TG Telegram Group Link
Channel: አለቃ ገብረ ሃና
Back to Bottom
ጉድ ባይ ብዬ መጣሁ

አለቃ ከስራ በጣም ደክሟቸው ያለሰአት ወደ ቤት ይመጣሉ።

ልክ እቤት እንደደረሱ ወ /ሮ ማዘንጊያ ሲያቃትቱ ሰምተው መቋሚያቸውን ጠበቅ አድርገው ወደ ቤት ሳያንኳኩ ..ሰተት ይላሉ ልክ እንደገቡ የሳቸው [የአለቃ] ቅርብ ጓደኛቸው አልጋቸው ላይ ከማዘንጊያ ጋር ጉዳዩን ተያይዞት ያያሉ።

አለቃም ተገርመው «እና…ንተ» ቢልዋቸው።

ማዘንጊያሽ እና ጓደኛቸው ደንግጠው «አለቃ ምነው ያለሰአቶ» ቢሏቸው እሳቸውም መልሰው «የስራ ባልደረቦቼን ጉድ ባይ ብዬ መጣሁ» አሉአቸው።
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦⇨ @Aleka_Gebre_Hana
             ⇨ @Aleka_Gebre_Hana
─── ❖ ── ✦ ── ❖ ───
ከመሶብዎ አይጡ

ሰው መቼም ወዶም ይሁን ፈርቶ አለቃን ይጋብዛቸዋል።

አንድ ቀን ሊጋበዙ ወደ አንዱ ቤት ጎራ ብለው እንደተቀመጡ ጋባዥዋ ሴት እንጀራ ለማቅረብ መሶቡን ከፈት ስታደርገው ትንሽ አይጥ ዘላ ትወጣና ትሰወራለች።

አለቃም ይህችን ጠንቀኛ አይጥ አይተዋት እንዳላዩ ጸጥ ብለዋል። ርቧቸው ስለነበረ ከራሳቸው ጋር እየታገሉ እስኪበቃቸው ድረስ ይበላሉ።

ከዚያም በመጨረሻ ማእድ ሲነሳ መመረቅ የተለመደ በመሆኑ እንዲህ ብለው ይመርቃሉ ;-

በላነው ጠጣነው ከእንጀራ ከወጡ እ /ር ይስጥልኝ ከመሶብዎ አይጡ።
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦⇨ @Aleka_Gebre_Hana
             ⇨ @Aleka_Gebre_Hana
─── ❖ ── ✦ ── ❖ ───
በሰው አገር ቀረሁ

አለቃ መንገድ ወጥተው ይመሽባቸውና የመሸበት እንግዳ ብለው ሰው ቤት ይጠጋሉ።

በኋላም ያረፉባት ሴትዮ ያለቃን ተረብ ታውቅ ኖሮ ተጨንቃ ተጠባ አሳ ወጥ ሰርታ እራት ታቀርባለች።

ያው ሴትየዋም አሳው ወጥ ላይ የማይገባበትን ውሀ ጨምራበት ነበርና ትንሽ ቀጠን ብሎ ነበር።

ታዲያ አለቃም የቀርበላቸውን እራት ጥርግ አድርገው ከበሉ በኋላ ለቅሶ ይጀምራሉ።

እንደው ያዙኝ ልቀቁኝ ሰዎቹም ተጨንቀው አረ አለቃ ምነካዎ? ብለው ቢጠይቁ «አዬ አሳ አገሩ ሲገባ እኔ በሰው አገር ቀረሁ» ብለው የሴትየዋን የአሳ ወጥ በደንብ አለመስራት ተናገሩ።
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦⇨ @Aleka_Gebre_Hana
             ⇨ @Aleka_Gebre_Hana
─── ❖ ── ✦ ── ❖ ───
ቢሻን እንበላለን ቢሻን እንጠጣለን

በሀገራችን እንደተለመደው ድግስ ካለ ቄሱም ሼሁም ሁሉም እንደየሀይማኖቱ ይጠራሉ። አዝማሪዎችም አይቀሩም።

ስለዚህ የአለቃ ግዳጅ አንዱ ድግስ መሄድ ነው።

ሴትየዋ ያው እንደነገሩ አሸር ባሸር የሆነ ድግስ ብጤ አድርጋ ኖሮ አለቃ ወጡም ቅጥንጥን ጠላውም ውሀ ውሀ ብሎባቸው ኖሯል።

ደጋሽ መጥታ አለቃ ይብሉ እንጂ ትላለች።

አለቃም «የመጣንበትን ቢሻን እንበላለን ቢሻን እንጠጣለን» ብለው የልባቸውን ተናገሩዋ ድግሱን የፈቀዱ መስለው።
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦⇨ @Aleka_Gebre_Hana
             ⇨ @Aleka_Gebre_Hana
─── ❖ ── ✦ ── ❖ ───
ጥፍር ያስቆረጥማል

አንድ ቀን አለቃ በእንግድነት ሰው ቤት ይሄዱና ምግብ ይቀርብላቸዋል።

እየበሉ ሳለ በድንገት ከምግብ ጋር የገባ የጥፍር ቁራጭ ያገኙበታል።

ከዚያም ባልቴቷም ትመጣና «አለቃ ብሉ እንጂ አይጣፍጥም እንዴ?» ትላቸዋለች።

አለቃም የተቋጠረ ፊታቸውን ፈታ በማድረግ «ኧረ ይጣፍጣል ከመጣፈጥም አልፎ ጥፍር ያስቆረጥማል!!» አሉ አሉ።
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦⇨ @Aleka_Gebre_Hana
@Aleka_Gebre_Hana
─── ❖ ── ✦ ── ❖ ───
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ!✌️💃⚡️

መልካም በዓል ይሁንላችሁ✔️

💫💜🤍💟💙🫶💜💗❣️

#ETHIO_CHANNEL

📢 @HOPESIS
📢 @Amesi_Tech
📢 @ZODIAC_ETHIO
📢 @ALEKA_GEBRE_HANA
📢 @ETHIOPIA_BOOK_STORE
📢 @SPACE_SCIENCES
🤖 @kokeb_koteri_bot
🤖 @ethio_library_robot
HTML Embed Code:
2024/05/31 23:22:54
Back to Top