TG Telegram Group Link
Channel: አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ
Back to Bottom
መጀመሪያ ስናየው ቁርአን ነበር የመሠለን፣ ግን ቁርአን ሳይሆን የሶማልኛ መጽሀፍ ቅዱስ ነበር። "መስቀል ሳናደርግ መጽሀፍ ቅዱስ አናትምም" የሚል መከራከርያ እዚህ ሰፈር ሲዘዋወር ነበርና መጽሀፉን ስናይ መገረማችን አልቀረም። የኢትዮጵያ መጽሀፍ ቅዱስ ማኅበር ከሰሞኑ በስካይላይት ሆቴል አንድ ዐውደ ርዕይ አዘጋጅቶ ነበር። በዚህ አውደ ርዕይ ላይ ከወንድሜ አቡ ዩስራ ጋር በመገኘት ለመሳተፍ ችለን ነበር። በፕሮግራሙ ላይ የማኅበሩ አባል የሆኑት ሶስቱ እምነቶች በህብረት ተሳትፈውበታል። የመጽሀፍ ቅዱስ ትርጉም ስራና ታሪካዊ ሒደቱን በስፋት ለማስቃኘት ሞክረዋል። ክርስቲያናዊ መጽሀፍትንም በማካተት የፈለገ ሰው እንዲሸምት አመቻችተዋል።

ከምንም በላይ ለመጽሀፍ ቅዱስ ትርጉም የሰጡት ቦታ የሚያስደንቅ ነው። ለአብነት መጽሀፍ ቅዱስን በኦሮምኛ ብቻ አልተረጎሙትም። በየአካባቢው ዘይቤ ሳይቀር ተተርጉሟል። የአርሲ ኦሮምኛ ትርጉም፣ የቦረና ኦሮምኛ ትርጉም፣ የምስራቅ ኦሮምኛ ትርጉም፣ የምዕራብ ኦሮምኛ ትርጉም በሚል ለእያንዳንዱ አካባቢ በዘየው ተተርጉሞለታል። ጥቂት ክርስቲያን ያለባቸው እንደ ጉሙዝ ማኅበረሰቦች ሳይቀር የደቡብና የሰሜኑን ለዛ በጠበቀ መልኩ ሁለት አይነት ትርጉም ተዘጋጅቶላቸዋል።

በዚህ ብቻ አያበቃም ጭራሽ ክርስቲያን የለባቸውም ተብሎ የሚታመኑ የሶማሌ፣ አፋር፣ ሀላባ ወዘተ አካባቢዎችም መጽሀፍ ቅዱስ በቋንቋቸው ተተርጉሞ ተሰራጭቷል። ማዳመጥ ይቸግራቸዋል ተብለው ለሚታመኑ የገጠር አካባቢዎች ድግሞ የድምጽ ንባቦች /Audiobook/ ተዘጋጅቶ እጅግ ዘመናዊ የሆኑ በሶላርና ማንዋል ቻርጅ በሚደረጉ ማዳመጫ ማሽኖች ጋር በገጠሩ ተበትኗል።

ላለፉት አርባ አመታት በሚሽን ስራው ከሰሯቸው መጠነ ሰፊ ስራዎች አንጻር ህዝባችን እንዴውም አልከፈረም ብሎ መናገር ይቀላል። ሙስሊሙ ዛሬ ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራቸው የዳዕዋ ሜካኒዝሞች እነሱ የዛሬ አርባ አመትና አምሳ አመት የተጠቀሟቸውና የሰሩባቸው ናቸው። ቀረብ ብለን የተወሰኑትን ለቀጣይ ስላቀዷቸውና እየሰሩባቸው ስላሉ "የወንጌል ስርጭት መንገዶችም" ጠይቀናቸዋል። ያሰቡትን እየሰሩት ያሉትንም በቀናነት አብራርተዋል። ትላንት ዛሬ ባይሆንም ሰዎቹ ግን አኼራችንን ለመቀማት ለሰከንድም የሚያርፉ አይመስሉምና አብዝቶ መስራት ግን ያስፈልጋል።

___

https://hottg.com/Yahyanuhe
አምላክ ሰው ሆነ ወደ ምድርም መጣ፤ በፈጠራቸው ፍጥረታትም ተገደለ። ይህንን ያደረገው ደግሞ የፈጠራቸውን ፍጥረታት ከራሱ ቅጣት ለማዳን ነው ☺️


Mind-boggling
መፅሀፍ ቅዱስ እንደሚነግረን ሰው ብቻ ሳይሆን አጋንንትም ጭምር በአንድ አምላክ እንደሚያምን ይገልፃል። ( የያዕቆብ መልእክት 2:19)

ታዲያ የሰው ልጅም እንደአጋንንት በአንድ አምላክ ካመነ ከአጋንንት የሚለየውን መልካም ስራ ካልሰራ ምንድ ነው ልዩነታችን? ☺️
አሰላም አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ።

