Warning: mkdir(): No space left on device in /var/www/hottg/post.php on line 59

Warning: file_put_contents(aCache/aDaily/2025-07-22/post/APOSTOLICsuccession/--): Failed to open stream: No such file or directory in /var/www/hottg/post.php on line 72
የመጽሐፉ ርዕስ፦ Homily on concerning the red heifer and crucifixion of our lord. @የጥያቄዎቻችሁ መልስ
TG Telegram Group & Channel
የጥያቄዎቻችሁ መልስ | United States America (US)
Create: Update:

የመጽሐፉ ርዕስ፦ Homily on concerning the red heifer and crucifixion of our lord.
ይዘት፦ ኅብረ አምሳላዊ ይዘት ያለው፤የመጽሐፍ ትርጉም ሲሆን፦ ቅዱስ ያዕቆብ ዘስሩግ በኦሪት ዘኊልቊ 19 ላይ ያለውን የመሥዋዕት አሠራር ስርአት ማለትም፦ በሊቀ ካኅናቱ አማካኝነት የምትሠዋ ጊደር፣ከዝግባ እንጨት፣ከሂሶጵ እና ከቀይ ግምጃ ጋር ጊደሪቱ ከሥጋዋ፣ከደምዋ፣ከቁርበቷ እና ከሥጋዋ ጋር የመቃጠሏ እና ለሰዎች ከእርኩሰት የመንጻት ስርአት ማከናወኛ የመሆኗን ነገር፥ከክርስቶስ ስቅለት ጋር በማገናኘት እና እነዚህ የመንጻት ስርአቶች የክርስቶስ ስነ-ስቅለት አስረጂ የሆኑ አምሳላዊ እና ምሳሌያዋ ገላጮች ለመሆናቸው ያስረዳበት መጽሐፍ ነው።

የአጻጻፍ ሁናቴው፦ በግጥማዊ መልክ የተጻፈ ሲሆን እያንዳንዱ ክፍል በአምስት በአምስት ስንኝ የተከፋፈለ ነው። በአጻጻፉ የኢትዮጵያውያን አበውን የመልክእ እና የዐርኬ አጻጻፍን ይመስላል።

እንደ መግቢያ

በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር አምላካችን ለሕዝበ እስራኤል የመሥዋዕትን ስርአት እንደሠራላቸው ቅዱስ መጽሐፍ ይነግረናል። ይህም መሥዋዕት ሊመጣ ላለው፥ለአካሉ እንደ ጥላ የሆነ፤እና በክርስቶስ ኢየሱስ ለቀረበው አማናዊ መሥዋዕት ምሳሌ ነው።
በብሉይ ኪዳን የተሠዉ ንጹሓን እንሥሣትም፥ሌላ መንፈሳዊ ትርጉም ቢኖራቸውም እነርሱም፤መሠዋታቸውም በክርስቶስ ይመሰላል።

ለምሳሌ፦ መሐልየ መሐልይ ዘሰሎሞን 2:9 ላይ ሙሽራይቱ ቤተክርስቲያን ሙሽራዋን እንዲህ ትለዋለች"ልጅ ወንድሜ በቤተል ተራሮች ላይ ሚዳቋን ወይም የዋሊያን እንምቦሳ ይመስላል።"

ይህ አጢነን፤ስንመለከት ደግሞ በኦሪት ዘዳግሞ 12 ላይ እንደተገለጸው ከሚሠው እና ከንጹሕ እንሥሣት የተመደቡ እንደሆኑ እናያለን።

መንፈሳዊ ትርጉሙን ከአበው፣አንዱ አባት በተረጎመበት መነጽር ስናይ፦
"ከእይታው አንጻር፣እርሷ ወንድሟን ከሚዳቋ ጋር አመሳሰለችው። ከፍጥረተ ዓለሙ በፊትም ቢሆን፥ለሰው ልጅ ምን እንደሚገባው ያያየልና። ስለሆነም ከአውሬዎች ወገን ከሚዳቋ የተሻለ እይታ ያለው የለምና፤ስለዚህ ምክንያት ለክርስቶስ እይታ ዘይቤያዊ አነጋር(Metaphor) አደረገችው። ዋልያም ቢሆን እባብን ይገድላል፣ጌታ በማይታየው እባብ ላይ እንዳደረገው።¹

እንዲህ ተብሎ በቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘናሬክ በኅብረ አምሳላዊ መንገድ ሊተረጎም ቢችልም፣በቁምም(በቃል በቃል ትርጉምም) ወስደን እኒህ የብሉይ ኪዳን መሥዋዕቶች የክርስቶስ ምሳሌ እንደሆኑ ማየት ይችላል።

ከቅዱስ ያዕቆብ በፊትም ቢሆን፥ይህንን መሥዋዕት የመሠዋት ስርአት (በኦሪት ዘኊልቊ 19 ላይ ያለውን) ለክርስቶስ ኢየሱስ አማናዊ መሥዋዕትነት ሰጥቶ በአዲስ ኪዳን መነጽርነት በማየት ለመጀመሪያ ጊዜ ተተርጉሞ ያየነው መልእክተ-በርናባስ በተባለው የመጀመሪያው ክፍለዘመን ጽሑፍ ሲሆን፣ ይህንን ትውፊት የያዙ አበው ለምሳሌ ያህል፦ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ዘሰላሚስ እና ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያም ጭምር በአዲስ ኪዳናዊ አተረጓጎም የተረጎሙ ሲሆን²፣ በጥልቅ መንገድ በመተርጎም ግን ቅዱስ ያዕቆብ ዘስሩግ ላይ የደረሰ የለም።

