TG Telegram Group Link
Channel: የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን
Back to Bottom
ባለስልጣኑ 2017 በጀት ዓመት የጥሬ ገንዘብና የንብረት ቆጠራን አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡
(ሰኔ 19 ቀን 2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የኦዲት ዳይሬክቶሬት የ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የጥሬ ገንዘብ እና የንብረት ቆጠራን በተመለከተ የማዕከል እና ለዘጠኙ ቅ/ጽ/ቤቶች ለቆጠራ ኮሚቴ እና አስቆጣሪዎች እንዲሁም ለስነ-ምግባር እና ፀረ ሙስና ዳይሬክተሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡
አቶ ሰለሞን አለማየሁ የባለስልጣኑ አማካሪ እንደገለጹት ዘርፉ ሙያዊ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው እንደመሆኑ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው አስፈላጊ እና ወቅታዊ መሆኑን ገልጸው ስራን በአግባቡ ለማከናወን እንዴት ይሰራል? በምን አግባብ ይሰራል? ከባለፉት አመታት የተለዩ ጉዳዮች ምንድን ናቸው? የሚሉትን ነገሮች በስልጠና ማስደገፍ አስፈላጊ ነው ያሉ ሲሆን በዚህም መሰረት ተግባራቶቻችንን ወጥ በሆነ መልኩ ማከናወን ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ወ/ሮ አለም ታደገ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ የዘመናዊ የውስጥ ኦዲት ማህበራዊ ቡድን ዘርፍ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናውን የሰጡ ሲሆን አጠቃላይ የቆጠራ ስራ በሚመለከት ከኦዲተር ምን ይጠበቃል፣የቆጠራ ቡድኑ አባላት የስራ ተግባር፣በስቶክ ቆጠራ ወቅት የመ/ቤቱ ሀላፊነት፣የጥሬ ገንዘብ ቆጠራ አስፈላጊነት እና መሰል ተግባራት እንዲሁም አጠቃላይ የበጀት ዓመቱን የቆጠራ አጠቃላይ ሂደት በዝርዝር አስረድተዋል፡፡
ወ/ሮ ትግስት ጌታነህ የባለስልጣኑ የውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እንደገለፁት ለስራው ወጥነት እና ቀልጣፋነት እንዲሁም አጠቃላይ ሙያዊ ግንዛቤ ለማሻሻል መድረኩ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

#ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F
#ድረ_ገጽ; educoc.gov.et
#ቴሌግራም https://hottg.com/AAEQOCAA
#ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@educationtraning2?_t=ZM-8u2f6smztvr&_r=1
#ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302
ቅ/ጽ/ቤቱ በ2017 በጀት ዓመት ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመተሳሰር በቅንጅታዊ አሰራር፣በመልካም አስተዳደር፣በአገልግሎት አሰጣጥና ብልሹ አሠራርና ሌብነት ማክሰሚያ እቅድ ያከናወናቸውን ተግባራት ገመገመ።

(ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የጉለሌ ቅ/ጽ/ቤት ከቅ/ፍ ጽ/ቤቱ ጋር ትስስር ፈጥረው የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ላይ ከሚገኙ ተቋማት የመጡ የስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ የቅ/ፍ ጽ/ቤቱ ጠቅላላ ካውንስል አባላት የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ የተገኙ ሲሆን የት/ጥራት ማረጋገጥና ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ክፍሌ ዓለሙ በበጀት ዓመቱ በቅንጅታዊ አሰራር እና በመልካም አስተዳደር የተከናወኑ ተግባራትን እንዲሁም የሌብነትና ብልሹ አሠራር እቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና የአገልግሎት አሰጣጥ፣የተገልጋይ እርካታ ትንተና ሰነድ የቅ/ፍ ጽ/ቤቱ የእቅድ ዝ/ክ/ግምገማ ባለሙያ ተወካይ የሆኑት አቶ አሸናፊ መለሠ አቅርበው ውይይት ተካሂዷል።

