TG Telegram Group Link
Channel: Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
Back to Bottom
ዛሬ አቅመ ደካሞችን ማዕከል ያደረገውና የሰው ተኮር ስራ ውጤት የሆነው የሼካ ፋጢማ ቢንት ሙባረክ የዐይነ ስውራን ትምህርት ቤት በመመረቁ ለቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እንኳን ደስ አለዎት ለማለት እፈልጋለሁ። ይህ ስኬት በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት የተሰሩና በተሳካ ሁኔታ ለአገልግሎት የበቁ የትምህርት ቤት ግንባታዎችን ፈለግ ተከትሎ በመገንባት የተገኘ ነው።

ከዚህ የዐይነ ስውራን ትምህርት ቤት ስኬት ትምህርት በመቅሰም የምንገነባቸው የከተሞቻችን መሰረታተ ልማት የአካል ጉዳት ላለባቸው ዜጎች ትኩረት የሚሰጡ እንዲሆኑ ማድረግ ይገባናል።

በዚህ አጋጣሚ ይህን የላቀ ትርጉም ያለው ስራ በመደገፋቸው ግርማዊት ሼካ ፋጢማ ቢንት ሙባረክን አመሰግናለሁ።

On the occasion of the inauguration of the Sheika Fatima Bint Mubarak School for the Blind I would like to extend my congratulations to First Lady Zinash Tayachew for the fruition of a citizen centered establishment putting the vulnerable at heart, following the success of the schools built throughout the nation through the Office of the First Lady.

Learning from the success of this school for the blind, we need to make sure that city infrastructure we build needs to pay attention to the needs of those with disabilities.

I take this opportunity to extend my gratitude to Her Highness Sheika Fatima Bint Mubarak for the support extended to this noble cause.
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ለኢትዮጵያ ብልጽግናን ስንመኝ ትጋትን እና ከልብ መስጠትን አንግበን ነው።
HTML Embed Code:
2024/05/21 09:56:36
Back to Top