የቅዱስ ያዕቆብ ዘስሩግ መግቢያ

ሊቁ መጽሑፉን ሲጀምር፥ ኦርቶዶክሳዊ ፍኖትን በመከተል በጽዋኤ እግዚአብሔር እና በጸሎት ነው። በተለይም ስለ ነገረ-መለኮት ስናጠና፣እና ስንማር፣ጸሎትን ማስቀደም ተገቢ እንደሆነ፣እና ነገረ-መለኮት እና መንፈሳዊ ሕይወት የማይነጣጠሉ እንደሆኑ! የሚያስተምረውን ተማኅልሎአዊ ነገረ-መለኮታዊ(Mystical Theology) ፍኖት የሚያጠናክር ነው።
"ከሁሉ በፊት፣ በተለይም ነገረ መለኮት(Theology) ስናጠና ጸሎት እናስቀድም።"³

እንዲል ቅዱስ ዲዮናስዮስ። ይህም አባት በኦሪት ዘኁልቊ መጽሐፍ ላይ፥ ስላለው ምስጢር ከሳቴ-ኅቡአት ክርስቶስ ሚስጢርን ይገልጥለት ዘንድ በተማጽኖ ይጀምራል።

በመቀጠልም ሊቀ-ነብያት ሙሴ ስለ እግዚአብሔር ወልድ በርካታ ጊዜ በምሳሌያት በኩል በኦሪት መጽሐፍቶቹ ውስጥ እንደተናገረ እና እንደጻፈ ያትታል። እንዲህ በማለትም ይህን ይገልጣል፦
"በመጽሐፍቱ መንገድ ላይ የተከመረ፣የተምሳሌያት ሀብት ተመለከትኹ።"⁴

ሊቁ የብሉይን መጽሐፍት "የአብ መጽሐፍት"(The book of the Father) ብሎ ይጠራቸውና በምሳሌያት በኩል ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስነ-ስቅለት እንዲሁም "ውበተ ወልድን"(The beauty of the Son) እንደሚያሳዩ እና ሕያው ምስክር እንደሆኑ ጽፏል።
"ቅዱሳት መጻሕፍት እርሱ ነፍስ የሆናቸውና፤ቅርንጫፎቹ ናቸው። ስለ እርሱ በብዛት ይናገራሉ። ሙሴ የተለያየ አማራጭ ያላቸውን የትንቢት ቀለማትን ያዘና፣በንባባቱ ቅጠሎች ገለጠው። በመሥዋዕቱ ደም የስቅለትን መንገድ ረጨ።"⁵

በማለቱም ሊቀ-ነብያት ሙሴ አስቀድሞ በምሳሌያት በኦሪት መጽሐፍቶቹ፣ሊመጣ ያለውን ድኅነት በጥላው ማስተላለፉን እንረዳለን።

ስለሆነም ሙሴ በኦሪት ዘኁልቊ የገለጠው ስርአት የሚመጣውን ዘለዓለማዊ ስርአት በጥላው እንደገለጠ፣ይህንም ለመረዳት ግልጠተ-እግዚአብሔር እንደሚያሻን፣በዓለማዊ ፍቅር ተይዘንም መረዳት እንደማንችል፣ ነገርግን መልእክተ እግዚአብሔርን ለመረዳት፥በፍቅር ማንበብ እና ራስን በማንጻት ውስጥ ሆነን ማንበብ እንደሚገባን፣ራሳችንን የምናነጻበት መንገድም ቅዱስ ሚስጢራት እንደሆኑ፣ስለሆነም በእነዚህ ውስጥ ሆነን መጽሐፉን ካነበብን ሚስጢራቱን እንደምንረዳ ነግሮን አማናዊውን ፍኖት ያጸናልናል።
ከእዚህ ሊቅ ትምህርት የምንረዳው ቁም ነገርም ነገረ-መለኮት እና መንፈሳዊ ሕይወት የተለያዩ እንዳልሆኑና፤እንዲሁም ከሚስጢራት የተለየ መንፈሳዊነት እንደሌለ፣እና ሚስጢራት ለመንፈሳዊ እድገታችን ያላቸውን ሚና ነው።በዚህም ትምህርቱ ኦርቶዶክሳዊውን ኅሊና(Understanding) ያጸናልናል።
በመቀጠልም፥የመጽሐፉን ጸሐፊ ሊቀ-ነብያት ሙሴን በምልጃው እንዲረዳው፤እንዲሁም የጻፈውን መጥቶ ያስረዳው ዘንድ ይጠይቀዋል።

..... ይቀጥላል

ማጣቀሻዎች
1. Commentary on blessing of blessings on 2:9
2. Demetrios Albertis, Jacob of Serug's Homily on concerning the red heifer and crucifixion of our lord,Page 10
3. On the Divine name chapter 3:section1
4. Homily on concerning the red heifer and crucifixion of our lord:15
5. ዝኒ ከማሁ:35

Forwarded from Orthodox Patristic Writings. (Esdros)

👍87

>>Click here to continue<<

የጥያቄዎቻችሁ መልስ

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)

Warning: Undefined array key 3 in /var/www/hottg/function.php on line 115

Fatal error: Uncaught mysqli_sql_exception: Too many connections in /var/www/db.php:16 Stack trace: #0 /var/www/db.php(16): mysqli_connect() #1 /var/www/hottg/function.php(212): db() #2 /var/www/hottg/function.php(115): select() #3 /var/www/hottg/post.php(351): daCache() #4 /var/www/hottg/route.php(63): include_once('...') #5 {main} thrown in /var/www/db.php on line 16