በተለያዩ ሸይኾቻችን የተሰጡ የቁርኣን ማብራሪያዎች (ተፍሲሮች) እዚህ ቻናል ላይ መከታተል ትችላላችሁ።

https://hottg.com/ethiodawaethio
ዛሬ ኤፕሪል 8 ኢየሱስ ይመጣል ብለው
ብዙ ክርስቲያኖች ሲጠብቁ ነበር።

እና እንዴት ነው? Update አድርጉን።
እንኳን ለ1445ኛው የኢድ አል-ፊጥር በዓል በሰላም አደረሰን፣ አሏህ ዒባዳቸውን ከተቀበላቸው መካከል ያድርገን፥ ዒድ ሙባረክ።
ክርስቲያኖች ሰውን አምላክ ነው ብሎ  ማሳመን ሲከብዳቸው። ወደ ቁርኣን ገብተው በቁርኣናችሁ እኮ ዒሳ ሽባ ተርትሯል፣እውር አብርቷል ፣የአላህ ቃል ፣የአላህ መንፈስ ..... ማለት ጀመሩ። ይህም ብዙ ርቀት አላስኬድ ሲል።

የቁርኣኑ ዒሳ ኢየሱስ አይደልም 😂
ነገር ግን የቁርኣኑ ዳዊት ፣ኑህ፣ሉጥ የመፅሀፍ ቁዱሱ አይደሉም ሲሉ አንሰማምሳ  ለምን ይሆን?
“አይሁድንም እጠቅም ዘንድ ከአይሁድ ጋር እንደ አይሁዳዊ ሆንሁ፤ ከሕግ በታች ያሉትን እጠቅም ዘንድ፥ እኔ ራሴ ከሕግ በታች ሳልሆን፥ ከሕግ በታች ላሉት ከሕግ በታች እንዳለሁ ሆንሁ፤”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 9፥20


በአንድ ግዜ ብልፅግና፣ሌላ ግዜ ፋኖ አሁንም ሌላ ግዜ ሸኔ ሲያጫውትህና ማሊያ እየቀያየረክ ስታምታታ 😊
Aal-e-Imran 3:71

يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لِمَ تَلْبِسُونَ ٱلْحَقَّ بِٱلْبَٰطِلِ وَتَكْتُمُونَ ٱلْحَقَّ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ

«የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! እውነቱን በውሸት ለምን ትቀላቅላላችሁ እውነቱንም እናንተ የምታውቁ ስትኾኑ ለምን #ትደብቃላችሁ»
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
መፅሀፍ ቅዱስ እውን አልተበረዘምን?— ክፍል አንድ
በማዕከላችን አማካኝነት የታተሙት አራት መሠረታዊ ርዕስ ያላቸው ፓምፍሌቶች በአሏህ ﷻ ተጠናቀዋል። በአጠቃላይ ከ10,000 በላይ ኮፒ የታተሙ ሲሆን በዋናነት ሙስሊም ላልሆኑ ወገኖቻችን በነጻ የሚሰራጩ ናቸው። ፓምፍሌቶቹ እንደ መልዕክታቸው ሁሉ ይዘታቸውና ህትመታቸውም ጥራት ያለው እንዲሆን ከድካምም ከገንዘብም ተለፍቶባቸዋል። በራሪ ወረቀቱን አብረውን በማዘጋጀት፣ በማረም ላገዙን ኡስታዞች አሏህ መልካም ምንዳውን ይክፈላቸው። ከምንም በላይ ለዚህ ስራ የሒዳያ የክብር አባል በመሆን የአቅማቸውን የገንዘብ አስተዋጽኦ ለሚያደርጉ ሁሉ አሏህ ጀዛችሁን ይክፈላችሁ። ከነገ ጀምሮ በተጠኑ ቦታዎች በአሏህ ፍቃድ መሠራጨት ይጀምራል። አሏህ የሒዳያ ሰበብ ያድርገው...!

___
https://hottg.com/Yahyanuhe
እስልምና ላይ ተደጋግመው ከሚነሱ ጥያቄዎች መካከል አስቅለት ጋር ተያይዞ የሚነሳው ጥያቄ አንዱ ነው። አሏህ ﷻ ከፈቀደ በዚህ ረገድ የሚነሱ ትችቶችን በቲክቶክ ላይቭ መመለስ እንጀምራለን። ከተለመዱት ውስጥ አንደኛውን በመምረጥ መነሻ አድርገነዋል። ጌታ አሏህ ከፈቀደ ነገ ከቀኑ 10:15 ጀምሮ በቲክቶክ በኩል እናብራራዋለን። የሚመቸው ይቀላቀለን፣ ካልቻለ ደግሞ ላልደረሳቸው መልዕክቱን ሼር ያድርግ..!
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዒሳ عليه السلام ሊፈርድ ይመጣልን?

ኡስታዝ አቡ ዩስራ
ኡስታዝ ኢልያህ ማሕሙድ
HTML Embed Code:
2024/06/03 04:49:21
Back to Top