የቅ/ጽ/ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ፍቅሩ ገቢሳ በመድረኩ መክፈቻ የትምህርት ስራ ትውልድ በእዉቀት በክህሎት እና በጥሩ ስነምግባር የሚገነባበትና የነገ ሀገር ተረካቢ ዜጋ የሚፈጠርበት ተቋም በመሆኑ ስራው የሁሉንም ባለድርሻ አካላት የጋራና የተቀናጀ ተሳትፎ እንደሚፈልግ ጠቁመው ጽ/ቤቱ በቅንጅታዊ አሰራርም ሆነ በመልካም አስተዳደር ስራዎች፣ሌብነትና ብልሹ አሠራርን ለማክሰም የተገልጋይ እርካታን በማሣደግ ረገድ ላስመዘገበው ውጤት አስተዋጽኦ ላበረከቱት ተቋማት ምስጋና በማቅረብ በቀጣይ የትምህርት ጥራትን በማረገገጥ የተማሪዎችን ውጤትና ስነምግባር ለማሻሻል የሚከናወኑ ተግባራት በሚፈለገው ደረጃ ውጤታማ ሆነዉ እንዲቀጥሉ ባለድርሻ አካላት ተሳትፏቸውን አጠናክረው እንዲሄዱ ጥሪ አስተላልፈዋል።
በመማር ማስተማር አገልግሎቱ በተለይም በግል ትምህርት ቤቶች የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችና የህገ ወጥ ተግባራት በቅንጅት በመሰራቱ ችግሮቹ በከፍተኛ ደረጃ መቀረፋቸውንና ለዉጥ መምጣቱን ስራ አስኪያጁ አክለው ገልጸዋል ።
በመርሀ ግብሩ ላይ በቅንጅታዊ አሰራርና በመልካም አስተዳደር ስራዎች ከቅ/ጽ/ቤቱ ጋር በመተሳሰር ከፍተኛ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ተቋማት ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል ።
ምንጭ፡-ጉለሌ ቅ/ጽ/ቤት

#ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F
#ድረ_ገጽ; educoc.gov.et
#ቴሌግራም https://hottg.com/AAEQOCAA
#ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@educationtraning2?_t=ZM-8u2f6smztvr&_r=1
#ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302
የእሳትና አደጋ ስጋት/መከላከል ስልጠና ለሰራተኞች መስጠት አስፈላጊ እንደሆነ ተጠቆመ፡፡
(ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርትና ስልጠና ቁጥጥር ባለስልጣን የልደታና አዲስ ከተማ ቅ/ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ አንዋር አብዲ በስልጠናው መክፈቻ ላይ እንደ ተናገሩት በቀጣይ 90 ቀናት ዕቅድ መተገበት አለባቸው ተብለው ከተያዙት ተግባራት ውስጥ አንዱ ስልጠና ስለሆነ በመርሀ ግብር ተይዘው ለሰራተኞቻችን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እንድሰጥ ተደርጓል፡፡
በሰኔ 20/2017ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር ት/ስ/ቁጥጥር ባለስልጣን ለልደታና አዲስ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሰራተኞች ከእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሰልጣኖች አቶ ዮሀንስ አብርሃ የፍተሻና ብቃት ማረጋገጥ ባለሙያ እና ወ/ሮ ወላንሳ ለገሰ የተቋማት ሙያ ምክር ቴክኒክ ድጋፍ ባለሙያ ተጋብዘው በአደጋ ደህንነትና መከላከል ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል፡፡
የስልጠናው ይዘቶች የአደጋ ምንነትና መንሰዎቹ፣የአደጋ ተጋላጭነት፣አደጋ የመቋቋም አቅም፣የእሳት ሳይንስ(የእሳት አፈጣጠር) የእሳት አመዳደብ፣የአሳት አጠፋፍ ዘደዎች፣ የእሳት ማጥፍያ መሳሪያዎች እና የእሳት ማጥፊያ መሳሪያዎች አፈታተሽ አብራርተው ስልናውን ሰጥቷል፡፡
ሰልጣኞችም የተሰጠ ስልጠናን አስመልክቶ ሐሳብና አስተያየት ሰጥተዋል፡፡በመጨረሻ የቅ/ጽ/ቤቱ አስኪያጁ ይህ እንደ መነሻ ለግንዛቤ ማስጨበጫ የተዘጋጅቶ የተሰጠ ስልጠና ስለሆነ ለቀጣይ Focal person ልከን ስልጠናውን ወስዶ እንዲያሰለጥን ማድረግ አለብን በማለት የመደምደምያ ሐሳባቸው በማስቀመጥ ስልጠናው ተጠናቋል፡፡
ምንጭ፡-የልደታና አዲስ ከተማ ቅ/ጽ/ቤት
#ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F
#ድረ_ገጽ; educoc.gov.et
#ቴሌግራም https://hottg.com/AAEQOCAA
#ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@educationtraning2?_t=ZM-8u2f6smztvr&_r=1
#ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302
#ዩቲዩብ https://www.youtube.com/channel/UCzbsHLZjub9c7uVPjc-vaow
ቅ/ፅ/ቤቱ አጫጭር ስልጠና ከሚሰጡ ተቋማት ጋር የክትትልና ቁጥጥር ኢንስፔክሽን አፈፃፀም ውጤት ትንተና ሪፖርት ላይ ውይይት አደረገ፡፡
(ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የካ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የትምህርትና ስልጠና ጥራት ማረጋገጥ ዳይሬክቶሬት የ2017 ዓ.ም የቴ/ሙያ አጫጭር ስልጠና የሚሰጡ ተቋማት የክትትልና ቁጥጥር ኢንስፔክሽን አፈፃፀም ውጤት ትንተና ሪፖርት ዙሪያ ላይ ዛሬ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ላይ የተቋማቱ ባለቤቶች ተወካዩች እና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱ መክፈቻ ላይ አቶ ደረጀ ሙሉጌታ የቅ/ጽ/ቤቱ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ማረጋገጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ባስተላለፉት መልዕክት በ2017ዓ.ም ስታንዳርድ ኢንስፔክሽን አገልግሎት ካገኙት 61 ተቋማት መካከል 20 ተቋማት የክትትልና ቁጥጥር ኢንስፔክሽን አገልግሎት ማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡
በዚህም ከተሠጠው ግብረ መልስ አንፃር ከግብአት ከሂደት ከውጤት ምን ያህል ማሰልጠኛ ተቋማቱ መሻሻል አሳይተዋል የሚለው ከተቀመጠው የክትትልና ቁጥጥር ኢንስፔክሽን ቼክሊስት አንፃር መታየቱን ገልጸዋል ፡፡
ተቋማቱ በስታንዳርድ ኢንስፔክሽን የታዩትን ክፍተቶች በእቅድ አካተው ክፍተቱን እየሞሉ መሄድ የሚገባቸው ሲሆን የየካ ክፍለ ከተማ የስራና ክህሎት ጽ/ቤት በቅርበት ድጋፍና ክትትል በማድረግ ለማገዝ ጥረት ማድረጋቸውን አሳውቀዋል፡፡
የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የካ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አቶ ዘመነ አብዩ በውይይቱ ማጠቃለያ ባስተላለፉት መልዕክት የአጫጭር ማሰልጠኛ ተቋማት ዘርፈ ብዙ ችግር አለባቸው አሁን ላይ ግን የተወሰነ መሻሻል እያሳዩ ሲሆን የማሰልጠኛ ተቋማት የሚሰጣቸውን ግብረ መልስ መሰረት በማድረግ መረጃዎችን በማደራጀት እና ያሉበትን ደረጃ ለማሻሻል ጥረት ማድረግ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል፡፡
ተቋማት ካለባቸው ችግር ወጥተው የትምህርት ስልጠናን በማስፋፋት እና የስራ እድል በመፍጠር በኢንዱስትሪው እንዲቀጥሉ ጥረት ማድረግ ይገባቸዋል ብለዋል፡፡
በ2017ዓ.ም የክትትልና ቁጥጥር ኢንስፔክሽን ግኝት ትንተና ሪፖርት ሰነድ በየካ ቅ/ጽ/ቤት የት/ስ/ጥ/ማረጋገጥ ዳይሬክቶሬት የቴ/ሙ/ት/ሥ/ጥ/ቡድን ባለሙያ በሆኑት በአቶ አብዱ ኢብራሂም ቀርቧል፡፡በቀረበው ሰነድም ላይ ተሳታፊዎች አስተያየት እና ጥያቄ በማቅረብ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

#ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F
#ድረ_ገጽ; educoc.gov.et
#ቴሌግራም https://hottg.com/AAEQOCAA
#ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@educationtraning2?_t=ZM-8u2f6smztvr&_r=1
#ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302
#ዩቲዩብ https://www.youtube.com/channel/UCzbsHLZjub9c7uVPjc-vaow
HTML Embed Code:
2025/06/28 02:33:12
Back to Top