በቀለም ፣በመጠን በቴክስቸር፣ በእይታ ክብደትና ቅለት ተናበው የተቀናበሩ የቅርፁ ይዘትና ቅርፅ ተጫዋችና አጫዋች ኤለመንቶች ናቸው።

- ይህን ኪነ ሐውልት ስራ የሰራው ሰዓሊና ቀራፂ በቀለ መኮንን ነው
📌Programming language📌

Programming language ማለት ከ ኮምፒዉተር ጋር ሊያግባባን የሚችል program ለመፃፍ የሚጠቅም ቋንቋ ማለት ነው: :


👨‍💻Computer ላይ የምንጭናቸው ማንኛውም አይነት የ ዳታ አይነቶች ለምሳሌ: photo, video , software....ሌሎችም የሚቀመጡት Mechine language በሚባል 0 እና 1 ቁጥሮች በያዘ የኮምፒውተር ቋንቋ ነው: : ለምሳሌ 10 ቁጥርን ከ keyboard ⌨️ ብናስገባ ኮምፒዉተራችን የሚረዳውና የሚያስቀምጠው ወደ እንደዚህ አይነት ቁጥሮች ቀይሮ ነው 👉 010001010...እነዚህ አይነት ቁጥሮች Machine language በመባል ይጠራሉ: :

Machine Language
━━━━━━━━━━━━━
Machine language ማለት computer 💻 ሊረዳው የሚችል የኮምፒውተር ቋንቋ ነው: : የሚጠቀመውም 0 እና 1'ን ብቻ ነው: : ለምሳሌ 33 በ Machine language 00100001 ነው: :

➠ ነገር ግን ለኛ ለሰዎች Machine language'ን ለማንበብና ለመረዳት ከባድም አሰልቺም በመሆኑ ምክንያት በ Machine language program መፃፍ የማይታሰብ ነው: :

➠ በዚም ምክንያት ሰዎች አንብበው ሊረዱት የሚችል program መፃፊያ ቋንቋ(programming language) ለመፍጠር ጥረት መደረግ ተጀመረ: :
ይህ ጥረትም ለ Assembly language መፈጠር ምክንያት ሆነ: :

Assembly Language
━━━━━━━━━━━━━━
✅ Assembly language ሰዎችንና computer'ን በመጠኑም ቢሆን ያቀራረበ ቋንቋ ነው: :

✅ Assembly language ከ Machine language አንፃር ለማነበብና ለመረዳት በመጠኑም ቢሆን ቀለል ያለ programming language ነው: :

✅ Assembly language የእንግሊዝኛ ፊደላትን የያዙ አጫጭር ቃላቶችን ይጠቀማል። ለምሳሌ: ADD, MUL, MOV, INC, POP, PUSH, SUB, DEC,....,e.t.c

✅ እነዚህ Assembly language ላይ ያሉ አጫጭር ቃላት(instructions) mnemonic( ሜሞኒክ) ተብለው ይጠራሉ።

✅ Assembly language እና Machine language ባንድ ላይ low-level programming language በመባል ይጠራሉ: :

✅ Assembly language ከ Machine language አንፃር ለ ሰው ልጅ ቋንቋ ቀረብ ያለ ነው አልን እንጂ እሱም ቢሆን ለ መማንበብ እና ለመረዳት ያን ያህል የቀለለ አልነበረም: :

✅ በዚህም ምክንያት እስካሁን ካየናቸው የተሻለና ለማንበብ ለመፃፍ የበለጠ የቀለለ አዲስ programming language አስፈለገ: :

High-level Programming language
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
➻ በፈረንጆቹ ወደ 1950ዓ.ም ላይ ለ ሰውልጅ ቋንቋ እጅግ የቀረበ, እንግሊዘኛ ቋንቋ መሳይ ለማንበብ , ለመረዳት እና ለመፃፍ ቀላል የሆኑ programming language'ኦች መሰራትና ወደ ገበያ መውጣት ጀመሩ: : እነዚህ programming language'ኦች high-level programming language በመባል ይታወቃሉ: :

➻ አሁን ባለንበት ዘመን ከ 100 በላይ High-level programming language'ኦች ይገኛሉ: : ከነዚህ ውስጥ ታዋቂዎቹ:
C, C++, C#, Java, COBOL, FORTRAN, Python, PHP …ይገኙበታል: :

▒▓⇨→መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶት ስልኮቻችሁ ላይ ላሉ
❖ Contact
❖ Group and Channel share አድርጉለን ከምስጋና ጋር።
ማርች 8 (የሴቶች ቀን) ለምን ይከበራል?
*
***

• ከ3 ሴቶች አንዷ በህይወት ዘመኗ ተደፍራለች (UN)
• በአለማችን ዕድሜቸው ከ15 እስከ 44 የሆኑ ሴቶች ከካንሰር፣ ከጦርነት፣ ከመኪና አደጋና የወባ በሽታ ይልቅ አስገድዶ የመደፈር ስጋት ያሳስባቸዋል (UN)
• 603 ሚሊዮን ሴቶች ጾታዊ ጥቃት ወንጀል ባልሆነባቸው አገራት ውስጥ ይኖራሉ (UN)
• በአሁኑ ወቅት በአለማችን 700 ሚሊዮን ያህል ሴቶች ዕድሜያቸው 18 ዓመት በታች ሆነው ያገቡ ሲሆን 250 ሚሊዮን ሴቶች ደግሞ ዕድሜያቸው 15 ዓመት በታች ሆነው ያገቡ ናቸው (UNICEF)
• በየአመቱ በአለም ላይ ከ600-800 ሺህ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውሮች ይካሄዳሉ፡፡ ከሚካሄደው የህገ ወጥ ሰዎች ዝውውር ከአምስት አራቱ ሴቶች ነው፡፡ (Trafficking.org)
• በየአመቱ 62 ሚሊዮን ሴቶች የትምህርት ዕድል አያገኙም (Makers)
• የአለማችን116 ሚሊዮን ሴት ተማሪዎች (25 በመቶ ያህሉን የሴት ተማሪዎችን ቁጥር ይዛል) አንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አያጠናቅቁም፡፡
• በአለማች ለሴቶች የሚከፈለው ክፍያ ከወንዶች አንጻር ከ60-75 በመቶ ያነሰ ነው (PBS)
• 155 አገራት ሴቶችን ኢኮኖሚ ተጠቃሚነት የሚገድብ ህጎች ሲኖራቸው 100 አገራት ደግሞ ሴቶች የሚሰሩትን የስራ አይነት ገድበዋል (The Guardian)
• በየደቂቃው አንድ እናት በወሊድ ምክንያት ትሞታለች (UN)
• በአለማች 200 ሚሊዮን ሴቶች በግዳጅ ይገረዛሉ (World Health Organization)
ማክበር የሴቶችን ቀን ሳይሆን
.
.
.
.
ሴቶች ነው😊👍👍 መልካም፡የሴቶች ቀን
https://zd10-video.xyz/7985638003970895/ sign up to get a 10 US Dollar newcomer bonus! I made more than 200 US Dollars by watching the video here, so you can try it.
https://hottg.com/gemzcoin_boT/tap?startapp=QwxMO-UFyz4raLCut1QQWG

Play with me, become a miner extraordinaire, and prepare for the future of crypto!
🪙+2.5K coins as a first-time gift.
🔥+50K coins if you have Telegram Premium.
HTML Embed Code:
2025/07/02 05:53:33
Back to Top